የነዚህ ተሸከርካሪዎች እና የነዳጁ ባለቤቶች በዚህ ወቅት የፈፀሙት ተግባር ግን የችግሩን ዋነኛ ባለቤት አሳይቷል
የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ነዳጅ ጭነው በየቦታው ተደብቀው የነበሩ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ቪድዮነዳጅ ጭነው ያለአግባባ በየቦታው ቆመው የሚገኙ የነዳጅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሳወቀ።
የአፋር ክልል ንግድ ቢሮን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጠየቀው ትብብር መሠረት ከክልሉ የፀጥታ አካል ጋር በመሆን በሰጠው ምላሽ ነው ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ ያለው።
አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ልዩ ቦታው ” ሰርዶ አድማስ ” በሚባል ቦታ በየጥሻው የቆሙት ቦቴዎች የፀጥታ አካል ባደረገው አሰሳ ተደብቀው በቆሙበት መያዛቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።
” በአሁን ሠዓት የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሸከርካሪዎቹ እጀባ በመስጠት ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ” ብሏክ።
” ‘ በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል ‘ በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተሸሸጉት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ያለአግባባ የሚያገኙትን ትርፍ ከማሰብ ውጪ የጫኑት ነዳጅ በባህሪው በትነት የሚባክን፣ አደጋን የማስከተል አቅም ያለው መሆኑን ለማሰብ አልፈቀዱም ” ሲል ኮንኗል።
” ከዚህ ባለፈ በየክልል ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን በማድረቅ እጥረት በመፍጠር ህብረተሰቡን የማጉላላት ስራን መስራታቸውን ማመን አይፈልጉም ” ሲል አክሏል።
በዚህም ” የፈፀሙት ሕገወጥ ተግባር በተጨባጭ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህን ተግባር የፈጸሙት ላይ መንግስት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሲል በድጎማ የከፈለበትን የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ የሚደረግ እንደሆነ እና ከምርት መሰውር ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሚደረጉ ይሆናል ” ብሏል።
” በነዳጅ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል ” ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ” በግብይት የሚሳተፉ አካላት ጤናማ የንግድ ስርዓትን ተከትሎ ትርፍ ከማግኘት ይልቅ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል ድጎማ ተደርጎበት የሚቀርበውን ነዳጅ በኮንትሮባንድ እና በጥቁር ገበያ አሳልፈው ይሰጣሉ ” ብሏል።
በዚህም ” በየክልሉ ከሚፈጠሩት እጥረት ባሻገር በዚህ መልኩ ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በየቦታው እንዲዘገዩ በማድረግ ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የማጉላላት ተግባር ይፈጽማሉ ” ሲል ወቅሷል።
” ነዳጅ አቅርቦት ላይ ሰው ሰራሽ እጥረት በየጊዜው እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሰል ተግባራት በግልጽ እየታዩ ባለበት አንዳንድ መረጃ ሰጪዎች ለመገናኛ ብዙኃን በሚሰጡት መረጃ ‘ የነዳጅ እጥረቱን የፈጠረው ለኛ የሚሰጠው የገበያ ድርሻ ማነስ ነው ‘ የሚል የማይገናኝ ምክንያት ሲያቀርቡ ይሰማሉ ” ሲል ኮንኗል።
” የነዚህ ተሸከርካሪዎች እና የነዳጁ ባለቤቶች በዚህ ወቅት የፈፀሙት ተግባር ግን የችግሩን ዋነኛ ባለቤት አሳይቷል
Source tikvahe

