Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ECONOMY  ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ
ECONOMY

ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ

Ethioreview newsEthioreview news—July 10, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ብሔራዊ ባንክ አዲሱን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፥ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚረዱ እርምጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

ዛሬ ይፋ የተደረገው ለውጥ የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘመንና አሠራሩን ከዓለም ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮዎች ጋር በማጣጣም ረገድ ፋይዳ ያለው ታሪካዊ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህም የባንኩን ፖሊሲ- ነክ የወለድ መጣኔ መወሰን፣ ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታ መጀመር፣ የአንድ ቀን የብድርና የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት ተግባራዊ ማድረግና የባንክ ለባንክ የገበያ ሥርዓት ማዘጋጀት ብሔራዊ ባንኩ በስትራቴጂአዊ ዕቅዱና በባንኩ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የተሰጡትን ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት እጅግ አስፈላጊ እርምጃዎች መሆናቸውም ተብራርቷል፡፡

More stories

ትራምፕ በፊሽካ ያስጀመሩት የታሪፍ ጦርነት

February 4, 2025

“የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ባንኮች በፋይናንስ ዘርፉ እንዲሠማሩ የወጣውን ፖሊሲ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር ነው”

November 13, 2024

“ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ደሞዝ 300 እጥፍ ያድጋል”

August 2, 2024

ፓርላማው ለ2018 በጀት ዓመት የ1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት አጸደቀ

July 3, 2025

የብሔራዊ ባንክ ስለጉዳዩ የሰጠው ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በዋናነት ዝቀተኛና የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ መኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ለመዘርጋት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህም ከባንኩ የመካከለኛ ዘመን ስትራቴጂአዊ ዕቅዶች መካከል ቀዳሚው ሲሆን ፥ ይህንኑ ለማሳካት ባንኩ ሰፊ ሕጋዊ፣ ተቋማዊና ቴክኒካዊ ዝግጅቶችን አድርጓል፡፡ በተለይም የባንኩ ቀዳሚ ዓላማ ዋጋን ማረጋጋት እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ከዘመናዊ የማዕከላዊ ባንክ አሠራርና ከፈጣን በገበያ ላይ ከተመሠረተ የፋይናንስ ሥርዓት ጋር የተጣጣሙ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎችን ለመተግበር የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የዝግጅት ሥራዎች በአብዛኛው የተጠናቀቁ በመሆናቸው ብሔራዊ ባንኩ በዛሬው ዕለት አዲሱን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ የሚከተሉትን እርምጃዎች ይፋ አድርጓል፡

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ በወለድ ተመን ላይ ወደ ተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይሸጋገራል፡፡ በአዲሱ የገንዘብ የፖሊሲ ማዕቀፍ መሠረት ባንኩ በዋናነት የገንዘብ ፖሊሲ አቋሙን ለማሳየትና አጠቃላይ የገንዘብና የብድር ሁኔታዎችን ለመወሰን የሚረዳ የብሔራዊ ባንክ ፖሊሲ-ነክ የወለድ መጣኔ (National Bank Rate) የሚባለውን የፖሊሲ ተመን (Policy Rate) ይጠቀማል፡፡ ይህ የማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጣኔ እንደ የዋጋ ንረትና የገንዘብ ሁኔታ እየታየ ከፍ ወይም ዝቅ የሚል ይሆናል፡፡

ሁለተኛ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኩ ፖሊሲ-ነክ የወለድ መጣኔ ለመጀመሪያ ጊዜ 15 በመቶ ይሆናል፡፡ ይህ የወለድ መጣኔ በአሁኑ ወቅት የሚታዩ ማክሮ ኢኮኖሚአዊ ሁኔታዎችን ማለትም፣እየቀነሰ ያለውን፣ነገር ግን አሁንም ከፍ ብሎ የሚታየውን የዋጋ ንረት፣ ዝቅተኛ የመሠረታዊ ገንዘብ ዕድገትና ካለፉት ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየወረደ የመጣውን የባንክ ብድር ዕድገት ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ ይህ የብሔራዊ ባንክ ፖሊሲ-ነክ የወለድ መጣኔ ባሁኑ ጊዜ ባንኮች እርስ በርስ በሚበዳደሩት ብድር ላይ ከሚከፍሉት ወለድ ጋር የተቀራረበ ነገር ግን ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጧቸው ብድሮች ላይ ከሚያስከፍሉት ከ16-20 በመቶ ከሚደርስ ወለድ ያነሰ ነው፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር፣ይህ የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጣኔ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት ብድር ላይ የሚያስከፍሉትን የወለድ ተመን የሚመለከት አለመሆኑን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ባንኮች በውድድር ላይ ተመሥርተው ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት ብድር ላይ የሚያስከፍሉትን የወለድ መጠን በራሳቸው መወሰናቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንዲሁም ባሁኑ ጊዜ ባንኮች በቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፍሉት ዝቅተኛው የ7 በመቶ ወለድ በዚህ በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን ምክንያት ለውጥ አይደረግበትም፡፡

