Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አብይ አሕመድ ለትግራይ ሕዝብ የጊዚያዊ አስተዳደር ዕጩዎች እንዲሰይም ጥሪ አቀረቡ
News

አብይ አሕመድ ለትግራይ ሕዝብ የጊዚያዊ አስተዳደር ዕጩዎች እንዲሰይም ጥሪ አቀረቡ

Ethioreview newsEthioreview news—March 26, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“የጊዜያዊ አስተዳደሩን ተግባር በብቃት መወጣት፣ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ይችላሉ ብላችሁ የምታምኑት እጩዎች ከዛሬ ጀምሮ ጠቁሙኝ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረቡ። “የትብብር ትግል እንዴት ይካሄድ” በሚሊል ርዕስ አቅጣጫ የማስያዝ ስራ እየሰራ ያለው ርዕዮት ሚዲያ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ አብይ አሕመድ ፕሬዚዳንት ለመሾም ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውን ታማኝ ምንጮች እንደነገሩት ገልጾ ማምሻውን ሰፊ ትንተና ሲሰጥ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ይድረስ ለትግራይ ሕዝብ” ሲሉ በግል የማህበራዊ ገጻቸው ባሰራጩት ጥሪ ሕዝቡ በነጻነት ጥቆማ እንዲሰጥ አበረታተዋል።

በቀጥታ ጥቆማ የሚሰጥበትን የኢሜል አድራሻ info@pmo.gov.et በማስቀመጥ ለትግራይ ሕዝብ በቀርበው ጥሪ ላይ የህግ አግባቡ የሚፈቅደው እንደሚከናወን ለማስጨበጥ ደንቦችና አሳሪ ህጎች ተጠቅሰዋል።

“እንደሚታወቀው በፌዴራል ሕገ መንግሥት 62(9) መሠረት፣ በፕሪቶሪያ ስምምነትና አዋጅ ቁጥር 359/1995 የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ፣ አሳታፊ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ይደነግጋል፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተቋቋመው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 533/2 ነው” በሚል የህግ ጥያቄ ለሚያነሱም ሆነ መረጃው ለሌላቸው እንዲያምች ህጋዊ አግባቡ ተዘርዝሯል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 15(3) መሠረት ጊዜያዊ አስተዳደር የሚቆየው ለሁለት ዓመታት ብቻ ነው። ነገር ግን ትክክለኛ ምክንያት ካለ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል ያስታወሱት አብይ አሕመድ፣ ከላይ በተጠቀሱት ህጎች እና በፕሪቶሪያ ስምምነት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጊዜያዊ የአስተዳደር ስራውን አጠናቆ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ህዝብ ለመረጠው መንግስት ኃላፊነቱን ማስረከብ እንደነበረበት አመልክተዋል።

“ነገር ግን” ይላል በትግርኛ ቋንቋ ለትግራይ ሕዝብ የተላለፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቁልፍ ተግባራቶቹን በተያዘለት ጊዜ ማከናወን አልቻለም። አንዱ ቁልፍ ተግባር ለምርጫ ሁኔታዎችን መፍጠር ነበር።  እንዲህ ያሉትን ያልተጠናቀቁ ተግባራት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ ህጉን በማሻሻል የጊዜያዊ የክልሉን የሽግግር አስተዳደር የስልጣን ጊዜን በአንድ ዓመት ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ ጭብጥ በማስቀመጥ ያስረዳል።

የፌደራል መንግስት የጊዜያዊ መንግስቱን የስልጣን ዘመን ለማራዘም ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንም በጥሪው ተካቷል።

