ግብጽን የምትከተለው ኤርትራ በኢትዮጵያ መንግስትና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በመጠቀም ኢትዮጵያ ላይ ፋላጎታቸውን ለመጫን አጋጣሚውን እየተጠቀሙበት ነበር። ከዛም አልፈው ወታደራዊ ስምምነት ሳይቀር መፈጸማቸው የሚዘነጋ አልነበረም።
የሁለቱን አገራት አለመግባባት የቱክርክ መንግስት ከዳኘ በሁዋላ ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከዚያም በመከላከያ ሚኒስትሮች አዲስ አበባና ሞቃዲሾ ቀጣይ ውይይቶች መደረገቻው የሚታወስ ነው። ፐረኢዚዳንቱም ሆነ ከጀርባ ሆነው የሚገፏቸው ግብጽና ኤርትራ በዲፕሎማሲ መሸነፋቸውን ያሳየው ይህ ጉብኘት ከመደረጉ በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በሶማሌ ሰላም አስከባሪነቱ እንዲቀጥል መወሰኑ በተለይ ለግብጽ ፖለቲካዊ ሞት ተደርጎ እንደሚወሰድ አስተያየት ሲሰጥ ነበር።

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፣ ከመንግስትና ፖለቲከአውን ከሚመሩ አካላት ጋር በማያያዝ ለግብጽ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ሲጮሑ የነበሩ የአገር ውስጥ ሚዲያዎችና “ኢትዮጵያዊ ነን” ባዮች፣ በጥቅል አፍ ያስያዘ የአንካራው ስምምነት የመሰረት ድንጋይ መተከሉ ተሰምቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሀሰን ሼክ መሃሙድ በአዲስ አበባ የተገኙት ከነዚህ ተከታታይ ውይይቶች በሁዋላ ነበር። ፕሬዚዳንቱ ባዲስ በቆይታቸው የተሳካ ምክክር ማድረጋቸውን አመልክተዋል። በዚህም የአንካራው ስምምነት በተባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር የሚሸጋገርበትን የማዕዘን ድንጋይ መትከላቸውን አስታውቀዋል።
ይህ የሁለቱ መሪዎች ውይይት የተደርገው ሃሰን ሼክ ካይሮና አስመራ ከተገኙ በሁዋላ መሆኑ ለኢትዮጵያ ታላቅ የዲፕሎማሲ ድል እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ከሁለኡም በላይ ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበት አግባብ በስምምነቱ መካተቱን አደራዳሪው የቱርክ ፐሬዚዳንት ይፋ ያደረጉ ከመሆኑ አንጻር ድሉ ታላቅ እንደሆነ እየተጠቆመ ነው።
ሁለቱ መሪዎች የጋራ ጥቅሞቻቸው በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የሁለቱ ሀገራትን ወንድማማች ህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን በጋራ ባወጡት የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል።
የአስመራው መንግስት የሶማሊያ ጉዳይ እንደሚያስጨንቀውና ግብጽን ጨምረው ወታደራዊ ስምምነት መፈጸሙን በሚያውጅበት ወቅት ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ አዲስ አበባ ሆነው የአንካራውን ስምምነት ለመተግበር መቁረጣቸውን ማስታወቃቸው በይፋ ባይገለጽም ቅሬታ ማስነሳቱ ተመልክቷል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ የነበራቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ውክልና ወደ ነበረበት ለመመለስና ለማጠናከር መስማማታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅርበት በትብብር ለመምራትና ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮቻቸውን ለመፈጸም ባለብዙ ወገን እና ቀጣናዊ ፎረም እንደሚያስፈልጋቸው በትኩረት መክረዋል።
መሪዎቹ ቀጣናዊ መረጋጋት ዕውን እንዲሆን ሁለቱ ሀገራት መተማመንና መከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልጋቸው አረጋግጠዋል።
ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባትን ለማሳደግ እና የጋራ ዕድገት እንዲመጣ የጋራ ጥረትን በማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚገባም ተግባብተዋል።
በሀገራቱ መካከል ያለውን የደህንነት ዘርፍ ትብብር ማስቀጠልና ማጠናከር እንደሚገባም መወያየታቸውን ያመለከተው የጋራ የአቋም መግለጫው፤ በቀጣናው የአክራሪ ታጣቂ ቡድኖችን ስጋት ለማስወገድ የሀገራቱ የጸጥታ አካላት ትብብራቸውን በማጠናከር ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን መስራት እንደሚገባቸው መሪዎቹ መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን በሁለቱ ሀገራት መካከል ማጠናከር ጠቀሜታ እንዳለው የመከሩ ሲሆን፤ ንግድን እና የጋራ ብልጽግናን ለማምጣት የመሰረተ ልማት ትስስርን ለማሳደግ ተስማምተዋል።
በመጨረሻም የአንካራ ስምምነትን በቁርጠኝነት በመፈጸም ወዳጅነትና ትብብርን ለማጠናከር የተስማሙ ሲሆን፤ በአንካራው ስምምነት መሰረት የተቀመጠውን የቴክኒክ ስምምነት ለመፈጸም መግባባት ላይ ደርሰዋል።
መግለጫው ይፋ ከሆነ በሁዋላ በቅርቡ ታድሶ በይፋ የተከፈተውን ብሄራዊ ቤተመንግስትና የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተው በክብር ተሸኝተዋል። ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ወደ ሀገራቸው ሲምለሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሸኝተዋቸዋል።

