Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የፕሮፓጋንዳ ምችና የጦርነት አሻራ በትግራይ

    March 11, 20230

    ሥርዐት አልባው ንግድ እና ስጋት የፈጠረው የኑሮ ውድነት!

    April 4, 20220

    በጥቃት ሳቢያ ተመድ በአማራ ክልል የረድዔት ሥራዎቹን ሊያቆም ነው – የኤርትራና ኢትዮጲያ የስልክ ግንኙነት ተቋረጠ

    October 9, 20240

    የህወሓት ‘ቀጣይ ዕቅድ’ አፈትልኮ ወጣ

    July 1, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ብልጽግና ከሸነፈ – ቀጣይዋ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሌሊሴ ነሜ

    June 19, 20210

    “በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል”

    February 18, 20250

    የቆዳ ዋጋ መውደቅና አገራዊ ኪሳራው

    May 9, 20210

    “ኡሁሩ ኬንያታ የትግራይ አማጺ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ይፋ አደረጉ”

    October 7, 20220

    Uhuru Pulls Out of First African Union Peace Talks

    October 7, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  “ህወሃት የራሱ ጉዳይ፤ቅድሚያ ለትግራይ ሕዝብ” ብ.ጄ ገ/እግዚአብሄር ነጻ መሬት የተደራጀው ጦር መሪ
News

“ህወሃት የራሱ ጉዳይ፤ቅድሚያ ለትግራይ ሕዝብ” ብ.ጄ ገ/እግዚአብሄር ነጻ መሬት የተደራጀው ጦር መሪ

Ethioreview newsEthioreview news—June 10, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የአገሪቱን ህገ መንግስት በመጣስ ከሻዕቢያ ጋር አዲስ ግንኙነት ከጀመረው ቡድን በመለየት “ሓራ” ወይም ነጻ መሬት የሰፈሩት የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች አጀንዳ መሆን ከጀመሩ ሰነባብቷል። የሰሜን ዕዝ አስተዳዳሪ እና ምክትል አዛዥ የነበሩት ጄነራል እንደሚመሩት የሚነገርለት ይህ ኃይል አራት ክፍለ ጦር ያደራጀና ሰፊ ድጋፍ ያለው ለሻዕቢያም ስጋት እንደሆነ ሲገለጽ ነበር። አሁን ይፋ እንደሆነም ሻዕብያን አጥበቀው ይቃወማሉ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረት መኖሩን እና ግጭት ውስጥ ቢገባ የዚህ ኃይል አሰላለፍ ምን ሊሆን እንደሚችል ተጠይቀው “አሰላለፋችን ከሕዝብ ጋር ነው። እነርሱ [የህወሓት አመራሮች] ከጌቶቻቸው ጋር ሊሄዱ ይችላሉ፤ እኛ ግን ከሕዝብ ጋር ነው የምነቀረው” ሲሉ ለቢቢሲ ትግርኛው ክፍል መልስ ሰጥተዋል።

የከፍተኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት የእነ ዶክተር ደብረጽዮንን ቡድንን በመደገፍ የታጣቂዎቹ ኃይሎች በይፋ ድጋፍ ሲሰጡ ስብሰባ ረግጠው ከወጡት መካከል ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ይጠቀሳሉ። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የኮር አመራሮች የተካተቱበት ይህ ኃይል ነጻ መሬት ላይ መስፈሩን ተከትሎ ብዙ ቢባልም በይፋ የሰጠው መረጃ አልነበረም።

የአቶ ጌታቸው ካቢኔ የነበሩና ከውስጥ መረጃ እንዳገኙ ጠቅሰው ” ስጋት የገባው ሻዕቢያ ይህን ኃይል ደምስሱ” ሲል አብረውት እየሰሩ ላሉት የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን መመሪያ መስጠቱን ይፋ አድርገው ነበር። ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት ጄነራሉ እንደጠቆሙት ስብስባቸው ሻዕቢያን አይደግፍም።

More stories

ስለ ኢትዮጵያ የሚነዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን በተደራጀ መንገድ ለመመከት

July 28, 2021

የጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር ” ካሁን በሁዋላ በስሜ ጠብ መንጃ ይዞ የሚነቀሳቀስ ሃይል የለም”

April 28, 2023

የግብጽ ክስ «ቧልት ነው፤ ያለ ፈተና የፀና ሕልውና የለም» የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር

January 18, 2024

የአፍሪካ ቀንድ ጥልፍለፍ ከሰሞኑ!

