የፌዴራል ፖሊስ ” በሽብር እና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ” ብሎ በቁጥጥር ካዋላቸው መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፦
– በዘረፋ፣
– በቅሚያ፣
– በሌብነት፣
– በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበት ነበር።
ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም ፦
– 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣
-6 ቅምያ ወንጀል፣
– 3 ሌብነት ወንጀሎች፣
– 3 ሰው #መግደል ወንጀል፣
– 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣
– አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣
– ከእስር ማምለጥ ወንጀል
– አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች እንዳሉበት ፖሊስ አመልክቷል።
ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበት ነበር።
እንደገና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት በጦር መሣሪያ የታገዘ የዘረፋ፣ ከአስር ቤት የማምለጥና በሌብነት ወንጀል የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጠት አስተላልፎበት ነበር።
ተጠርጣሪው በውሳኔው መሠረት ማረሚያ ቤት የገባው ይግባኝ ጠይቆ ሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረለት ቢሆንም በድጋሚ ይግባኝ በማለቱ ቅጣቱ ወደ 25 ዓመት ተቀንሶለት ለ17 ዓመታት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ #በይቅርታ መፈታቱን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለ ተገልጿል።
EthiopianFederalPolice

