Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  “በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ”
TIPS 1

“በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ”

Ethioreview newsEthioreview news—July 4, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባቀረቡት ሪፖርት የሰጡትን ማብራሪያ አንኳር ነጥቦች በየሴክተሩ በመለየት ከታች አትመናል:

ሙስናን በሚለከት

“ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፡፡ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት፡፡ ለዚህም ነው መንግስት የህግ ማሻሻያዎችን እያደረገ ያለው፡፡ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅም ይህን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ፤ ይህን መጠየቅ የሚችል ህግ አልነበረንም፡፡ አዋጁ ይህን ችግር በመቅረፍ የህግ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን አዋጁ ያጠቃናል ያሉ ሌቦች ከወዲሁ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው፡፡ በመሆኑም ሌብነትን በመታገል ረገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተግባር የተጨበጠ ስራ ማከናወን አለበት፡፡”

ህግ ማስከበርን በተመለከተ

More stories

ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር ?  ሰባት የፋኖ ቡድኖች ያሉበት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

July 22, 2024

በኦሮሚያ የሰላም ውይይት ፍንጭ ተሰማ፤ “ጃል መሮ እጅ ካልሰጡ ከጃል ሰኚና ከመንግስት አያመልጡም”

October 11, 2024

ኢምሬት ከፈረንሳይ ጋር ያሰረችውን የ 20 ቢሊዮን ጦር መሳሪያ ግዢ አቋረጠች

August 31, 2024

ኢትዮጵያ እንዲህ ተዘርፋለች፤ ” አሁንም ሌቦች አሉ የመንግስት ሌብነት ማለት ግን ይህ ነው”

July 7, 2024

“ሶስት ክላሽ ሲይዙ አራት ኪሎ ይታያቸውና ውርውር የሚሉ አካላት፤ ትንሽ ሲቆነጠጡ ደግሞ ጀኖሳይድ ይላሉ፡፡ ይህ ተገቢነት የለውም፡፡ መንግስት በሰለጠነ መንገድ ችግሮች በውይይትና ድርድር እንዲፈቱ ቅድሚያ መስጠቱን እንደ ድክመት የሚቆጥሩ ካሉ፤ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ነው፡፡”

ሰላምን በተመለከተ

“ኢትዮጵያ ለረዥም ዘመናት በግጭትና ጦርነት አዙሪት ውስጥ አልፋለች፡፡ ይህ የመገዳደል ታሪክ  በእኛ ትውልድ ሊቆም ይገባል፤ መንግስት ለሰላም የሚከፈል ማነኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነው፡፡ባለፉት ጊዜያትም መንግስት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ በሆደ ሰፊነት በርካታ ርቀት ተጉዟል፡፡ በግጭትና ጦርነት ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን መያዝ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ለኢትዮጵያ ዛሬም ነገም የሚበጀው በሰላምና በሰከነ መንገድ ተወያይቶ ችግሮችን መፍታት ነው፡፡”

የለውጡ ሂደትን በተመለከተ

“ሀገራዊ ለውጡ እንዲመጣ ያደረጉ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ፤ አንደኛው ነባር ችግሮች ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወቅታዊ ስብራቶች ናቸው፡፡ ከዚህ አኳያ ነባር ችግሮችን በአገራዊ ምክክር እና ሽግግር ፍትህ ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡ በምክክሩ ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንሰራበት ሲሆን፤ ያለፉ በደሎችን ደግሞ በሽግግር ፍትህ የሚፈቱ ይሆናል፡፡ ወቅታዊ ችግሮችን ደግሞ በተቋማት ሪፎርም እየተፈቱ ይገኛሉ፡፡ከዚህ አኳያ ለተመዘገቡ ስኬቶች እውቅና እየሰጠን የሚቀሩትን ደግሞ በጋራ መስራት አለብን፡፡”

