Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  ሕዝብ የሰጣቸውን አንቱታ ጠብቀው፣ በብሄር ታርጋ አገራቸው ላይ ሳይማማሉ ያረፉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ መታወሻቸው ብዙ ነው
TIPS 1

ሕዝብ የሰጣቸውን አንቱታ ጠብቀው፣ በብሄር ታርጋ አገራቸው ላይ ሳይማማሉ ያረፉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ መታወሻቸው ብዙ ነው

Ethioreview newsEthioreview news—January 7, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail


“ከዚህ ምርጫ በኋላ ለአገሬ የምመኘው ሰላም፣ አንድነት እና ብልፅግና ነው፡፡ እኔም በ91 ዓመቴ በምርጫው የተሳተፍኩኝ ሲሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማስተላልፈው መልእክት የአገሪቱን ሰላምና አንድነት እንድትጠብቁ አደራ እላለሁ፡፡ አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት፡፡” 

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፉት መልእክት

አቶ ቡላቻ ደመቅሳ ህዝብ በግብራቸው የሰጣቸውን አክብሮት ሳያበላሹ ጠብቀው ያለፉ ጉምቱ ፖለቲከኛ ነበሩ። በፖለቲካ ህይወታቸው የሚያውቋቸው ብቻ ሳይሆን አገር በይፋ እንደሚያውቀው በብሄር ተሸፍነው “ፍለጠው፣ አስወጣው፣ አባረው …” ሲሉ ተሰምተው አያውቁም።

ካጃዋር መሐመድ ጋር መዋል ከጀመሩ በሁዋላ ” አማራ አታግቡ፣ ከአማራ ጋር አትገበያዩ …” ሲሉ እነነበሩት አንደበታቸውን አንድም ቀን ሳያረክሱ እንዳማረባቸው ያለፉት አቶ ቡልቻ፣ እድሜ ጠግበው ቢያልፉም ህዝብ ሃዘኑን የገለጸላቸው ሌሎችን ዘር ሳይለዩ የሚያከብሩ ጨዋ ሰው በመሆናቸው ነው።

አቶ ቡልቻ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በመሆናቸው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በኢትዮጵያ ላይ ሲያሴሩ፣ ሲመክሩባት፣ እንድትተራመስ ሲቀሰቅሱ ታይተውም ተሰምተውም አያውቁም። አንዳንዶች በሽምግልና ሳይቀር እዛና እዚህ እየረገጡ አገር ሲያተራምሱ እንደሚታዩት አይነት ክብረ ነክ ታሪክ የላቸውም።

More stories

ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር ?  ሰባት የፋኖ ቡድኖች ያሉበት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

July 22, 2024

በኦሮሚያ የሰላም ውይይት ፍንጭ ተሰማ፤ “ጃል መሮ እጅ ካልሰጡ ከጃል ሰኚና ከመንግስት አያመልጡም”

October 11, 2024

ኢምሬት ከፈረንሳይ ጋር ያሰረችውን የ 20 ቢሊዮን ጦር መሳሪያ ግዢ አቋረጠች

August 31, 2024

ኢትዮጵያ እንዲህ ተዘርፋለች፤ ” አሁንም ሌቦች አሉ የመንግስት ሌብነት ማለት ግን ይህ ነው”

July 7, 2024

የራሳቸውንም ይሁን የድርጅታቸውን ዓላማ ግልጽ በሆነ መድረክ የሚያራምዱ፣ በብሄር ጃኖ ተሸፍነው ህዝብ እንደሚያተራምሱት ዓይነት ምግባር የሌላቸው ጨዋ ሰው እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው በህይወት እያሉ ደጋግመው የመሰከሩላቸው ጥሩ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ነበሩ።

በብሄር ፖለቲካ እንደተጠለሉት አብዛኛ የደም ነጋዴዎች በአንድም ቦታ ስማቸው የማይነሳው አቶ ቡልቻ በስራ ገበታቸው፣ በተሰጣቸው ኃላፊነቶች፣ በፖለቲካ ድርጅት መሪነታቸው ስማቸው በክፉ ተነስቶ አያውቅም። ሌላው ቀርቶ ውድ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ሲያሳድኑ የነበሩት፣ እነ ነዲ ገመዳን የስለቀጡት አቶ መለስ እንኳን ከግርማቸው የተነሳ ያከብሯቸው ነበር።

ለዚህ ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልጹ “ሊተኩ የማይችሉ” ያሉዋቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ” ሲሉ በተባ ብዕራቸው ምስክርነት የሰጡዋቸው።

“እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲቀበል ተመኝተዋል። አቶ ቡልቻ የተወለዱት በ1922 ዓ.ም. ሲሆን የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መስራች እንደሆኑ ይታወሳል።

ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቦጂ ድረመጂ ወረዳ የተወለዱት አቶ ቡልቻ የቤተሰባቸው አራተኛ እና ብቸኛ ወንድ ናቸው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጊምቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በኩየራ አድቬንቲስት ተከታትለዋል።የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከያኔው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ አግኝተዋል።

ቢቢሲ ታሪካቸውን ሰብስቦ እንደሳፈው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የመንግስት ስራን የጀመሩት በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት የገንዘብ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር በመሆን ነበር።

አሜሪካ ሀገር በሚገኝ ሴርኪኡዝ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የተማሩት አቶ ቡልቻ ለአስር ዓመታት ያህል ምክትል ሚኒስትር ሆነው ካገለገሉ በኋላ በ1966 አብዮቱ ሲፈነዳ ተመልሰው ወደ ውጭ አገር ሂደዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የሰሩት አቶ ቡልቻ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ የፓርላማ አባል ነበሩ። በአንድ ወቅት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ “የኢትዮጵያን ፓርላማን ለማየት እንጅ የእዉነት ነው ብየ አይደለም የገባሁት” ብለዋል።

አቶ ቡልቻ ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪ ከቀዳሚ የግል ባንኮች አንዱ የሆነውን አዋሽ ባንክ አቋቁመዋል። አቶ ቡልቻ የባንኩ ዓላማ ለኦሮሞ አርሶ አደሮች ብድር ማመቻቻት እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ትውስታ … አቶ ቡልቻ በርካታ ትውሳታዎች ቢኖሯቸውም በብዛት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው፣ ቲክቫህን የመሳሰሉ የቴሌግራም ወሬ አቀባዮች የሚከተለውን ሰንደውላቸዋል።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?

በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።

ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።

በተለይ  ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።

በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።

” ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ‘ ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ‘ ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።

ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ‘ አስራ አንድ ነው ! ‘ እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? “

ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።

” መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ?  ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? “

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች  የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አብይ አሕመድ “በትንሹም በትልቁም ግጭት አያስፈልግም” ስላሉ ኦብነግ መግለጫ አወጣባቸው፤ የጎዴ መስኖ ዳግም ተወለደ
አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ የተከሰተባት ደቡብ ኮሪያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከስልጣናቸው ሊለቁ ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2