Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በትግራይ የወጣቶችና ታዳጊዎች ስደት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ነው
NewsSOCIETY

በትግራይ የወጣቶችና ታዳጊዎች ስደት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ነው

ትህነግ - ለትግራይ ያበረከተው ገጸ በረከት እያደር ገሃድ እየወጣ ነው

Ethioreview newsEthioreview news—May 19, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪና ብቸኛ አማራጭ ነኝ” የሚለው ትህነግ ለህዝቡ እያበረከተ ያለው ገጸ በረከት እያደር ገሃድ እየሆነ ነው። በተለይም ከጦርነቱ በሁዋላ ይፋ እየሆኑ ያሉ መረጃዎች አስደንጋጭ ናቸው። በተለያዩ የአረብ አገራት እስር ቤቶችና በባህር በሚደርሰው መከራ በስፋት ተጎጂ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው እየተገለጸ ነው።

ኤርትራ ወጣት የሚባል ሃይል በገፍ አገሩን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የኤርትራ ጎዳናዎች ጸጥ እርጭ ብለዋል። በኢትዮጵያ የስደት ጣቢያና በተለያዩ ስፍራዎች የሚኖሩ ኤርትራዊያን ቁጥር ከዘጠኝ መቶ ሺህ በላይ እንደሆነ ይነገራል። ተዘግቶ የነበረው ድንበር ሲከፈት ብቻ 300 ሺህ የሚሆኑ የኤርትራ ተወላጆች ነቅለው ኢትዮጵያ መግባታቸውን መንግስት ማስታወቁ አይዘነጋም። በተመሳሳይ ትግራይ ከጦርነቱ መቆም በሁዋላ የታየውና እየታየ ያለው ስደት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የገለጹት የክልሉ የሚመለከታቸው ሃላፊ ናቸው። የዋዜማን ሪፖርት ከስር ያንብቡ።

ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የነበረችው ትግራይ በጦርነቱ ማግስት ከገጠሟት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንዱ የወጣቶች በገፍ ክልሉን እየለቀቁ መሰደድ ነው። 

በትግራይ ስደት ከጦርነቱ በፊትም የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ ግን እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እንደጨመረ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ሓይሽ ሱባጋድስ  ለዋዜማ ተናግረዋል።

More stories

ሶማሊላንድ በፀጥታ ስጋት ምክንያት የግብፅ የባሕል ቤተመጽሐፍን መዝጋቷን አስታወቀች

September 12, 2024

የአሜሪካ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገለፀ!!!!

February 17, 2021

“የአሜሪካ መንግስት ለምርጫ ጉዳይ አልላከኝም” ጄ ፍሪ ፌልትማን – አፍሪቃ ህብረትና አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ምርጫ ይታዘባሉ

May 12, 2021

ዶ/ር ዳንዔል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም

March 27, 2021

እድሜያቸው ከ 15 እስከ 18 የሚሆኑ ታዳጊዎች ትምሕርታቸውን አቋርጠው ከአገር እየወጡ እንደሆነ፣ አብዛኞቹ በየመን እና ሳውዲ አረቢያ እስር ቤት ወስጥ ቀሪዎቹ ደግሞ በሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እጅ እንዳሉና በርካታ ወጣቶችም በመንገድ ላይ እና በበረሃ እየሞቱ እንደሆነ መረጃዎች ይደርሱናል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የመንን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊገቡ ሲሉ በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና፣ ጅቡቲ ላይ በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ካጡት መካክል፣ አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊው ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

ይህ አስደንጋጭ ክስተት እየታየ እንኳን በቀሪዎቹ ወጣቶች ላይ የመሰደድ ፍላጎት ሲቀንስ አለመታየቱ በትግራይ ክልል ያለው ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ይላሉ ሓይሽ።

እንደ አይ ኦ ኤም ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጡት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዚህ ውቅት እንደ አገር ያለው የስደት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሚያሳይ ሲሆን ፣ በትግራይ ያለው ግን ከዚያ የተለየና ለመቆጣጠርም አዳጋች የሆነ ነው።

ትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከ 500 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች አሉ፣ በመጠለያ ጣቢያው በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ባለመኖሩና ምንም አይነት ለነገ የሚሉት ተስፋ የሚታያቸው ባለመሆኑ ወጣቶቹ ስደትን ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገዋል ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ወጣቶቹ በብዛት እየተሰደዱ ያሉት ከምሥራቅ እና ደቡብዊ ዞኖች፣ከሰሜን ምዕራብ እና ሰሜናዊ የትግራይ አካባቢዎች፣ከመቀሌ ከተማ እና አካባቢዋ በተወሰነ መልኩ እንደሆነ ኃላፊው ሓይሽ ተናግረዋል።

ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዲሁም የሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ለመሰደዳቸው ሌላው ምክንያት እንደሆነ ሓይሽ ያስረዳሉ።

ዋዜማ በዚሁ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማኅበርን ያነጋገረች ሲሆን ማኅበሩ በክልሉ ያለው ሥራ አጥነት ያስከተለው የወጣቶች ስደት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል።

የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሠናይ ከሓሳይ ለዋዜማ እንደተናገሩት ማኅበሩ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመተባበር በ 10 ወርዳዎች፣ በ 30 ቀበሌዎችና በ1 ሺህ 200 መቶ ወጣቶች ላይ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል።

የጥናቱም ፍለጋ ከጦርነቱ በኋላ የወጣቱ መተዳደሪያ ምንድነው?፣ትምሕርት ጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት አንጻር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለዋዜማ አስረድተዋል። 

ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ባለመኖራቸውና በክልሉ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የሚጨበጥ ተስፋ ባለመኖሩ ምክንያት ካሉት ወጣቶች መካከል ግማሽ ያህሉ የመሰደድ ሃሳብ ያላቸው እንደሆኑ በተደረገው ጥናት መሰረት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

ጥናቱ እንደሚያመለክትው በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ካሉ ወጣቶች መካከል 81 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ከጦርነቱ በፊት የራሳቸው ተቋም የነበራቸው፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ፣ መልካም የሚባል ሕይወት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸውና ከጦርነቱ በኋላ ግን ያላቸውን ጥሪት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያጡ ናቸው ሲሉ።

ከትምህርት ፍላጎት ጋር ተያይዞ በወጣቶቹ ላይ በተደረገው ጥናት ካሉት ወጣቶች መካከል 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የመማር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው የሚሉት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸን ያላቸውን ነገር በሙሉ ስላጡ እኛን የሚያስተምሩበት አቅም የላቸውም የሚል እንደሆነ አብራርተዋል።

ከሥራ ፈጠራ አንጻር፣ 31 በመቶ የሚሆኑት የራሳችን ሥራ ፈጥረን እንሰራለን የሚሉ እንደሆኑ 29 በመቶዎቹ ደግሞ በተለያዩ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ተቀጥረን መስራት አለብን የሚል ሃሳብ ያላቸው፣ ቀሪዎቹ ግን የመሰደድ ፍላጎት ያላቸው ናቸው ብለዋል

ከነዚህ የመሰድድ ፍላጎት ካላቸው ውስጥ 53 በመቶዎቹ እድሜያቸው ከ 26 እስከ 35 ባለው መካከል የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ግን ከ 15 እስከ 25 ባለው መካከል እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ በክልሉ ካሉ ወጣቶች 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበይነ መረብ አገልግሎት እንደማያገኙ 97 በመቶ የሚሆኑት የኮምፒዩተር አገልግሎት፣ 29 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የስልክ አገልግሎት የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ሥራ ለመፈለግና የሚወጡ የሥራ እድሎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን ለማየት አስቻይ ሁኔታ የላቸውም በማለት ተናግረዋል።

ከማኅበራዊ ሕይወታቸው ጋር ተያይዞ 89 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ትዳር የመያዝ፣ ኃላፊነት የመውሰድና ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንደሌላቸው ባደረጉት ጥናት ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል።

በሌላ በኩል ትግራይ ከጦርነቱ መገባደድ በኋላ የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተደማምረው የደቀቀው ምጣኔ ሀብቷ ለወጣቱ መሰደድ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል።

ዋዜማም በሕገወጥ መንገደ ተሰደው በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች በስልክ አነጋግራለች።

ሕሉፍ ዓባይ ተወልዶ ያደገው በሽረ እንዳ ሥላሴ ከተማ ገባር ሽረ በተባለ አካባቢ እንደሆነ ለዋዜማ የገለጸ ሲሆን፣ በዚያም የሚተዳደረው በብረት ብየዳ ሥራ እንደነበር፣ በጦርነቱ ምክንያት ግን ያለው ሃብት ንብረት በሙሉ እንደወደመትና ባዶ እጁን እንደቀረ ይናገራል።

ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆኑን የሚገልጸው ሕሉፍ የሚያደርገው ቢጠፋው የራሱንንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሰንበት በሕገ ወጥ መንገድ መሰደድን መምረጡን ገልጿል።

ሕሉፍ ያሰበውና የሆነው ለየቅል እንደሆነበትና በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ኃይሎች ተይዞ በእስር ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት መግፋት ከጀመረ አምስት ወራት መቆጠራቸውን አስረድቷል።

ሌላኛው ከውቅሮ ከተማ ተሰዶ እንደወጣና ትምህርቱን ከአስራ አንደኛ ክፍል እንዳቋረጠ የሚናገረው ሀበን ተስፋይ ቤተሰቦቹ ሊያስተምሩት አቅማቸው ባለመፍቀዱ ስደትን መምረጡን ገልጿል።

በእስር ቤቶቹ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰደው የወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መኖራቸውን ዋዜማ በእስር ቤቱ ወስጥ ካሉ ሰዎች ማረጋገጥ ችላለች።

ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው የክልሉ ወጣቶች ቢሮና የወጣቶች ማኅበር ወጣቶቹን ከስደት ለመታደግ በፌዴራል መንግስቱም ይሁን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከ [ዋዜማ] የተወሰደ

NEWSSOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የሴቶች የላይኛው መራቢያ ክፍልን የሚያጠቃ በኢንፌክሽን አማካኝነት የሚከሰት በሽታ ምንነትና መዘዙ
የኢራኑን ፕሬዚዳንትና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሳፈሩበት ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ፤ ፍለጋው ቀጥሏል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2