Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  SOCIETY  በመጨረሻም እስራኤላዊያን “ጦርነት በቃን”
SOCIETY

በመጨረሻም እስራኤላዊያን “ጦርነት በቃን”

Ethioreview newsEthioreview news—September 2, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail



የሃማስና የእስራኤል ጦርነት ከ11 ወራት በፊት ከጀመረ ወዲህ በእስራኤል ውስጥ ከታዩት ትልቁ የተባለለት ተቃውሞ  ትላንት እሁድ ምሽት ተጀምሯል።

በጋዛ ስድስት እስራኤላውያን ምርኮኞች በሀማስ  መገደላቸውን ተከትሎ  የእስራኤል የሰራተኞች ህብረት የስራ ማቆም አድማ ጠርቶ ነው በሺዎች  የሚቆጠሩ ዜጎች ጎዳና በመውጣት ተቃውሟቸውን ማሰማት የጀመሩት።

ወደ አደባባይ የወጡት እስራኤላውያን በመጨረሻም “ጦርነት በቃን የተኩስ አቁም ስምምነትን ይደረግ” የሚል ጥያቄንም አንስተዋል።

በዚህ ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ዜጎች በምዕራብ እየሩሳሌም በሚገኘው የኔታኒያሁ ቢሮ አጠገብ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ የሚገኙ ምርኮኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ አሁኑኑ ከፍልስጤሙ  ቡድን ሃማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።



በታቃውሞው ላይ በጋዛ የታሰሩትን ቤተሰቦች የሚወክለው የታጋቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች ፎረም የስድስቱ ታጋቾች ሞት  የተከሰተው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኒታኒያሁ ጦርነቱን ለማስቆም ታጋቾችን ለማስፈታት  ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው  የመጣ ነው በማለት ኮንነውታል።

ለ11 ወራት በሀማስ ተይዘው የነበሩና አሁን ሕይወታቸው ማለፉ የተሰማው ስድስት ምርኮኞች ሲሆኑ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው በፍልስጤም ግዛት ውስጥ የታሰሩት ሰዎች ቁጥር 101 መሆኑንና 35 ሰዎች ሞተዋል ተብሎ ይታመናል።

በስራኤል እና ሃማስ መካከል ያለው ጦርነት በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 7 ቀን ከተጀመረ ወዲህ በእስራኤል የጦርነት ይብቃ ጥያቄዎች እንዲህ በሰፊው ሲሰማ የመጀመሪያው ሆኗል።

ሆስፒታሎች ፣  የጤና አጠባበቅ ማእከሎች፣ ድንገተኛ አደጋ  ሰጪ ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ሲቀሩ ሌሎች ሰራተኞች የተሳተፉበት የተባለው ሀገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ በመንግስት ላይ ጫና ማድረግ ካልቻልን ሌሎች ታጋቾችንም በህይወት አናገኛቸውም በሚል እየተካሄደ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ማቆም አድማውን የተቀላቀሉ ሰራተኞች በአሰሪዎች በኩል ደሞዝ እንዳይከፈላቸው አስታውቋል።

እስራኤል ከሃማስ ጋር ወደ ሰላም እንዳይመጡ ዋና ምክንያት ነው የተባለው የፊላዴልፊ ኮሪደር ሲሆን  14 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው አካባቢ ጋዛን ከግብፅ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ የሚገኝ እና አሁኑ የእስራኤል ጦር የሚቆጣጠረው ነው።

በመጀመሪያው የስምምነት ምዕራፍ እስራኤል የድንበር ዞኑን ለመቆጣጠር የጠየቀች ሲሆን ሃማስ ግን የእስራኤል ወታደሮች መውጣት አለባቸው ብሏል።

ቤኒያሚን ኔታንያሁ ሃማስ ከሥሩ ባሉ ዋሻዎች የሚያደርገውን የጦር መሳሪያ ዝውውር እንደገና እንዳይጀምር ኮሪደሩን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ነው የሚያምኑት ተብሏል።

በዚህ አለመግባባት ውስጥ ታዲያ ታጋቾችን ለመልቀቅ የነበረው ተስፋ እየጨለም ነው የሚሉ ቤተሰቦች እና አሁን ላይ ደግሞ ብዙዎች የተቀላቀሉት የህዝብ ጥያቄ የሆነው።

አሜሪካ፣ ኳታር እና ግብፅ ስምምነቱን ለመፍጠርና ለማደራደር ወራትን ያሳለፉ ሲሆን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኔታንያሁ በፊላዴልፊ ኮሪደር ላይ የበለጠ ተለዋዋጭ እንዲሆኑ ግፊት ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

ዛሬ ላይ ሰላም ይውረድ ብለው በቴልአቪቭ ጎዳናዎች የወጡት እስራኤላውያን በጥቅምት 7 ታግተው ለሞቱት ዜጎች ሃማስን ተጠያቂ ቢያደርጉም፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለችግሩ አለመፈታት ተጠያቂ ናቸው ብለዋል።

የሆነው ሆኖ እስራኤላውያን ሰላምን ፈልገው አደባባይ መውጣታቸው ፍሬ አፍርቶ የንጹሃን ሞት ማብቂያው ይሆን ዘንድ የብዙዎች ምኞትም ጻሎትም ነው።

ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት በትንሹ 40 ሺህ 738  ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 94 ሺህ 154 ቆስለዋል ነው የተባለው።

በእስራኤል በበኩል ደግሞ 1 ሺህ 139 ሰዎች ሲገደሉ 250 ሰዎች በሃማስ መታገታቸውን ቢቢሲና ሲኤንኤን ዘግበዋል።

በናርዶስ አዳነ ኢፕድ

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል ይፋ አደረገ
“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2