Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የተዛበቱ ዝምታን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰራዊት እንድታዋጣ የሶማሊያ መንግስት ወሰነ
News

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የተዛበቱ ዝምታን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰራዊት እንድታዋጣ የሶማሊያ መንግስት ወሰነ

Ethioreview newsEthioreview news—January 2, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ሚዲያዎች፣ ስለ ኢትዮጵያ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲዘግቡ በውጭ አገራት በተቋቋሙ ሚዲያዎች የሚሰሩ አብዛኞቹ በሰበርና፣ በደማቅ ዜና “ኢትዮጵያ ከአውሶም ተሰናበተች። በጃንዋሪ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ለቆ ይወጣል” ደጋግመው ሲዘግቡ ነበር። ዝምታን የመረጡት የኢትዮጵያ መሪዎች ከአንካራው ስምምንት በሁዋላ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ጩኸት መና አድርገውት ኢትዮጵያ በሶማሊያ ጦር እንድታዋጣ ስምምነት መደረሱ ተሰምቷል። “ተባረረች” ሲሉ ሰበር ዜና ያከታተሉ ግን ዜናውን ዝም ብለው አልፈውታል።

ብሉምበርግ “በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ውዝግብ በአንካራ ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአውሶም ለማካተት እያሰበች ነው” ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ወደ ሶማሊያ አቅንተው ሞቃዲሾ መድረሳቸውን ይፋ ሲያደርግ ነው።

ዴይሊይ ሶማሊያ ከብሉምበርግም ሆነ ሮይተርስ ቀድም ዜናውን ኢትዮጵያ በ AUSSOM ተልዕኮ ሰራዊት እንድታዋጣ የሶማሊያ መንግስት እንደወሰነ ይፋ አድርጓል።

የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ በ AUSSOM ተልዕኮ ሰራዊት እንድታዋጣ የወሰነ ሲሆን የምታዋጣው የሰራዊት ቁጥር የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ቀጣይ January 10, 2024 በአካል ተገናኝተው በስምምነት የሚቋጩት እንደሚሆን ይጠበቃል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ዛሬ ይፋ እንደሆነው የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድ የመሩት ልዑክ ወደ ሶማሊያ ያቀኑት ከአቻቸው ጋርና ከሚመለከታቸው ጋር ለመምከር ነው።

ብሉምበርግ ጉዳዩን አስመልክቶ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታን ጠቅሶ ይህንኑ አረጋግጧል። ሚኒስትሯ ወደ ሶማሊያ ያቀኑት የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) የሚኖራቸውን ተሳትፎ አስመልክቶ ይወያያሉ። ብሉምበርግ አያይዞ “በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ውዝግብ በአንካራ ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአውሶም ለማካተት እያሰበች ነው” ሲሉ ሚኒስትሩ መናገራቸውን አስታውቋል።

ብሉምበርግ እርግጠኛ ሆኖ ኢትዮጵያ ጦር እንደምታሰማራና ሶማሊያ አቋሟን መቀየሯን በሰፊ ዘገባው ገልጿል። ይህ ከመሆኑ በፊት አማራጭ ያጡት የግብጽ ፕሬዚዳንት አልሲሲ የሶማሌያና ኢትዮጵያን ስምምነት አድናቂ አፈጻጸሙን በአጽንዎ የሚከታተሉና ስምምነቱ ቀጣናውን ስለማ እንደሚያደርግ ጠቅሰው መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የሶማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ፊቂ “በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አለመግባባት ተፈትቷል” ማለታቸውን ቢቢሲ ሶማሊኛን ጠቅሶ አማርኛው ዘግቧል።

ዘገባው አክሎም “የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) የሚተካው የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ውስጥ የኢትዮጵያን ወታደሮች ማካተት እንደማትሻ ሶማሊያ የጠቆመች ሲሆን፣ ሁለቱ አገራት የሻከረ ግንኙነታቸውን በአንካራ ስምምንት ካደሱ በኋላ ውጥረቱ የረገበ ይመስላል።” ሲል የግምቱን ድምዳሜ አስፍሯል።