በቁጥር 533/2015 አንቀጽ 3(2) መሰረት የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሹመት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነትና ስልጣን እንደሆነ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ምንም እንኳን ሹመት የመስጠቱ ስልጣን በህግ የእሳቸው ቢሆንም ” የጊዜያዊ አስተዳደርን ተግባር በብቃት በመወጣት፣ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ይችላሉ ብላችሁ የምታምኑትን እጩ ከዛሬ ጀምሮ info@pmo.gov.et በሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኢሜል መላክ ትችላላችሁ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ትህነግ ወደ ትግራይ ጓዙን ጠቅልሎ ከሄደ በሁዋላ፣ ሰፊ ኃይል አደራጅቶ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ከተጀመረው ጦርነት በሁዋላ የተለያዩ መሪዎች ትግራይን እንዲያስተዳደሩ ቢመደቡም የተፈለገው ውጤት ሊገኝ

አልቻለም።በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ትግራይን እንዲመሩ የተመደቡት የጦርነቱ ወቅት አፈ ቀላጤ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በትህነግ ውስጥ በተፈጠረ መሰንጠቅ ሳቢያ መስራት ተስኗቸው ቢሯቸውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በርካታ ሚስጢሮችን ይፋ ያደረጉት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው።

“ትህነግ – ዲ” የሚባለውና በዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን በትግራይ ሰራዊት የተወሰኑ አመራሮች ስለሚደገፍ የጊዜያዊ አስተዳደሩን መዋቅር በኃይል በማፍረስ ቁልፍና ማህተም መረከቡን ተከትሎ የትግራይ ወጣቶች ተቃውሞ ማሰማታቸው፣ ይህ ሲሆን ታጣቂዎቹ ተኩሰው መግደላቸና ማቁሰላቸው፣ እንዲሁም በርካቶችን ማሰራቸው አፍቃሪ ትህነግ በሆኑ ሚዲያዎች ሳይቀር በቪዲዮ መረጃ ተደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ በተደጋጋሚ በተካሄደ ውይይት በትግራይ አዲስ የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም ስምምነት መደረሱን የዘገቡ አንዳንድ ሚዲያዎች ” ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፕሬዚዳንት ሆኑ” በሚል ምንጮች እየጠቀሱ ሲዘግቡ ሰንበተዋል።
የርዕዮቱ ቴዎድሮስ ጸጋዬ በትግራይ ብሄርተኝነት ስሜትና ቅኝት መነጽርና ድንበር አበጅቶ በሚመራው የግሉ ሚዲያው በትናንትናው ዕለት ለአንድ ሰዓት ከሃያ አራት ደቂቃ ብቻውን ባሰራጨው የግል ትንተናው፣ ስለ አዲሱ ፕሬዚዳንት ስያሜ የሰጠው መረጃ የተለየ ነበር።

” አብይን ለማስወገድ የሚደረግ ጥምረትን እንደግፋለሁ” የሚለው ቴዎድሮስ የትህነግ አመራሮች ቅድሚያ አንድነት መፍጠርና በጥምረቱ የበላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ግን ዋና ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ ይገልጻል።

ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ለረዥም ሰዓት ባቀረበው የብቻው ዲስኩር፣ አዲሱን ሹመት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውን መረጃ እንዳለው ጠቅሶ ሲዘረዝር ተሰምቷል።

በዚሁ ዝርዝር ትንተናው ውስጥ አብይ አሕመድ የአገር መከላከያ በትግራይ ክልል ባሉ ካምፖቹ ተመልሶ እንዲሰፍር መፍቀድ ከቅድመ ሁኔታዎቹ መካከል አንዱና ዋናው እንደሆነ አመልክቷል።

ይህ በተላለፈ ሰዓታት ውስጥ አብይ አሕመድ “የትግራይ ሕዝብ ሆይ የትግራይን ሰላም የሚያስጠብቅ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ይሰራሉ ብለህ የምታስባቸውን እጩዎች ጠቁም” የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ኢ.ቢ.ኤስ ይፋ ያደረገው የብርቱካንን ቪዲዮ ወደ አየር እንዲመልስ መንግስት ጠይቋል” ሰራተኞች
Ethiopia Advances WTO Membership As Govt Announces ‘Successful’ Fifth-Round Negotiations
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2