Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  የአጋች ታጋች ድራማ በባህርዳር፤ ታዳሚዎች ሙሽሮችን ይጠብቃሉ፣ አጋቾች ሙሽሮችን አንቀው 3 ሚሊዮን!!
TIPS 1

የአጋች ታጋች ድራማ በባህርዳር፤ ታዳሚዎች ሙሽሮችን ይጠብቃሉ፣ አጋቾች ሙሽሮችን አንቀው 3 ሚሊዮን!!

Ethioreview newsEthioreview news—September 30, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በቅርቡ በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የተፈጸመው የእገታ ወንጀል ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ሁለት ወጣቶች ሠርጋችሁን የአብረሃም እና የሣራ ያድርግላችሁ ሊባሉ አንድ ቀን ብቻ ቀርቷቸዋል፡፡ በማግሥቱ ለሠርጉ የተጠራው እድምተኛ ወደ ሠርጉ ቤት ሲመጣ ግን ያጋጠመው ያልተጠበቀ ነገር ነው፡፡ ለሠርጉ በተጣለው ድንኳን ውስጥ አናስገባም ሠርገኛ ከሚለው ዘፈን ይልቅ ሀዘንተኞች ተቀምጠውበታል፡፡

አጋቾች ሙሽሮችን አግተው ሦስት ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው የሙሽሮችን ቤተሰብ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅ ገምቱት፤ ለሦስት ጉልቻ በቁልኝ የተባሉት ወጣቶች ሦስት ሚሊዮን ብር የተጠየቀባቸው መከራ አምጪዎች መኾናቸውንም አስቡት። አንድ አነስተኛ ክሊኒክ ከፍቶ የሚሠራን ባለሙያ ሦስት ሚሊዮን ካላመጣህ ሙሽራ ልጅህን በሕይወት አታገኛትም ሲባል ምን ሊሰማው እንደሚችል ራሳችንን በሱ ቦታ አድርገን እናስበው፡፡

ከላይ ያነሳነውን የእገታ ወንጀል ለአብነት አነሳነው እንጂ በአማራ ክልል ውስጥ ከዚህም የከፉ የእገታ ወንጀሎች በስፋት እየተፈጸሙ ነው፡፡

ከሕጻናት እስከ አዛውንት፣ ከሙሽሮች እስከ ባለትዳሮች፣ እናቶች እስከ ልጆች እየታገቱ ገንዘብ ተጠይቆባቸዋል፡፡ ለታጋቾች ገንዘብ መክፈል የቻሉትም ኾኑ ያልቻሉት ታጋቾቻቸውን በሞት ተነጥቀዋል፡፡ የስቃይ እንባንም አንብተዋል፡፡

የእገታ ወንጀሉ በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያልቅ ወንጀል ከኾነም ሰነባብቷል፡፡ ተዋናዮቹም የጭካኔን ጥግ በማሳየት ወደር የለሽ ወንጀሎኞች ኾነዋል፡፡

ማኅበረሰቡ በጉያው ያቀፋቸውን አጋቾች መቼ ለሕግ እንደሚያቀርባቸው መገመት አይቻልም፡፡ “ነግ በእኔ” ይሉትን የአበው ብሂል ከዘነጋነውም ሰነባብተናል፡፡

አጋቾች በጠራራ ፀሐይ ሰው እያገቱ ለሻንጣ የሚከብድ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡ የታጋች ቤተሰቦች ለአጋቾቹ የሚኾን ገንዘብ ወደ አደባባይ ወጥተው ይለምናሉ፡፡ የኑሮ ውድነት ወገቡን ያጎበጠው የዋህ ማኅበረሰብም ከጉሮሮው ነጥቆ ለአጋች ጉሮሮ ጀባ ይላል፡፡
ይሄ የሚቀጥለው እስከመቼ ነው?

አንድ ሰው ታገተ ሲባል ይደነግጥ የነበረው ውስጣችን የብዙዎችን እገታ ተለማምዶታል፡፡ ከመጋረጃ ጀርባ የነበረው የእገታ ወንጀልም የአደባባይ ሥራ ኾኗል፡፡

አሁንም ጥያቄው በዚህ መልኩ የምንቀጥለው እስከ መቼ ነው? የሚለው ነው፡፡ ሕግ ማስከበር የመንግሥት ተቀዳሚ ኀላፊነት ቢኾንም ሕግ የተላለፉ ሰዎችን በጉያችን መደበቁ ግን የኛ ስህተት መኾኑን ማመን ይኖርብናል፡፡


በእርግጥ የአደባባይ ዘረፋዎች እና በጠራራ ፀሐይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ስንመለከት ሕጉ እና ሕግ አስከባሪዎቹስ  ወዴት አሉ? ማለታችን ስህተት አይኾንም፡፡

”ሕጋችንም ታግቶ ይኾን እንዴ“ ብለን ብንጠይቅም ስህተት የማይኾነው ሁሉም ወንጀሎች የሚፈጸሙት የሕግ አካላት በቅርበት ባሉባቸው ትላልቅ ከተማዎች ውስጥ ጭምር ስለኾነ ነው፡፡

ባሕር ዳርን የእገታ ወንጀል መናኽሪያ እንድትኾን ስንፈቅድ፣ ውበቷ ጠርቷቸው ወደ እሷ የሚመጡትን ሰዎች እንዲፈሩ እያደረግን መኾኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ባሕር ዳርን ለአብነት አነሳን እንጂ ጎንደርም፣ ደብረ ማርቆስም፣ ደሴም፣ ደብረ ብርሃንም ኾኑ  ሌሎች የክልሉ ከተሞች ውስጥ ችግሩ ተመሳሳይ ነው፡፡

ባሕር ዳርን ወይም ሌሎችን የክልሉ ከተሞች የዝርፊያ እና የእገታ ጥላሸት ሲቀቧቸው እያየን ዝም ማለታችን ወይም ችግሩን ለሕግ አስከባሪዎች ብቻ የተውን ሰዎች ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ አሁን ነው፡፡

በክልሉ  በሁሉም አከባቢዎች የሚደረጉ እገታዎችን ማውገዝ ያለብን በጋራ ነው፡፡ የሕግ አካላት ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲፈጽሙ እየወተወትን እኛም ግን ጥላሸት እየተቀባ ላለው እሴታችን ዘብ መቆም ይገባናል፡፡

አጋቾች በክልሉ ውስጥ ያለውን የሰላም መደፍረስ ሳይቆርጡት የደረሳቸው ሎተሪ አድርገው ሲዘርፉን እና ሲያግቱን ዝም ማለታችን በጣም ስህተት ነው፡፡ ስንዘረፍም ኾነ ስንታገት የፀጥታ አካላት አልደረሱልንም የሚል ሰበብ መደርደሩ መፍትሔ አያመጣልንም፤ ይልቁንም በጋራ ቆመን ችግር ፈጣሪዎችን ልንታገላቸው ይገባል፡፡

አሚኮ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ማኀበራዊ ሚዲያ በተማሪዎች ውጤት ተጽኖ ይኖረው ይኾን?
“ኢትዮጵያን ጠብቋት፤ ለክብሯም ቁሙላት”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2