Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News2  ሰንደቅ ዓላማ – የሉዓላዊነታችንና የነጻነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ እሴት
News2

ሰንደቅ ዓላማ – የሉዓላዊነታችንና የነጻነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ እሴት

Ethioreview newsEthioreview news—October 15, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ኢትዮጵያ ብዙ ሆና አንድ፣ አንድ ሆና ደግሞ ብዙ ነች፤ የዚህ መገለጫው ደግሞ ሰንደቅ ዓላማችን ነው” – ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከበረው 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ እንዳሉት ሰንደቅ ዓለማ የብሔራዊ አንድነታችን እና ሕብረታችን ማሳያ፣ የዜጎች ሀገራዊ ፍቅር እና ብሔራዊ ስሜት መገለጫ፣ ታሪካዊ ማኅበራዊ ትስስራችን እና የሥነ-ልቦናዊ አንድነታችን የሚንፀባረቅበት ምልክት ነው፡፡

ሰንቅ ዓለማ የመስዋዕትነት፣ የነጻነት፣ የሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ዓርማ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ የአንድነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የነጻነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ እሴት፣ የአብሮነታችን፣ ዓርማ ምልክትም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ደምና አጥንታቸውን አፍስሰው፣ ውድ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለው፣ በክብር አስጠብቀው፣ በክብር ያስረከቡን በልባችን ታትሞ የቆየ የአሸናፊነትና የነጻነት ዓርማችን ነው ብለዋል፡፡

More stories

ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

November 20, 2024

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ

March 4, 2025

አጋቹ ተያዘ

March 6, 2023

በይነመረብ ማህበርዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት!!

November 29, 2022

ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዓመታት ነጻነቷን እና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ታፍራ እና ተከብራ የቆየች ታላቅ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗንም አውስተዋል፡፡

በመንግሥታዊ አስተዳደር ሥርዓትም ቢሆን በጣም ረጅም ዓመታት ካስቆጠሩት ቀዳሚ ሀገራት ተርታ የምትጠቀስ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታየ፣ የሰንደቅ ዓላማ ታሪኳም ከሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ጋር በእጅጉ የተቆራኘና የተሳሰረ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሀገራዊ ነጻነታችንና ሉዓላዊነታችንን ለመንጠቅ በየዘመናቱ በተደጋጋሚ የመጡ የውጭ ወራሪ ኃይሎችን እናት አባቶቻችን በተባበረ ክንድ በአንድነት ቆመው መክተውና አሳፍረው የመለሱት ለሀገራቸው እና መለያቸው ለሆነው ሰንደቅ ዓላማ ከሚሰጡት ክብር እንደሆነ አስታውሰው፣ ይህም ከፍቅር እና ብሔራዊ ስሜት በመነሳት እንደሆነ ሁላችንም ከቀደምት ታሪካችን የምንረዳው ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህም የሀገራችን ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን እስከ ዛሬም ጸንቶ የቆየው ኢትዮጵያውያን በአንድነት በከፈሉት መስዋዕትነት እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በኛ በኢትዮጵያውያን ብቻ ታትሞ የቆየ ብሔራዊ መለያችን ብቻም ሳይሆን በአፍሪካውያን እና በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የነጻነትና የእኩልነት ንቅናቄ ዓርማ ምልክት ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም በርካታ አፍሪካውያን ሀገራት፣ አንዳንድ የካሪቢያን ሀገራት እና ንቅናቄዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላመ ቀለማት ለሰንደቅ ዓላማቸው ሊጠቀሙበት ችለዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማንኛም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር ሊሰጥና እንደ ብሔራዊ በዓል ሊያከብረው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማን ቀን ትርጉም ባለው መልኩ ማክበር ለብሐሔራዊ መግባባት፣ ለአብሮነታችን፣ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት መጽናት እጅግ አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

አክለውም፣ “ኢትዮጵያ ብዙ ሆና አንድ፣ እንድ ሆና ደግሞ ብዙ ነች፤ የዚህ መገለጫ ደግሞ ሰንደቅ ዓላማችን ነው፤ እንደ ሀገር ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እንዲሁም የኢትዮጵያን ከፍታ አስተማማኝ መሰረት ላይ ለማኖር የምንችለው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ በማድረግ በተሰማራንበት ሥራ ሁሉ ጠንክረን በመሥራት ነው” ብለዋል፡፡

ከትላንት እስከ ዛሬ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በደማቸው ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን አስጠብቀው ያኖሯትን ሀገር እኛ ዛሬ በዕውቀታችን፣ በጉልበታችን እና በላባችን በማልማት ያሉብንን የዘመናት እዳዎች ወደ ሀብት በመቀየር በታላቅ ተስፋና ነገን በማለም በአብሮነት ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ በማድረግ ለኢትዮጵያ ከፍታ ከመቼውም በበለጠ ለመሥራት መነሳት እንደሚኖርብንም ተናግረዋል፡፡

ሉዓላዊነታችን የተሟላ የሚሆነው ሀገራችንን ከልመና ነጻ ማውጣት ስንችል ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ፣ ይህ ትውልድ ያለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ተገንዝቦ በየተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ በዕውቀቱና በላቡ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ መረባረብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የዛሬው ትውልድ የራሱ የጋራ አሻራ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብን በአንድ ልብ፣ በአንድ ሀሳብ፣ በራሱ ዕውቀት፣ ጥረትና ላብ ገንብቶ በማጠናቀቅ ኃላፊነቱን እንደተወጣ ሁሉ በቀጣይነትም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ከፍተኛ ኃላፊነቱ ነውም ብለዋል፡፡

በዚህች በዛሬዋ ዕለት የሀገራችንን ህልውና ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉትን የመከላከያ፣ የፀጥታ እና ሌሎች ሠራተኞችን በማክበር በአንጻሩ ደግሞ ሀገራችንን ለማዳከም የሚሠሩና በከንቱ ምኞቶቻቸው ሀገራችንን የሚያውኩትን ኋላ ቀር ምኞቶቻቸውን በማምከን ለሰንደቅ ዓላማችን ክብር በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

በለሚ ታደሰ

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን እውነታዎች
መንግስት ካቀረርበው ከ285.5 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ደንበኞች 79 ሚሊዮን ብቻ ተጠቀሙ፣ ዶላር ከፈተኛ ቅናሽ አሳየ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2