በጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው።
በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት በ “X” ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን ተቸካይ ነው።

የትህነግ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት በጦርነቱ ወቅት ስለተፈጸመው ቅድሚያ ግምገማ መደረግ እንዳለበት የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን፣ አሁን ላይ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረው ይፋዊ ኝኙነት በየአቅጣጫው ተቃውሞ እያስነሳ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “ከቀደመ ተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር፣ በህዝብ ኪሳራ የግልና የቡድን ጥቅሙን ለማስጠበቅ ስልጣንን የሙጥኝ ያለ ሃይል ነው” ሲሉ ፕሮፌሰሩ በይፋ ዘልፈዋል።
የሻዕቢያ ዋና ጀነራልና ከፈተኛ የሚባሉ ሽማግሌ መኮንኖች መቀለ መግባታቸውን ተከትሎና ሰሞኑንን አቶ ልደቱ “ትህነግን አትደብድቡት” በማለት በይፋ እየተሟገቱ ባለበት ሰዓት ፕሮፌሰሩ የሰነዘሩት ትችት በብዙ መልኩ በትግራይ ያለውን የሕዝብ ስሜት የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።
“ወንድም ሕዝብ አትበሉን። ለጨፈጨፍነው የትግራይ ሕዝብ ካሳ አትጠይቁን” በማለት የተሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ ኝኙነት የከመረውን የትህነግ ክፋይ ” ሲፈጠር ጀመሮ ለሻዕቢያ ለመገረድ የማለ” በሚል አፍቃሪ ትህነግ የነበሩ ሚዲያዎች በተከታታይ እየዘለፉት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ትህነግ በአገር መከላከያ ላይ በክህደት ቀስቅሶት በተቀጣጠለውና ቂም ቋጥሮ ሲተብቅ ለነበረው ሻዕቢያ መልካም አጋጣሚ በሆነለት ጦርነት የሞቱት የትግራይ ተወላጆች ከአንድ ሚሊዮን እንደሚልቁ በተለያዩ አካላት መገለሹ ይታወሳል። ፕሮፌሰር ክንድያ በሚመሩት የመቀለ ዩኒቨርስቲ የተጠና ጥናት ጠቅሰው መረጃውን ያሰራጩ እንዳሉት ከሞቱት ውስጥ 76 በመቶ የሚሆኑትን የጨፈጨፈው ሻዕቢያ ነው።
ሻዕቢያ በትግራይ ክልል የፈጸመው ጭፍጨፋ ብቻ ሳይሆን ከፈጸመው ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ውድመት ወዘተ አንጻር እነ ደብረጽዮን በዚህ ደረጃ ራሳቸውን ሸጠው ከሻዕቢያ ጋር ለመስራት መስማማታቸው የፈጠረውን ስሜት አመላክች አሳብ በፕሮፌሰሩ ቲዊት ውስጥ ተካቷል።
በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የትህነግ ክፋይ ኃይል በትግራይ ደቡባዊ ዞን ውስጥ አንዳች አይነት ተቀባይነት እንደሌለው የጠቀሱት ፕሮፌሰር ክንድያ፣ ቡድኑ በዞኑ ህዝብ ያጣውን ህጋዊ ቅቡልነት (legitimacy) በሃይል ለማግኘት ከሰሞኑ የጀመረው እንቅስቃሴ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ካለችው እንስሳ ጋር የሚመሳሰል በቀቢጸ ተስፋ የገባበት የእውር ድንብር እርምጃ ነው ሲሉ ኮንነውታል።
በሌላ ተመሳሳይ ዜና የትህነግ የጦር መሪዎች አስመራ ደርሰው ከመጡ በሁዋላ የሻዕቢያ ዋና ጄነራል መኮንኖችን ይዘው መቀለ መግባታቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ አስታውቀዋል።
ያለውን መሳሪያና ተተኪ የሌለውም ሰራዊት ያመቻል ወዳለው አካባቢ እያስገባ ያለው ሻዕቢያ ዋናውን ጄነራሉን ወደ መቀለ የላከበትን ምክኛት ሳይገልጹ ዜናውን ያሰራጩ ጉዳዩ በምክክር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት ለማድረግ እንደሆነ አመልክተዋል።
የእነ ደብርጽዮን ትህነግና የፖለቲካ አመራሩና የጦር መሪዎች ህገ መንግስት ጥሰው ከሻዕቢያ ጋር በይፋ ግንኙነት እያደረጉ ቢሆንም የፌደራል መንግስት ዝምታን መመረጡ በርካቶችን እያነጋገረ ሲሆን፣ በተለይ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ማክሰኞ ዕውቅና ካነሳ “ትርምስ ይፈጠራል” በሚል ዛቻ ሲያሰሙ እንዳልሰማ መሆኑ ግራ ያጋባቸው ጥቂት አይደሉም።
ተበታትኖ የነበረው የፋኖ ኃይል ተሰባስቦ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ጸሃፊ፣ የሎጂስቲክ ኃላፊ፣ የጦር አዛዣና ምክትል እንዲሁም የስራና የኃላፊነት ደረጃ ሳይመድብ ህብረት መፍጠሩን ተለትሎ ወደ አስመራ ያቀኑት የሻዕቢያ መኮንኖች ጉዟቸው በድል የታጀበ እንደሆነ ደጋፊዎቻቸው እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ኃላፊ ሳመድብ ስለተመሰረተው የፋኖ አንድ ድርጅት ስምምነት አለመደረሱን፣ ቅሬታ መኖሩን እንዲሁም የጥድፊያ እንደሆነ የሚገልጹ መረጃዎች እየቀጡ ነው።
የሚታወቁ ስምና የአማራር ኃላፊነት ያላቸው በስክ ይህንኑ ልዩነት አስመልክቶ ሲነጋገሩ የተቀዱ የተለያዩ የስልክ ውይይቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በሚል ስያሜ የተቋቋመው ድርጅት ባወጣው መግለጫ ስልጣን ሳይከፋፈሉ የተመረጡት መሪዎች 13 ናቸው። የአዲሱ የፋኖ ህብረት መመስረቱ ይፋ ሲሆን እስከንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) እጣ ፈንታ አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።
እስክንድር “እኛ የተXአልን ነን። ድርጅት መስርተናል። እነሱ ተሰባስበው ድርጅት ሲመሰርቱ እንነጋገራለን” በማለት ወደ ኤርትራ ሊልከው ለነበረ አጋሩ መመሪያ ሲሰጥ የስልክ ድምጹ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነው።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter

