Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  የሚረብሽ ዜና – በወጡበት እየቀሩ ያሉት የትግራይ ሴቶች
TIPS 1

የሚረብሽ ዜና – በወጡበት እየቀሩ ያሉት የትግራይ ሴቶች

Ethioreview newsEthioreview news—July 9, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail


በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አፈና፣ ግድያ እና ፆታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተጎጂ ቤተሰቦች እና የሴቶች መብት ተሟጋቾች እየገለጹ ይገኛሉ።

በመቀለ ባለፉት 11 ወራት 12 የሚሆኑ ሴቶች መገደላቸውን የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ለቢቢሲ ተናግሯል።

*ማሳሰቢያ፡ ይህ ታሪክ የሚረብሽ ይዘት አለው።

ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ በምሥራቅ ትግራይ ዞን አዲግራት ከተማ ነዋሪ የነበረችው የ44 ዓመቷ አዳነሽ አብርሃ አስከሬኗ ከከተማዋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው በደቡብ ትግራይ መኾኒ ውስጥ ነው የተገኘው።

“የልጄን አስከሬን ከስድስት ወር በኋላ አገኘሁት” ያሉት እናቷ ስምረት ተክሉ፣ አስከሬኗ በጎመን ማሳ ውስጥ ተጥሎ እንደነበር ይናገራሉ።

ቢቢሲ በአዳነሽ አካል ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጥቃት፣ አስከሬኗ የተገኘበት እርሻ እና በዚያን ጊዜ የለበሰችውን ልብስ የሚያሳይ ምስል አይቷል።

ለሦስት ወራት የጠፋችው የ16 ዓመቷ የማኅሌት ተኽላይ አስከሬንም በአድዋ ከተማ በሚገኘው ቻይና ካምፕ ውስጥ ተቀብሮ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ሌሎች የፆታዊ ጥቃት እና አሰቃቂ ግድያ ሰለባዎች የሆኑ ማንነታቸው እንዲሁም ያሉበት ሁኔታ ያልታወቁ ሴቶች እንዳሉ በሴቶች ጉዳዮች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ባለፈው የካቲት ወር በሰሜን ምዕራብ ዞን ውስጥ ወደ ሰለኽላኻ ከተማ በሚያስገባው ድልድይም እንዲሁ የአንድ ሴትን አስከሬን ፖሊስ አግኝቶ ነበር።

ማንነቷን የሚገልጽ መታወቂያ ማግኘት ባለመቻሉ ስሟን፣ እድሜዋን እና የመጣችበትን አካባቢ ማወቅ እንዳልተቻለ የላዕላይ ቆራሮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለነ አስገዶም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

መጋቢት 19/2016 ዓ.ም. በመቀለ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ከተደረገ በኋላም ፖሊስ የተገደልችበትን ሁኔታ እና ምክንያት ማወቅ አልቻለም።

“እኛ አላወቅናትም። ሬሳዋ ለረጅም ጊዜ ተጥሎ ስለቆየ ማንነቷን ለይቶ ማወቅ አልቻልንም። ለብሳው የነበረውን ልብስ ይዘን ወደ አጎራባች ወረዳዎች ሄደን ነበር። እስከ አክሱም እና አድዋ ድረስ በመሄድ የሚያውቃትን ለማግኘት ብንሞክርም አልተሳካልንም። ስለዚህ ከሌላ ቦታ አምጥተው ጥለውታል ብለን ነው የምንገምተው” ብለዋል።

በትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ጉዳይ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ዓለም ምስግና፣ ወንጀሎቹን በቁጥር ለመለየት እንደሚያስቸግር እንዲሁም ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሠራ እንደሆነ ይናገራሉ።

ከእነዚህ ሰለባዎች መካከል አንዳንዶቹ እነማን ናቸው? ቤተሰቦች ስለልጆቻቸው ምን ይላሉ?

‘ልብሷን፣ ጫማዋን እና ፀጉሯን አቆዩልኝ’

አዳነሽ አብረሃ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባለቤቷ ጋር 5፡30 ላይ ‘ጸበል ተጠምቄ እመለሳለሁ’ ብላ ከቤቷ እንደወጣች አልተመለሰችም

እድሜያቸው 85 የሆኑት ወይዘሮ ስምረት ተክሉ፣ መኖርያ ቤታቸውን የሞሉት የተለያየ ቀለማት እና መዓዛ ያላቸውን አበቦች ሲያዩ ልጃቸው አዳነሽ አብረሃን አስታውሰው ያነባሉ።

ነገር ግን አሁንም ድረስ በፍርሃት እና በድንጋጤ ውስጥ ያለችውን ሌላኛዋ ልጃቸውን “አታልቅሺ” እያሉ ሊያጽናኑ ይሞክራሉ።

አዳነሽ አብረሃ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም. ከባለቤቷ ጋር 5፡30 ላይ “ጸበል ተጠምቄ እመለሳለሁ” ብላ ከቤቷ እንደወጣች የቤተሰቧ አባላት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ስልኳ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሲሠራ ነበር፤ ከዚያ ግን ተዘጋ።

“አርብ ጸበል ተጠምቄ . . . ቅዳሜን ደግሜ ለእሁድ የሚሆን ይዤ እመጣለሁ ብላ ለሠራተኛ መልዕክት ትታ ሄደች። የእሷን መምጣት ስጠባበቅ ብዙ ቅዳሜዎች አለፉ” ይላሉ እናቷ።

አዳነሽ ተወልዳ ያደገችው አዲግራት አካባቢ ነው። የቤተሰቧ አባላት እንደ አንድ ደግ፣ ታታሪ፣ ለውጥ ወዳድ፣ ልጅ እና ሰላማዊ ትዳር የምትመኝ ወጣት ሴት ያስታውሷታል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የትግራይ ወረዳዎች በመምህርነት አገልግላለች። ሙያው ውስጥ ባሳለፈቻቸው አምስት ዓመታት የተዋወቀችውን የሥራ ባልደረባዋ አግብታ ነበር።

በመቀለ ዩንቨርስቲ የሒሳብ ትምህርት ተምራለች።

በትዳር 15 ዓመታትን ያሳለፈችው አዳነሽ ከማስተማር ሙያ ወጥታ የራሷን ሥራ ትሠራ እንደነበር ቤተሰቦቿ ተናግረዋል።

አዳነሽ ሕይወቷን ለማሻሻል ከአምስት ዓመት በፊት ወደ እስራኤል ሄዳም ነበር።

ሆኖም ከስድስት ወራት በኋላ በጤና ችግር ምክንያት ወደ አገሯ መመለሷን እናቷ ወ/ሮ ስምረት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ወደ እስራኤል ሄጄ አመጣኋት። እዚህ ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር ተንከባከብኳት – ከዚያም ከእኔ ጋር መኖር ጀመረች።”

ጤንነቷ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሲመለስ አዳነሽ የጭማቂ መሸጫ ሱቅ ከፈተች። ራሷን ለመደገፍ የአገር ውስጥ እና የውጭ ችግኞችንም ትሸጥ ነበር።

ከዚያም መስከረም ወር ላይ እንደወጣች ስተቀርባቸው ጊዜ፣ ያያት ሰው ካለ መረጃ እንዲሰጣቸው ምስሏን እና ስሟን በፌስቡክ ላይ አካፈሉ። በተለያዩ ገዳማት እና አድባራትም ሲያፈላልጓት ቆዩ።

ከዚያም መኾኒ በሚገኝ የማሽላ ማሳ ውስጥ ተጥላ የተገኘች ሴት እንዳለች በደረሳቸው መረጃ ማምነቷን ለመለየት ለብሳው የነበረውን ልብስ እና ጫማ ለፖሊስ አሳውቀው ልጃቸው መሆኗ ተረጋገጠ።

“ነገር ግን በደንብ እስኪጣራ ድረስ አዳነሽ ስለመሆኗ ለቤተሰቡ አልተናገርንም” ይላል አጎቷ ኮማንደር ፍትሃነገሥት በርሄ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ እናቷ ደውለው ገንዘብ የጠየቁ እና የባንክ ሒሳባቸውን የላኩ ግለሰቦች ነበሩ።

“በጥር ወር. . . 100,000 ብር ስጡን አሉን። . . . ግን እሷ አልነበረችም። በግንቦት ወር መተማ ውስጥ እንዳለች ነገሩን። አሳዩን ብንል ግን ምንም የለም” ይላል።

