Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  OPINION  ደራስያንን እንደሰው ያለመመልከት አባዜ – አለማየሁ ገላጋይ
OPINION

ደራስያንን እንደሰው ያለመመልከት አባዜ – አለማየሁ ገላጋይ

Ethioreview newsEthioreview news—February 4, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፊት ለፊት ስራው፣ ከበስተጀርባ ደግሞ ህይወቱ ይገኛል፡፡ ሥራው የህይወቱ ማጣቀሻ ነው የሚሉ አሉ፡፡ በዚህም ሥራውን እንደ አነፍናፊ ውሻ አስቀድመው ህይወቱን ያንጎዳጉዳሉ፡፡ “እንዲህ ሲል የፃፈው በህይወቱ እንዲያ ስለሆነ ነው፡፡” በማለት ሥራና ህይወቱን ያጋባሉ፣ ያፋታሉ፡፡ ስለዚህ የደራሲ ቤት በሩ ቢዘጋም ከመግባትና ከመውጣት አይከላከልም፡፡ የደራሲ ደጃፍ ውሻ ቢታሰርበትም አያስፈራም፡፡ ቢታጠርም ከዘላዮች አያመልጥም፡፡

እኛ ዘንድ እንዲያ ለማድረግና ለመሆን የሚያስችል ሁኔታ የለም፡፡ ደራሲ የጓዳ ህይወቱ ቀርቶ አደባባይ የዋለው ሥራው እንኳን “በሙሉ አይን” አይታይም። ሀዲስ አለማየሁ፣ በዓሉ ግርማ፣ መንግሥቱ ለማ፣ ከበደ ሚካኤል፣ ፀጋዬ ገብረመድህን… የኖሩት ቀርቶ የፃፉትም የሚታየው በእሽኩርምሚት ነው። ከሥራዎቹ ፊት “ተልመጥማጮች” ያጠሩት የሙዚየም “ክር” አለ፤ አይታለፍም፡፡ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያም አለ፤ “በእጅ መንካት ክልክል ነው” የሚል፡፡ እኔ የሚገርመኝ “የተልመጥማጮቹ” በክር ማጠርና መንገር አይደለም፡፡ የእኛ አክብሮ ሥነ – ፅሁፍን በሙዚየም ህግ መጎብኘት እንጂ …፡፡

“የሀዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር ተረታማ ነው” ከተባለ “ቱግ” የሚሉ “አንቀራባጮች” አሉ። “በዓሉ ግርማ ልቦለድ ያድፋፋል፤ አጨራረሱ መሰላቸት የሚታይበት የተካለበ ነው” ከተባለ የሥራው “ተሸላሚዎች” ፣ “ሐይማኖት የግል ነው፣ ለምን ይነካብናል?” በማለት ህገ መንግሥት መጥቀስ ይዳዳቸዋል፡፡ “የመንግሥቱ ለማ ግጥሞች ጥብቀትና ፍላት የሌላቸው በተሃ ናቸው” ከተባለስ? ጉዳዩን የቤተሰብ ፖለቲካ አድርገው “አብዬን?” የሚሉና የዛገ ጦር ከራስጌ የሚመዙ ሞልተዋል፡፡ “ከበደ ሚካኤል መከሩ፣ ዘከሩ እንጂ አልተቀኙም” የሚል ካለ፣ “ባባቶቻችን ደም” ይዘፈንበታል፡፡ “ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥም እንጂ ዝሩው ያዳግተዋል” ብሎ በህይወት መኖር ያዳግታል …
የእኛ ሥነ – ፅሁፍ መብላላት ሲገባው የሚደነብሸው ለዚህ ሳይሆን ይቀራል? ገንዘብ ያወጣሁበትን መፅሐፍ ለመግዛት፣ ጊዜ ያፈሰስኩበትን ልቦለድ (ለማንበብ)፤ ቦታ የሰጠሁትን ሥራ ለማስቀመጥ … እንዴት በሌሎች እይታ እንድገመግመው እገደዳለሁ? እንዳቅሜ ከቻልኩ “ብበላው”፣ ካልቻልኩ “ብደፋው” ከውይይት ያለፈ ከሳሽና ወቃሽ ሊመደብብኝ ይገባል?…