ሶስተኛ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገንዘብ ፖሊሲ ጋር የተያያዙ ጨረታዎችን በየሁለት ሳምንቱ ያካሂዳል፡፡ እነዚህ ጨረታዎች የሚደረጉት ብሔራዊ ባንኩ ከወቅታዊ ሁኔታዎች በመነሣት ከባንክ ሥርዓቱ ውስጥ ትርፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ወይም ተጨማሪ ገንዘብ ለመልቀቅ እንዲያስችለው ነው፡፡ እነዚህ ብሔራዊ ባንክ ከባንኮች ጋር የሚያደርጋቸው ጨረታዎች በዋናነት የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ-ነክ የወለድ መጣኔ እምብዛም የተራራቀ አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ በባንክ ሥርዓት ውስጥ ያላግባብ የተከማቸ የገንዘብ መጠን መኖር የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ ተመኑን ከማዕከላዊ ባንኩ ፖሊሲ- ነክ የወለድ መጣኔ በእጅጉ እንዲቀንስ የሚያደርግ ከሆነ፣ ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ሥርዓቱ ትርፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከባንኮች ጋር የሚገበያይበትን ጨረታ ያካሂዳል፡፡
በአንጻሩ ፣ በአጠቃላይ የባንክ ሥርዓት ውስጥ የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥምና የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ ተመን ከፍ ያለ እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ተጨማሪ ገንዘብ ለማቅረብ ይህንኑ ጨረታ ይጠቀማል፡፡

አራተኛ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይሰጣል፡፡ እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ምክንያት ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ፍሰት አቋማቸውን ለማስተካከል እንዲረዳቸው ነው፡፡ እነዚህ ቋሚ አገልግሎቶች የሚሰጡት ከብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን 3 በመቶ በማስበለጥ ወይም በማሳነስ ይሆናል፡፡

አምስተኛ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርስ የሚበዳደሩበትን የተነቃቃ የገንዘብ ገበያ ለመመሥረት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በቅርቡ ለመዘርጋት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የገንዘብ ገበያው ኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ላይ ተመሥርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ሲውል ትርፍ ገንዘብ ያላቸው ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ፡፡ በመሆኑም፣ ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ወይም ትርፍ ገንዘብ ሲኖራቸው እርስ በርስ የመገበያየት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ አሠራር ሥራ ላይ ሲውል የባንክ ለባንክ የወለድ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ-ነከ የወለድ መጣኔ ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ብሔራዊ ባንኩ ሁኔታውን ለማስተካከል ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታን ይጠቀማል፡፡

ስድስተኛ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ቢሸጋገርም፣ በሽግግሩ ወቅት ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቀጥታ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች በጊዜያዊነት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በሌላ አነጋገር፣ አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማስተላለፊያ ዘዴዎች ከተጠበቀው በላይ ዝግ ያሉ ከሆኑ፣ ብሔራዊ ባንክ ነባሮቹን ቀጥተኛ የፖሊሲ መሣሪያዎች በተጨማሪነት ይጠቀምባቸዋል፡፡ ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደፊት አቅጣጫ ይሰጥበታል፡፡

ማጠቃለያ

ዛሬ ይፋ የተደረገው ለውጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘመንና አሠራሩን ከዓለም ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮዎች ጋር በማጣጣም ረገድ ፋይዳ ያለው ታሪካዊ እርምጃ ነው፡፡

የባንኩን ፖሊሲ- ነክ የወለድ መጣኔ መወሰን፣ ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታ መጀመር፣ የአንድ ቀን የብድርና የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት ተግባራዊ ማድረግና የባንክ ለባንክ የገበያ ሥርዓት ማዘጋጀት ብሔራዊ ባንኩ በስትራቴጂአዊ ዕቅዱና በባንኩ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የተሰጡትን ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት እጅግ አስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉ ለውጦች በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚና በባንክ ዘርፍ የሚታዩ አንዳንድ ሥር የሰደዱ ድክመቶችን ለማስወገድ እንደሚረዱ ብሔራዊ ባንኩ በጽኑ ያምናል፡፡

ስለሆነም፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ ለአዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ተግባራዊነትና ውጤታማነት ያልተቆጠበ ትብብራቸውን እንዲለግሱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ ከ14 ዓመት የትዳር ጓደኛው ግማሽ ሚሊዮን ብር የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
ቀብድ እና ህጋዊ ውጤቱ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ECONOMY

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

March 29, 2026
ECONOMY

“የስምምነቶች ሁሉ እናት” ህንድ እና የአውሮፓ ህብረትታሪካዊ የንግድ ስምምነት አደረጉ

January 27, 2026
ECONOMY

በኢትዮያ ከ21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በርላይ የጋዝ ክምችት ተገኘ

October 30, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2