በዚህ ሁኔታ ለወራት በጭንቀት ያሳለፉት ወ/ሮ ስምረት ቀደም ሲል የአዳነሽን ሞት የተረዱት የቤተሰብ አባላት ከስድስት ወራት በኋላ መርዶውን እንዳረዷቸው ይናገራሉ።

“ከስድስት ወር በኋላ ነበር የሰማሁት። እዚያ ስሄድ ይህች ሟች የኔው ናት አልኳቸው። ቀሚሷን ጫማዋን ፀጉሯንም አቆይተውልኝ አየሁት። ነገር ግን ተጠርጣሪው እስካልተያዘ ድረስ አስከሬኑ እንደማይሰጥ ስለነገሩኝ እንዳላየሁ እንዳልሰማሁ ቀን ከሌሊት ሳለቅስ ከረምኩ።”

የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ኮማንደር ዓለም እንደተናገሩት ተጠርጣሪው መያዙን እና የአስከሬን ምርመራ ተጠናቆ ውጤቱን ለዐቃቢ ሕግ እንደሚተላለፍ ተናግረዋል።

የአዳነሽ አብረሃ የቀብር ስነ ስርዓት ሰኔ 6 ቀን 2016 ተፈጽሟል።

የጓደኛዋን ልደት ልታከብር ወጥታ ያልተመለሰችው የ32 ዓመቷ ዘውዲ

“የቤተሰባችን ጧሪ ነበረች”

ነሐሴ 2015 ዓ.ም. አጋማሽ ላይ አዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ፣ መቀሌ አዲ ሓውሲ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 1፡30 ላይ ብዙዎችን ያስደነገጠ ግድያ ተፈጽሟል።

More stories

ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር ?  ሰባት የፋኖ ቡድኖች ያሉበት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

July 22, 2024

በኦሮሚያ የሰላም ውይይት ፍንጭ ተሰማ፤ “ጃል መሮ እጅ ካልሰጡ ከጃል ሰኚና ከመንግስት አያመልጡም”

October 11, 2024

ኢምሬት ከፈረንሳይ ጋር ያሰረችውን የ 20 ቢሊዮን ጦር መሳሪያ ግዢ አቋረጠች

August 31, 2024

ኢትዮጵያ እንዲህ ተዘርፋለች፤ ” አሁንም ሌቦች አሉ የመንግስት ሌብነት ማለት ግን ይህ ነው”

July 7, 2024

በወቅቱ ታርጋ የሌላት መኪና የያዙ ሰዎች ግለሰቧን ከነቦርሳዋ ለተወሰነ ርቀት እየጎተቱ ከወሰዱ በኋላ ጥለዋት ገድለዋት ጠፉ የሚሉ መረጃዎች መሠራጨት ጀመሩ።

ከእሷ ጋር ነበረች የተባለችው ጓደኛዋ ራሷን ስታ ወድቃ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ገብታ ነበር። ከዚያ በኋላ በምርመራ ላይ ከሚገኙ አምስት ተጠርጣሪዎች መካከል አንዷም ሆና ነበር።

ግድያውን የፈፀመው ማነው? ቤተሰቦቿስ ለምን ግልጽ መረጃ እስካሁን አላገኙም? ምንም የሚታወቅ ነገር የለም።

ነገር ግን ግድያው አሰቃቂ በሆነ መንገድ መፈጸሙ ግልጽ ነው። ዘውዲ ሃፍቱ በዚህ መልኩ ከሞተች 11 ወራት አልፈዋል።

“እስካሁን ፍትህ አላገኘንም። በፍርድ ቤት ቀጠሮ ከመመላለስ የዘለለ የሚጨበጥ ነገር አልተነገረንም። ምን እንደተፈጠረ አናውቅም፤ ምንም መረጃ የለንም። ይህ ሆነ ብሎ የነገረን የለም” ስትል ታናሽ እህቷ ብርቱካን ሃፍቱ ለቢቢሲ ተናግራለች።

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የቀድሞ ጓደኛዋ በዋስ ስትለቀቅ ሌሎች አራት ሰዎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።

የ32 ዓመቷ ዘውዲ ተወልዳ ያደገችው መቀሌ ማይ አንበሳ በሚባለው አካባቢ ነው።

“ወላጆቻችን ተቸግረው ነው ያሳደጉን። እናታችን ሻይ እየሸጠች ነው ያሳደገችን፤ አባታችን ደግሞ የጥበቃ ሠራተኛ ነው” ትላለች።

ዘውዲ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘች ሲሆን፣ በሼባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አካውንቲንግ ተምራለች።

ዘውዲ ምሥጢራዊ በሆነ ሁኔታ በተፈጸመባት ግድያ ከመሞቷ በፊት ሥራዋ ዕለታዊ ዕቁብ መሰብሰብ ነበር።

በተገደለችበት ዕለትም እንደተለመደው ዕቁብ ስትሰበስብ ውላ ምሽት ላይ የጓደኛዋን ልደት ለማክበር ነበር ከጓደኛዋ ጋር የወጣችው።

“ገንዘቡን ተቀብያት ልብሷን ቀይራ ወጣች። ነገር ግን ከሄደች አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አይደር ገብታለች ተብሎ ተደወለልኝ።”

ከዚያ በኋላ ቃሏን ለመስማት አልታደለችም።

“እነዚህ ተመሳሳይ ጥቃቶች በሴቶች ላይ ሲደጋገሙ አስደንግጦኛል። ወደ ሥራ ወጥቼ እስክመለስ ድረስ እፈራለሁ። ይህ የሁሉም ሴቶች ፍርሃት ይመስለኛል” ትላለች።

የ16 ዓመቷ ማህሌት ተኽላይ

እንደወጣች የቀረችው ታዳጊ

በመኝታ ክፍሏ ውስጥ “ሁሉም ነገር ቆንጆ ነው፣ ግን ማንም አያስተውለውም፣ ሁልጊዜ አዎንታዊ አስብ፣ ማንንም አትነቅፍ . . .” ወዘተ የሚሉ ጥቅሶች አሉ።

ተምራ፣ ከታላቅ እህቷ ጋር ንግድ ለመሥራት እና በስማቸው የሚጠራ ነገር ለመትከል ከፍተኛ ፍላጎት ነበራት፤ ሁሌም ስለ አዳዲስ ፈጠራዎች ይነጋገሩ ነበር።

የ16 ዓመቷ ማኅሌት ተኽላይ ዘንድሮ አገር አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ እና ጥሩ ውጤት ለማምጣት በዝግጅት ላይ ነበረች። ከትምህርቷ ጎን ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን እና ቋንቋ በማጥናት ጥሩ ውጤት አስመዝግባ ነበር።

ነገር ግን 16ኛ ዓመቷን በያዘች በአንድ ወር ውስጥ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ከቤቷ ወጥታ ወደ ቋንቋ ት/ቤት ስትሄድ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታገተች።

በዕለቱ ቤተሰቦቿ በግል ስልኳ ተደውሎ ‘ሦስት ሚሊዮን ብር’ እንዲከፍሉ እንደተጠየቁ ያስታውሳሉ።

ከዚያም ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ደውለው ቤተሰቡ ገንዘቡን ለመክፈል ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ጠየቁ።

ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ የማኅሌት ድምፅ አልተሰማም፤ የጠለፏት ሰዎች ያሉበት ቦታም አልታወቀም።

የማኅሌት ቤተሰቦች ግን ከዛሬ ነገ ትገኛለች በሚል ተስፋ ፖሊስ እና ማኅበረሰቡ ትብብር እንዲያደርጉ ጥረት ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

አብዛኛው የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥቁር ልብስን ከሞት እና ከመጥፎ ዕድል ጋር ስለሚያያይዘው በቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ጥቁር እንዳይለብስ አያቷ ከልክለው ነበር።

ከማኅሌት እገታ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ስለነበር፣ ትገኛለች የሚል ትልቅ ተስፋ በቤተሰቧ ዘንድ ነበረ።

“ማሂ ስትመጣ ነጭ ለብሰን ፎቶ ተነስተን የሁላችንም ፎቶ ቤት ውጥ እንሰቅላለን። ስለት ወደ ገባንባቸው ገዳማት ይዘናት እንሄዳለን፤ አእምሮዋ እንዲታደስ እናደርጋለን” እያሉ በተስፋ ውስጥ እንደነበሩ እህተዕ ሚሊዮን ትገልጻለች።

ሆኖም ፖሊስ ከሦስት ወራት በኋላ ማኅሌት ተኽላይ ተገድላ እንደተቀበረች ተጠርጣሪዎች ማመናቸውን የአድዋ ፖሊስ አዛዥ አቶ ተስፋይ አማረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ስለ ግድያው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት አዛዥ፣ ተጠርጣሪዎቹ የተቀበረችበትን ቦታ እንደጠቆሙ እና አሁንም ምርመራው እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“ተጠርጣሪዎቹ በሰጡን መረጃ መሠረት አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ሄድን” በማለት ‘ቻይና ካምፕ’ የሚባል ቦታ ላይ ሬሳው እንደተገኘ አስረድተዋል።

“የቤታችን ድምቀት ነበረች” ስትል ማኅሌትን የምታስታውሳት ሚሊዮን፣ ከታናሽ እህቷ ጋር ስታደርጋቸው የነበሩ የዕለት ተዕለት ንግግሮች፣ ሳቅ እና ጨዋታን ትናፍቃለች።

“አሁን የምንፈልገው ድምፃቸው የተፈኑ ብዙ ሴቶች ፍትህ እንዲያገኙ ነው” ትላለች ማኅሌት መኝታ ክፍሏ ውስጥ የሠራቻቸውን የተለያዩ የግድግዳ ጽሑፎችን እና ቅርጻ ቅርጾችን እያሳየች።

የከተማው ፖሊሲ የአስከሬን ምርመራው ውጤት “ወራትን” ሊወስድ እንደሚችል እና በአሁኑ ጊዜ አስተያየት መስጠት እንደማይችል ይናገራል።

ፍትሕ የሚጠይቁ የትግራይ ሴቶች

በተለይ ከሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ በትግራይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ እንደመጣ ሲገለጽ ቆይቷል።

ባለፈው ወር መጀመሪያ ላይ በመቀሌ እና አዲግራት ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር።

ሰልፎቹ ላይ የተገኙ የሴቶች ማኅበር እና የትግራይ ፍትህ ቢሮ ተወካዮች “በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ዘግናኝ ግፍ” እንደሚያወግዙ ተናግረዋል።

የሴቶች ማኅበር ኃላፊ ወይዘሮ አበባ ኃይለሥላሴ “ፍትህ ሊረጋገጥ ባለመቻሉ” ወንጀሉ ጭካኔ በሞላበት ሁኔታ እየቀጠለ እንደሆነ ይናገራሉ።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐዲሽ ተስፋ በበኩላቸው “ሕግ እና ሥርዓትን ለማስጠበቅ እና አጥፊዎችን ለሕግ ለማቅረብ እየሠራን ነው” ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ከትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮማንደር ዓለም ምስግና ከጦርነቱ በኋላ በክልሉ የፀጥታ መዋቅር ላይ ክፍተቶች እንዳጋጠመ እና በግለሰቦች ላይ ግድያን ጨምሮ ከባድ በጦር መሳሪያ የታገዙ ወንጀሎች ሲፈጸሙ እንደቆዩ ይናገራሉ።

በሴቶች እና በሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃትንም አውግዘዋል።

በመቀሌ ከተማ ብቻ ባለፉት 11 ወራት ወደ 12 የሚጠጉ ሴቶች መገደላቸውን የሚገልጹት የፖሊስ ኃላፊው፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን በደል በትኩረት ለመከታተል ከፍትህ አካላት ጋር እየሠሩ እንደሆነም ገልጸዋል።

ከተፈጸሙት ግድያዎች መካከል ከአንዱ በስተቀር “ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ ነው። . . . ዐቃቤ ሕግ አንዳንድ ማስረጃዎችን ከፌዴራል መንግሥት እየጠበቀ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሁኔታዎች ተመቻችቷል” ብለዋል።

በጦርነቱ ወቅት በሁሉም የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና በጦርነቱ የተወሰኑ የኮሚሽኑ መርማሪ እና የወንጀል ምርመራ ባለሙያዎች መሞታቸውን በመግለጽ ይህም ወንጀሎችን በሚመረመሩበት ፍጥነት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩንም አስረድተዋል።

Source Bbc Amharic

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
How Ethiopia’s Red Sea deal could impact Israel, Egypt, and the UAE
የኃይሌ ክስ እርግጥ ለኦሎምፒክ ውጤት ከመቆርቆር የተነሳ ነው?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2