“አስቀድመን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሶማሊያም ሆነ ከአዲሱ ተልዕኮ ውጭ አይሆንም ብለን ሽንጣችንን ገትረን የተሟገትነው በመሪያችን የዲፕሎማሲ ጥበብና በሰራዊታችን ብቃት ስለምንተማመን ነው።” ሲል ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው “ጋት” በሚባለው የግል ሚዲያው በዜናው መደሰቱን ጠቅሶ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ካስገባችና ህይወት መክፈል ከጀመረች 17 ዓመታት ሆኗታል። በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ሶስት ሺህ የሚጠጋ፣ በሁለቱ አገራት ስምምነት ደግሞ አምስት ሺህ የሚልቅ ኃይል ማስፈሯ በተለያዩ ጊዜያት መገለጹ ይታወሳል። አንዳንዶች ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል።

የጦር ኃይሎች አዛዥ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሶማሊያን 60 ከበመቶ በላይ የኢትዮጵያ መከላከያ እንደሚጠብቅና፣ የሶማሊያ ህዝብ በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ሙሉ እምነት እንዳለው በመግለጽ ሶማሊያ ባትፈልግም ከብሄራዊ ጥቅምና ስጋት አንጻር ጦሩ ለቆ እንደማይወጣ ፍንጭ መስጠታቸው ይታወሳል።

ፊልድ ማርሻሉ ይህን ሲሉ በስም ጠርተው የተለያዩ ክልሎች የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲወጡ እንደማይፈልጉ፣ ይህንንም በገሃድ ማቅረባቸውን ጠቁመው ነበር። ከአንካራው ስምምነት በፊት ሶስቱ ትልልቅ ክልሎች ከሞቃዲሾ መንግስት ጋር በይፋ መለየታቸውን እስከማወጅ መድረሳቸውም አይዘነጋም።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የአንካራውን ስምምነት ከፈረሙ በሁዋላ ኤርትራ ሄደው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በቅርቡ መክረው ነበር። ሚኒስትሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያን ግብጽ ልከው የተለያዩ መግለጫዎች ሲሰጡ ነበር። ኤርትራና ግብጽም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ የምታደርገውን ጥረት እንደሚያወግዙና በይፋ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ከአንካራው ስምምነት በሁዋላ ” መንግስት ተሸነፈ፣ ኢትዮጵያ ተዋረደች” ወዘተ ሲሉ የነበሩ ይህን ዜና አልፈውታል። ቢቢሲ የመከላከያ ሚኒስትሯን ጉብኘት ተከትሎ ሶማሊያ አሳቧን መቀየሯን ድምዳሜ ላይ ደርሶ ዘግቧል።

የተመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ በሞቃዲሾ ቆይታው፦

  • በኢትዮጵያና በሶማሊያ መሪዎች በአንካራ የተፈረመው “የሁለቱን ሃገራት ብሄራዊ ጥቅም አስጠብቆ ችግሮችን በውይይትና በንግግር የመፍታት ሥምምነት – Ankara declaration” በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ሽኩቻ በማስወገድ ይልቁንም መከባበርና መተማመን ለማስፈኑ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን ያስገነዝባል፣
  • አትሚስን በተካው የአፍሪካ ሕብረት ባሰማራው አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማስፈንና ድጋፍ ተልዕኮ በሶማሊያ (AUSSOM) ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድርሻና ተልዕኮ ዙሪያ በጥልቀትና በስፋት በመወያየት ለሁለቱ ሃገራት መሪዎች ግብዓት ያዘጋጃል (የመጨረሻ ውሳኔ በቀጣይ January 10, 2025 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በ CAADP — Comprehensive Africa Agriculture Development Programme ስብሰባ ኡጋንዳ ላይ ሲገናኙ እንደሚወስኑ ይጠበቃል፣
  • በሁለቱ እህትማማች ሃገራት የደህንነትና መረጃ ልውውጥ (በዋነኝነትም ወታደራዊ መረጃ ዙሪያ)፣ በድንበር አካባቢ የሚከናዎኑ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርንና ኮንትሮባንድ ንግድን በመከላከል፣ የጋራ ወታደራዊ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አሕጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲመካከሩ ይጠበቃል። ሲል ጋት ሚዲያ አመልክቷል።

ይህ እስከተጻፈ ድረስ ከመንግስት ወገን ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ትግራይ – ወርቅ ለማውጣት ሲባል ያልተፈቀዱ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢሮው አሳሰበ!
ስምንት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን በይፋ ተቀላቀሉ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2