January 5, 2023

ቢቢሲ ትግርኛው ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ ያነጋገራቸው የዚሁ ክንፍ መሪ ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ከፓርቲ ነጻ የሆነ ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል። አቶ ጌታቸውና ወ/ሮ ኬሪያ ይህ ኃይል ለትግራይ ሕዝብ ስለሚያስፈልግ እንዳይበተን አስፈላጊው ሁሉ እንደሚደረግ መጠቆማቸው አይዘነጋም።

ከትግራይ ኃይሎች በመለየት ከአፋር ክልል ጋር በሚዋሰን አካባቢ የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የሚናገሩት ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) “ከፓርቲ [ህወሓት] ነጻ የሆነ ኃይል” ለመፍጠር ወደ ነጻ መሬት መውረዳቸውን ገልጸው ለቢቢሲ የሰጡትን መረጃ እንዳለ አቅርበነዋል።

ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አዲስ ነገር ለመፍጠር” ወደ በረሃ መውደረዳቸውን ሲያብራሩ “ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣. . . ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር ” እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።

ህወሓትን የመጣል ዓላማ እንዳላቸው የተጠየቁት ጄነራሉ “እኛ የምንሠራው ፓርቲ፣ እኛ የምናቋቁመው ወታደራዊ መንግሥት የለም” ብለዋል።

በአፋር እና በትግራይ ክልሎች ውስጥ አራት ክፍለ ጦር ያለው ሠራዊት ማደራጀታቸውን የሚናገሩት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ፣ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን ይናገራሉ።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።
ይህንንም ተከትሎ የሠራዊቱ አመራሮች ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነን እና ሌሎች የሠራዊቱን ውሳኔ የተቃወሙትን ማገዳቸው ይታወሳል።

“አሁን በትግል ላይ ነን ያረጀነውም በትግል ነው” ያሉት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር “ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም” ብለዋል።

“የትግራይ ሕዝብ በነጻነት እና ወገንተኝነት በሌለበት መንገድ የመረጠውን አካል ነው የምናገለግለው” ብለዋል።

ከሌሎች የትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር ያላቸው ልዩነት በንግግር ለመፍታት ሞክረው “እምቢ” እንደተባሉ የሚናገሩት ጄነራሉ፤ የተወሰዱ እርምጃዎችንም መቃወማቸውን ገልጸዋል።

መጀመሪያ ከኮር በላይ የሆኑ አመራሮች ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር አውግዘው መግለጫ ሲያወጡ “አልቀበልም” በማለታቸው መታገዳቸውን ያስታወሱት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር “አንቀበልም ማለት መብታችን ነበር” ካሉ በኋላ “ባህሪያቸው ግን ማገድ ነው” ብለዋል።

“እኔ የህወሓት ደጋፊ አይደለሁም ማለት፣ ራሱን ይቻል አልሸከመውም ማለት፣ ሠራዊቱ መሸከም የለበትም ማለት ነው” ብለዋል።

“ራሱን ችሎ ወደ ሕዝብ ይግባ እና ይወዳደር፣ ህወሓት ይጥፋ አይጥፋ የራሱ ጉዳይ ነው። ይቀጥል አይቀጥል የራሱ ጉዳይ ነው። እኔን የሚመለከተኝ የትግራይ ሕዝብ ጉዳይ ነው።”

ለተቃውሟቸው ጠመንጃ ማንሳትን መምረጣቸው በጦርነት ውስጥ የቆየውን የትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግጭት አዙሪት አይከተውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ጄነራሉ “እኔ ኢንተርናሽናል ጄነራል ነኝ። ይህንን ሆኜ የህወሓት ሚሊሻ መሆን አልፈልግም። ህወሓት ፓርቲያችን ነው የሚሉ የእርሱን ሚሊሻ እንደሆኑ ነው የሚቆጥረው። ሚሊሻነትን ደግሞ አልቀበልም” ብለዋል።

ህወሓት ያለውን ካላደረግክ “ትጠፋለህ፤ መኖር አትችልም። ከትግራይ ትጠፋለህ” ያሉት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ያላቸውን ልዩነት ለመፍታት “በጽሑፍ ሞክረናል” ብለዋል።

“ማኅተም መንጠቅ አያስፈልግም ማለት ያስቀጣል እንዴ? ጽህፈት ቤቶች በመዶሻ እየሰበርክ አስተዳዳሪዎች ማባረር ትክክል አይደለም ማለት ያስቀጣል እንዴ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።

እኛ የታገልነው በሰላም እንድንኖር ነው ያሉት ጄነራሉ “በሰላማዊ መንገድ በጽሑፍ ሞከርን። ብዙ ጊዜ ሞከርናቸው እምቢ አሉ። የመጨረሻ ሊያስሩን መሆኑን ስናውቅ ወጣን። ሊያስሩን የፈለጉት ደግሞ ይህ አሁን የሚመኩበትን ሠራዊት እንደሚያጡት ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ በአፋር እና በትግራይ አካባቢ ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጣቂ ቡድናቸው ስም ገና አለመወሰኑን እና ወደፊት እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