… እንደውም ከሥራዎቹ አልፈን ደራሲዎቹ ህይወትና ኑሮ ላይ ብንሳፈር “ውረድ!” ባይ እልፍኝ አስከልካይ ሊመደብብን ይገባል? ስለ ሀዲስ ዓለማየሁ ብህትውና፣ ስለ በዓሉ ግርማ ውሎና አዳር፣ ስለመንግስቱ ለማ ሽሙጥ፣ ስለ ከበደ ሚካኤል የኩርፊያ ኑሮ፣ ስለ ፀጋዬ ገብረመድህን የተመላኪነት መንፈስ … ማውራት ግለሰብ ማውሳት ነው?…

ዮሐንስ አድማሱ ስለ ደራሲ ማውሳት ግለሰብ ማማት ተደርጎ እንዳይወሰድ የሚዘክር ተቀዳሚ ገጣሚ ነው፡፡ ስለ ዮፍታሔ ንጉሴ በቀረበው ጥናት ላይ የባለቅኔውን “የቆንጆ ፀርነት” ከማውሳት አልፎ እናቱ “ሒያጅ” እንደነበሩ ይጠቅስና እንዲህ ይላል፤
“ዮፍታሄን እንዲህ ማንሳቴ አለመልኩ እንዳይመለክ፣ አለግብሩ እንዳይወቀስ፣ እንደ ግዑዝ እንዲታይ ነው፡፡”

ዮሐንስ “እንደ ግዑዝ” ሲል ምን ማለቱ ነው? እንደ ዕቃ? እንደ ሀውልት? ወይስ ምን? ብለን እንጠይቅ። ዮሐንስ ማለት የፈለገው ዮፍታሄ እንደ ግለሰባዊ ህልው፣ አድራሻና መዳረሻ እንዳለው ሳይሆን ለመወያያ ወደ ሀሳብነት ደረጃ ከፍ አድርገን፣ የሰው ልጅ ምስጢር ማስተንተኛ ይሁነን ነው፡፡ ደራሲን “ከሰውነት” አውጥቶ ወደ “ሀሳብነት” ማሳደግ፣ ለህብረተሰብ አውጠንጣኝነት የሚበጅ ነው፡፡ እኛ ግን ለዚህ አልታደልንም፡፡

በተለይ ጥቂቶቹ ደራሲዎቻችን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ በሥማቸው የሥነ ፅሁፍ ደብር ይደበርና ጭፍን አምልኮ ይካሄድባቸዋል። አለመልኩ ይመለካሉ፤ አለግብሩ ይዘከራሉ፤ አይመረመሬ ይሆናሉ፡፡
ይሄን አምልኮ ለመሻር በማሰብ ይመስላል ብርሃኑ ዘሪሁን “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ላይ ስለ ደራሲዎች ቁርቁስ ተከታታይ መጣጥፍ አቅርቦ ነበር፡፡ በተለይ መንግሥቱ ለማ እና ፀጋዬ ገብረመድህን ያላቸውን የፉክክር “አተካራ” አጠንክሮ ጠቅሶታል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቀው ጸጋዬ ገብረመድህን፤ “ጦቢያ” መፅሄት ላይ እንዲህ በማለት መልስ ሰጥቶ ነበር፡-

“… ወዳጄ ብርሃኑ ዘሪሁን ነበር በተለመደ ቅንነቱ በሥነ – ፅሁፍ ዓለም የደራሲያን መከራከርና መወዳደር ሙያውን ያዳብራል፣ የአንባቢውንም ህዝብ ጣዕምና ግንዛቤ ያካብታል በሚል ትክክለኛ ሀሳብ ተነስቶ፣ በአዲስ ዘመን አምድ ላይ “የደራሲያን ጦርነት” ብሎ ያስቀመጠው መልዕክት፣ እሱም እኛም ወደ አላሰብነው አቅጣጫ ሄዶ፣ ለከተሜው የቧልት ፍጆታ ሆነ፡፡ እስከዛሬ “ጦርነት” እየተባለ “በምሁራን” አካባቢ ይቧለትበታል፡፡ እንጂ ከወዳጄ ከመንግስቱ ለማ ጋር እንኳን ጦርነት ቁርቋዞም አልነበረንም”
ፀጋዬ ይሄን ይበል እንጂ መለስ አድርጎ ስለ መንግስቱ ለማ ቀልድ ለበስ ንግግር ሲገልፅ አንዳች ነገር እንደነበር ለመጠርጠር እንገደዳለን፡፡