ጤናን በተመለከተ

“በዘንድሮው ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ክትባት ተሰጥቷል፡፡ የኩፍኝ ወረርሽኝን ለመከላከልም በ58 ወረዳዎች ክትባት ተሰጥቷል፡፡ የወባ አጎበር ስርጭትም ተከናውኗል፡፡ በተለይ የመድሃኒት አቅርቦትን በአገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከ8 በመቶ ወደ 36 በመቶ ማደረስ ተችሏል፡፡”

ሙስናን በሚለከት

“ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፡፡ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት፡፡ ለዚህም ነው መንግስት የህግ ማሻሻያዎችን እያደረገ ያለው፡፡ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅም ይህን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ፤ ይህን መጠየቅ የሚችል ህግ አልነበረንም፡፡ አዋጁ ይህን ችግር በመቅረፍ የህግ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን አዋጁ ያጠቃናል ያሉ ሌቦች ከወዲሁ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው፡፡ በመሆኑም ሌብነትን በመታገል ረገድ  ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተግባር የተጨበጠ ስራ ማከናወን አለበት፡፡”

የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተመለከተ

“የፕሪቶሪያው ስምምነት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ረገድ የባህል ለውጥ ያመጣንበት ነው፡፡ ተኩስን በማቆም አገልግሎትን በማስጀመር ትልቅ ድል አግኘተንበታል፡፡ ባንኮች፣ አየር መንገድ፣ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ ጀምረናል፡፡ ይህ ጅምርም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡”

ትምህርትን በተመለከተ

“የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መንግስት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡ በዚህም 30 ሺህ የሚሆኑ አዳዲስ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ይህ ብቻ ሳይሆን በርካታ ተማሪዎችም የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የትምህርት ስርዓቱ አካታች እንዲሆንም ዘመናዊ የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ ነገር ግን አገራዊ ለውጡን ተከትሎ አንድም ዩኒቨርሲቲ አልገነባንም፡፡አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ያለነው ጥራትን ማረጋገጥ ላይ ነው፡፡”

የግብርና ግብዓትን በተመለከተ

“ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳባሪያ ከውጭ ታስገባለች፡፡ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከሚወጣው ወጪ ባሻገር ለአርሶ አደሩ ለማጓጓዝ ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ ይጠይቃል፡፡ መንግስት ይህን ሁሉ ታሳቢ በማድረግ በዘንድሮው ዓመት ስራው ቀደም ብሎ ነው የጀመረው፡፡ እስካሁን ባለው ሂደትም 13 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ መጓጓዝ ተችሏል፡፡ ቀሪ 2 ሚሊዮን የሚሆነው ጅቡቲ ደብ እየደረሰ ነው፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ኢትዮጵያ በምርጥ ዘር አቅርቦት እራሷን ለመቻል እየሰራች ነው፡፡ በመስኖ ልማትም ትልቅ እምርታ እየተመዘገበ ነው፡፡ ለአብነትም በዘንድሮው ዓመት ብቻ 40 ሺህ የሞተር ፓምፕ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፡፡”

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ

“የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡ በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፡፡ምርታማነትን ማሻሻልም ሌላኛው ስራ ነው፡፡ በዘንድሮው ዓመት ከዓለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡በተጨማሪም መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፡፡ ይህ ሁሉ የሚከናወነው የኑሮ ውድነቱ ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል ነው፡፡ በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ ተችሏል፡፡”

የፋይናንስ ዘርፉን በተመለከተ

“የፋይናንስ ሴክተሩ በበርካታ አመላካቾች ጤናማ ሂደት ውሰጥ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ12 ሺህ 800 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም የባንክ ደብተር አውጥተው እየተጠቀሙ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማይመለስ ብድር አማካኝ አሃዝ 5 በመቶ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ግን 4 ነጥብ 5 በመቶ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ከዓለም አማካኝ ያነሰ ነው፡፡ ባንኮች ከሚያቀርቡት ብድር ከ80 በመቶ በላይ የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ነው፡፡ ይህም የፋይናንስ ዘርፉ በጤናማ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን ባንኮች ከአገር ውስጥ ባለፈ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን ከወዲሁ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡”

ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾችን በተመለከተ

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት ወጪ ንግድ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከሐዋላ አገልግሎትም 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ገቢ ተገኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም በምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳቢ አገር ናት፡፡ በበጀት ዓመቱም 3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ችላለች፡፡ ስንዴን ጨምሮ በተኪ ምርቶችም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ነው፡፡ ለአብነትም በበጀት ዓመቱ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት ተችሏል፡፡


ገቢ አሰባሰብን በተመለከተ

“ባለፉት 11 ወራት መንግስት 466 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ችሏል፡፡ ይህም ከተያዘው እቅድ አንጻር የ96 በመቶ አፈጻጸም አለው፡፡ ነገር ግን  ይህ ከኢትዮጵያ አገራዊ ጥቅል ምርት አንጻር 7 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ይህም ከፍተኛ የሆነ ግብር መሰወር መኖሩን  አመላካች ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ ነው፡፡ ይህንን ጥረትም ዜጎች ሊያግዙ ይገባል፡፡”

ለኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጉ ስድስቱ  “መ” ዎች:-

1) መወያየት- ችግሮችን ከግጭት ይልቅ በውይይት መፍታት

2) መትከል- ከችግኝ ባሻገር ለኢትዮጵያ የሚበጁ ተቋማትን በመትከል ሀገርን ማጽናት

3) መታደስ- እሳቤዎቻችንና አኗኗራችንን ወቅቱን በዋጀ መልኩ ማደስ

4) መሰብሰብ- ግብርን ጨምሮ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ገቢዎችን መሰብሰብ

5) መነጠል-  ከክፉ ሃሳብን፣ ከዘረኝነት እና ከሰፈርተኝነትን መነጠል

6) መዘጋጀት- አሁናዊ ሁኔታዎችን በሚዋጅ መልኩ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ማዘጋጀት ፤ ለዚህ ደግሞ እርስ በርስ ማገር በመሆን አገርን ማጠናከር፡፡

ዲፕሎማሲን በተመለከተ

“ኢትዮጵያ የደም መሰዋትነት በመክፈል ጭምር ለሶማሊያ ሰላም ሰርታለች፤ አሁንም ለሶማሊያ የምንመኘው ሰላምና ልማት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፍላጎት እያስመዘገበች ካለው የኢኮኖሚ እድገት አንጻር የባህር በር ማግኘት ብቻ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የትኛውም አካል ሳይጎዳ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ በውይይት እውን ማድረግ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ጥያቄም ተገቢና ቅቡልነት ያለው ነው፡፡ በዚህ ላይ ጥያቄ ካለም እርስ በርስ በመነጋገር መፍታት ይቻላል፡፡  በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ችግሮቻቸውን በሰላም እንዲፈቱ ገለልተኛ በሆነ አግባብ እንዲፈታ እየሰራች ነው፤ ይህንንም አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡”

ሙስናን በሚለከት

“ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፡፡ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት፡፡ ለዚህም ነው መንግስት የህግ ማሻሻያዎችን እያደረገ ያለው፡፡ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅም ይህን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ፤ ይህን መጠየቅ የሚችል ህግ አልነበረንም፡፡ አዋጁ ይህን ችግር በመቅረፍ የህግ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን አዋጁ ያጠቃናል ያሉ ሌቦች ከወዲሁ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው፡፡ በመሆኑም ሌብነትን በመታገል ረገድ  ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተግባር የተጨበጠ ስራ ማከናወን አለበት፡፡”

Via AddisAbaba communication



NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ገቢ እና ወጭን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምን አሉ?  የውጭ ባንኮች ለዉድድር 
መፈንቅለ መንግስት መታሰቡን አብይ አሕመድ አስታወቁ፤ ሙሉ የአፈጻጸሙን ዕቅድ መንግስት ያውቀዋል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2