“እስካሁን ሦስት አራት ግንባሮች አሉን” ያሉት ጄነራሉ በትግራይ ሠራዊት ውስጥም ብዙ ኃይሎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

“የእኛ ሠራዊ ት ነው የሚሉት ሚሊሻ ከእኛ ጋር ነው ያለው። ከፍቶት ነው ያለው። ለውጥ ይፈልጋል። ጊዜው የወጣቶች እንዲሆን ነው የሚፈልገው። እንዲማር እንዲለወጥ ይፈልጋል። የተሻለ ገቢ እንዲኖረው ይፈልጋል። ወላጆቹ እና ቤተሰቦቹ ከውጊያ ወጥተው አሁን መልሶ ግንባታ እና ለውጥ ሰላም ይፍለጋል። ስለዚህ ወጣቱ ሠራዊት እኛ ጋር ነው። ብዙዎች ነን።”

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ወደ ግጭት ከመግባታቸው በፊት የሚያሰቀምጡት ቅድመ ሁኔታ መኖሩን ተጠይቀው “እስካሁን ያናገረን ኃይል የለም” ብለዋል።

መቀመጫቸውን በአፋር እና በትግራይ ክልል ማድረጋቸውን የጠቀሱት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር “ወደ አፋር ወርደን እንድንደራጅ ያደረገን ምክንያት አፋር እና ትግራይ ቤተሰቦች ስለሆኑ ነው። የፈቀደልን መንግሥት የለም። ቸግሮን ነበር እዚያ አካባቢ ያሉት አካላት ለተቸገርን እዚህ እንደራጅ ወይ? እንሰንሰብ ወይ? ብለን ጠየቅናቸው። ተሰባሰቡ አሉን። ይህ እኮ ትልቅ ነገር አይደለም። ትግራይ ጫፍ ነው ያለነው። ፈቃድ መጠየቅም የለብንም” ብለዋል።

አራት ግንባር እንዳላቸው የሚጠቅሱት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር “ትልቁ ኃይላችን የሚገኘው ትግራይ ውስጥ ነው” ይላሉ።

ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ተጠይቀው “እዚህ እንዳለን ያውቃሉ” ያሉ ሲሆን፣ የሚያገኙት ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደሌለ ግን ተናግረዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ሲሾሙ ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን እና ወገንተኛ ያልሆነ ሠራዊት መገንባት ካልተቻለ “እናንተ ደገፋችሁን አልደገፋችሁን ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለው ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

ጥር 15/2017 ዓ.ም. የትግራይ ሠራዊት አመራሮች ውሳኔን ከእርሳቸው ጋር ተቃውመው የወጡ እና አሁን ሠራዊት እያደራጁ የሚገኙ አመራሮች እነማን እነደሆነ ተጠይቀው ስማቸውን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረት መኖሩን እና ግጭት ውስጥ ቢገባ ውሳኔያቸው ምን እነደሚሆን የተጠየቁት ጄነራሉ “አሰላለፋችን ከሕዝብ ጋር ነው። እነርሱ [የህወሓት አመራሮች] ከጌቶቻቸው ጋር ሊሄዱ ይችላሉ፤ እኛ ግን ከሕዝብ ጋር ነው የምነቀረው” ብለዋል።

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የተወለዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በ1974 ዓ.ም. ህወሓት ወታደራዊውን አመራር ለመጣል የሚያደርገውን ትግል ተቀላለሉ።

በህወሓት ውስጥ ከተራ ወታደር እስከ ክፍለ ጦር አመራር ሆነው ያገለገሉት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በመጨረሻም የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አስተዳዳሪ እና ምክትል አዛዥ ነበሩ።

የትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ ከጥቂት ወራት በፊት በጡረታ ከመከላከያ ሠራዊት የተሰናበቱት ጄነራሉ በትግራይ ጦርነት ውስጥ ወታደራዊ አመራር ሆነው ተሰልፈዋል። ጄነራሉ በትግራይ ሠራዊት ውስጥ አርሚ 50 የሚባለውን ልዩ ኮማንዶ ኃይል እንደገነቡም ይነገርላቸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአፋር ያለው የታጣቂ ቡድንን አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ፖሊስ የሲዳማ ቡናና የወላይታ ዲቻ ጨዋታ አስመልክቶ መረጃ ሰጠ፤ “እናቴ ልጅሽ ሞቷል ተብላ እያለቀሰች ነበር”
ሻዕቢያ ለዜጎቹ ጠንቅ እየሆነ ነው፤ ኡጋንዳ ቪዛ ከለከለች፤ ሌሎች አገራትም እንዳይከተሉ ስጋት አለ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news