“… እኔ ከገጠር ሜጫ ምድር ከገበሬና ከመለስተኛ ነጋዴ ቤተሰብ መጥቼ፣ አዲስ አበባ በምኒልክ ከተማ፣ ብዙ የሥነ ፅሁፍ ታላላቅ ሰዎች በታወቁበት፣ በደረጁበትና ሥር በሰደዱ መሀል ገብቼ፣ ገና በሀያ ዘጠኝ ዓመቴ ስሸለም፣ የነፍሳቸውን መክሊት እንደወሰድኩባቸው ያህል በተለይ ጉምቱዎቹ የሥነ ፅሁፍ አባቶች ያደረሱብኝን የምቀኝነት ቁስል በቁጭት ሳስታውሰው፣ የወዳጄ የመንግሥቱ ለማ ደማም ቅሬታ፣ እንኳንስ ሊያማርረኝ እንደቅድመ ማስጠንቀቂያ ምክር ነበር የጠቀመኝ፡፡ በዛሬው ጊዜ ታዲያን እንደመንግስቱ ለማ ደማም ቀልደኛ፣ ኮሶውን ከማር ለውሶ ማሻር የሚያውቅበት ደራሲ ስለጠፋ ነው፣ የጭቃ ጅራፍ ለጣፊና የጭቃ ጅራፍ “ተለጣፊ” ብቻ የተንሰራፋው፡፡ ያም ሆኖ የመንግስቱም ቀልድ አንዳንድ ጊዜ መራራ ነበር፡፡”

ሥነ ፅሁፋዊው “በደረቁ እጥበት” የደራሲዎቻችንን ህይወት አንፅቶ የአደባባይ ክት – ልብስ አደረገው እንጂ በየስርጉጡ የተነካካከ ነበር። የሚገርመው በላውንደሪ ሥራ መጠመዳችንና በማንፃት ሥራ መለከፋችን የነበረው እንደነበረው የማቅረብን ያህል የሚጠቅመን አልነበረም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብቅ የሚሉ መረጃዎቻችንን ስንመረምር፣ ፀጋዬ ቁርቁሱን እጅግ አድርጎ እንዳለዘበው ይገባናል።
የሥዕልና የሥነ-ፅሁፍ ሀያሲው ስዩም ወልዴ “ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ” የተሰኘ መፅሀፉ ውስጥ ስለዚሁ የደራሲያን የመሸራደድና የመጠቃቃት ባህርይ ይነግረናል፡፡ ከበደ ሚካኤል የአፄ ኃይለሥላሴ ሽልማት ድርጅት ሲሸልማቸው፣ ደራሲ ዓለማየሁ ሞገስ በዚሁ በሽልማቱ ጉዳይ ስብሰባ ጠሩ፡፡ ወወክማ ለታደመው ሰውም በአደባባይ “ከበደ ደራሲም ተርጓሚም አይደለም፡፡ ከበደ ሌባና ባንዳ ነው” እንዳሉ ስዩም ወልዴ ነግሮናል፡፡

እንኳን የጓዳው ህይወት እንዲህ ያሉ የአደባባይ መግለጫዎችም ያለተፈጥሯቸው ውስጥ ለውስጥ እንዲስለከለኩ እያስገደድናቸው ነው። ለምን? ለማን? … ደራሲዎቻችንን ከህልፈት በኋላም፣ ሲወጓቸው እንደሚደሙ፣ ሲነግሯቸው እንደሚደመሙ ከማሰብ፤ እንደ ዮሐንስ አድማሱ ወደ ሀሳብ ደረጃ አሳድጎ፣ አጠቃላይ የሰው ልጅን ማጥኛ ማድረግ አይበጅም? እኔ ይበጃል ባይ ነኝ፡፡
*ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ሀኪሙን አትግደሉ!  (Whoever you are!)  የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ መልዕክት
የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት በሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመራቸውን ገለፁ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው?

June 3, 20260
OPINION

የቱሲዲደስ ወጥመድ እና የኢትዮጵያ የቤት ሥራ [ልብ ያለው ልብ ይበል]

June 3, 20260
OPINION

ግልፅ ደብዳቤ ለራያ ቆቦ ሕዝብ [በለጠ ሞላ ከትላንት እስከዛሬ እስከማውቀው]

May 28, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news