Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን እውነታዎች
POLITICS

ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን እውነታዎች

Ethioreview newsEthioreview news—October 15, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሰንደቅ ዓለማ የሉዓላዊ ሀገር መለያ አርማ እና የህዝቦች ማንነት መገለጫ ነው፡፡ የህዝቦች ታሪክና አንድነት መገለጫ እና የሀገር ምልክትም ነው፡፡ ሰንደቅ ዓለማ የሰላም፣ የድል አድራጊነት እና የስኬት መገለጫ ተደርጎ ከፍ ብሎ ይውለበለባል፡፡ ሀገራት ካላቸው ሀገራዊ ታሪክና ዳራ ጋር አያይዘው ለሰንደቅ ዓለማቸው ያላቸውን ፍቅር እና ክብር በማሳየት ያከብሩታል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ጥንታዊ እና ነጻ ሀገራት የድል ቀናቸውን፣ በቅኝ ግዛት የተያዙት ሀገራት ደግሞ ከቅኝ ግዛትነት ነጻ የወጡበትን ቀን፣ በተለያዩ ምክንያት ዘግይተው ሀገር የሆኑት ደግሞ ነጻና ሉዓላዊ መንግሥት የመሰረቱበት ቀን ለማስታወስ የሰንደቅ ዓለማ ቀን ያከብሩታል፡፡

በዓለማችን 52 ሀገራት የሰንደቅ ዓለማ ቀንን ያከብራሉ፡፡ ኢትዮጵያም በራሷ መንገድ የሰንደቅ ዓለማን ቀንን ሀገራዊ መልክና ይዘት ያላቸው መልእክቶችን ቀርጻ በደማቅ ሁነቶች ታከብራለች፡፡ በዓሉ ጥቅምት በገባ በመጀመሪው ሳምንት ሰኞ ይከበራል፡፡ ኢትዮጵያ ላለፉት 16 ዓመታትም የሰንደቅ ዓለማ ቀንን በተለያዩ መሪ ቃሎች ስታከብር ቆይታለች፡፡ በዓሉ በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ በፌዴራል ደረጃ፣ በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በሁሉም የፌዴራልና ክልል ተቋማት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ይከበራል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት 16 ዓመታት ቀኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ ስታከብር ምን ዓይነት መልእክቶችን ተጠቅማ ነበር? ባለፉት 16 ዓመታት የሰንቅ ዓላማ ቀናት አከባበሮች በሰንደቅ ዓለማው መርሆች እና ለብዘኃነታቸው ባላቸው ትርጉም ዙሪያ ግልጽነት ለመፍጠር፣ ዜጎች በሰንደቅ ዓለማው ትርጎሜ እና ቅርጽ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ለማድረግ፣ የተዛቡ እና አሉታዊ አስተሳሰቦችን ለማቃናት ለማረም የሚያስችሉ መልዕክቶች ተላልፈውባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ አረንጎዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማት ያሉት ሲሆን መሃሉ ላይ ሰማያዊ  ኮከብ መደብ ብሔራዊ አርማ ያለው ሰንደቅ ዓለማችን  ልምላሜያችንን፣ ተስፋችን እና ለሀገር ሉዓላዊነት የሚከፈል መስዋእትነት ያንጸባርቃል፡፡

በኢትዮጵያ እስከ አሁን የተከበሩ የሰንደቅ ዓለማ ቀኖችን አስመልክቶ የተንጸባረቁ መሪ ሀሳቦችን በከፊል እናስታውስ፡-  

• 7ተኛው “በህዝቦቹዋ ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሄራዊ ክብራችንና ሰንደቅዓለማችንን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር ኢትዮጵያ!”

• 10ኛው “ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል!” 

• 11ኛው “ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን!”

• 12ኛው “ሰንደቅ ዓለማችን የብዙሃን ድምር ውጤት፣ የአንድነታችን ምሶሶ ነው!” 

• 13ተኛ “ሰንደቅ ዓለማችን ፣ለሰላማችን፣ ለአንድነታችን፣ ለሀገራዊ ብልጽግናችን!”

• 14ኛ “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓለማ ከፍታ!”

• 15ኛ “ሰንደቅ ዓላማችን የብዘሃነታችንና የሉዓላዊነታችን ምሶሶ ነው!” 

• 16ኛ “የሰንደቅ ዓለማችን ከፍታ ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!”

• 17ኛ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”

በመሃመድ ፊጣሞ

አስገራሚ እውነታዎች -ስለ ሰንደቅ ዓላማ



ለመጀመሪያ ጊዜ የሰንደቅ ዓላማ ሃሳብ እንዴት እንደመጣ እርግጠኛ የሆነ መረጃ ባይኖርም፣ በተደረጉ ጥናቶች  እጅግ ጥንታዊው ሰንደቅ ዓላማ መሰል በኢራን  ሻህዳ ከተማ የተገኘው የነሐስ ሰንደቅ ዓላማ ነው። 

ይህም በ2400 ዓመተ ዓለም እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ፤ ሌሎች የሰንደቅ ዓላማ እውነታዎች እንደሚከተሉት እነሆ፡-

• ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት በመላቀቅ ነፃነታቸውን ሲቀዳጁ፣ የኢትዮጵያን የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የነጻነት ምልክት በማድረግ በሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ውስጥ በማካተት ያዋሉ ሲሆን፣ ይህም “የፓን አፍሪካን ቀለሞች” በመባል እንዲታወቅ አድርጎታል።

• “ቬክሲልኦሎጂ” ስለ ሰንደቅ ዓላማ  የሚያጠና መስክ ሲሆን ቃሉ በላቲን ሰንደቅ ዓላማ  ወይም ባነር የሚል ትርጓሜን ይዟል፡፡

• ኔፓል የዓለማችን ብቸኛዋ አራት ማዕዘን ያልሆነ ሰንደቅ ዓላማ  ባለቤት ሀገር ናት፤ሰንደቅ ዓላማዋ የሦስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን የሂማላያስ ተራራን እና የሀገሪቱን ሁለት ኃይማኖቶች የሚያመለክት ነው፡፡

• የዴንማርክ ሰንደቅ ዓላማ  የዓለማችን እድሜ  ጠገቡ ሰንደቅ ዓላማ  በመሆን ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን ከ1219 ጀምሮ በጥቅም ላይ እንደነበር ይገለፃል፡፡

• ቀይ ቀለም በብዙ ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ላይ የሚገኝ ሲሆን 78 በመቶ በሚሆን መጠን በዓለም ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ላይ ይገኛል፡፡

• ቱርክ፣ አልጄሪያ፣ ፓኪስታን እና እስራኤል በሰንደቅ ዓላማ ቸው የሚከተሉትን ኃይማኖት ምልክት ያዋሉ ሀገራት ናቸው፡፡ 

• የሮማኒያ ሰንደቅ ዓላማ  የዓለማችን ትልቁ ሰንደቅ ዓላማ  ሲሆን 349.4 ሜትር ርዝመት እና 227.8 ሜትር ስፋት አለው፤ ይህም  79 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ነው፡፡

• የኦሎምፒክ ሰንደቅ ዓላማ የዓለማችንን 5 አህጉር ያላቸውን አንድነት እና መስተጋብር በአምስቱ ቀለበቶች በኩል ያመላክታል፡፡እያንዳንዱ ቀለም ቢያንስ በአንድ የዓለም ሰንደቅ ዓላማ ላይ ይታያል።

• ሰንደቅ ዓላማ  ሀገራትን ከመወከል ባሻገር በባሕር እንቅስቃሴ ወቅት መርከበኞች የሚግባቡበት ነው፤ ይህም መርከቡ ያለበትን ሁኔታ ለማመላከት ይረዳል፡፡

• በጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስትሮናትስ ኔሊ አርመስትሮንግ እ.ኤ.አ በ1969 የተቀመጠው ሰንደቅ ዓላማ “ኦልድ ግሎሪ” የተሰኘው የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ  ነው፡፡

• የሞዛምፒክ ሰንደቅ ዓላማ  ባለው የተለየ ዲዛይን እና የጦር መሳሪያ ምስል  ከሌሎች ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ  የተለየ ነው፡፡

• ሲዊዘር ላንድ እና ቫቲካን ሲቲ የስኩዌር ቅርፅ ያለው ሰንደቅ ዓላማን የሚጠቀሙ የዓለም ብቸኛ ሀገራት ናቸው፡፡

በአፎሚያ ክበበው ETV

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ፐርፐዝ ብላክ – ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ 10 ግለሰቦች በማታለል ሙስና ወንጀል ተከሰሱ
ሰንደቅ ዓላማ – የሉዓላዊነታችንና የነጻነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ እሴት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2