Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ እስክትገነጠል ድረስ ማገገሚያና ምሽግ ነው” አምባሳደር አስገዶም
News

“የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ እስክትገነጠል ድረስ ማገገሚያና ምሽግ ነው” አምባሳደር አስገዶም

Ethioreview newsEthioreview news—June 3, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በማለት የሚጠራው ስብስብና ደጋፊዎቹ በኢትዮጵያ ሕዝብ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በተደጋጋሚ የጄኖሳይድ ክስ ያለማቋረጥ የሚያሰሙበት ዋና ስልት ይፋ ሆነ። የፕሪቶርያ ስምምነት ማድፈጫ ወይም ማገገሚያ መሆኑን እነዚሁ የትህነግ ክንፎች አረጋግጠዋል፡፡ 

ራሱን ብቸኛ የትግራይ ሕዝብ ወኪልና ተከላካይ አድርጎ የሚያቀርበው ትህነግ በአገር መከላከያ ላይ የክህደት እርምጃ መውሰዱ በመላው ኢትዮጵያ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም። በተለይም ግፍ የተፈጸመባቸው የመከላከያ አባላት እያነቡ በደላቸውን ሲናገሩ የነበረው የሕዝብ ስሜት መራር ከመሆኑም የተነሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በሙሉ ፈቅደኝነት የተቀላቀሉት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነበሩ።

ምርጫ ቦርድ ህልውናውን ገፎ የሰረዘው ትህነግ፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት እንደ ማገገሚያ እንደሚጠቀምበት የተገለጸው ከቀናት በፊት በተደረገ የጋራ የዙም ውይይት ላይ ሲሆን፣ ውይይቱን  የተዘጋጀው በUTNA ( Union of tigrayans in north america ) እና በገረአልታ ኢንስቲትዩት አማካኝነት እንደሆነ ዝግጅቱን የተከታተሉ አመልክተዋል፡፡ 

 የዙም ምክክር መድረኩ ከላይ የተጠቀሱት ክፍሎች ቢያካሂዱትም፣ ሰነዱ የተዘጋጀው በእነ ዶክተር ደብረጽዮን ትህነግ አማካይነት እንደሆነ ተመልክቷል።  UTNA ( Union of tigrayans in north america )እና ገረአልታ ኢንስቲትዩት ሁለት ተመጋጋቢ የትህነግ እህት ቅርንጫፎቹ እንደሆኑ ይታወቃል። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ዜናውን ያሰራጩት ወገኖች እንደሚሉት “ጄኖሳይድ ተፈጽሟል” በሚል በተደጋጋሚ የሚቀርበውን በዙም ስብሰባው “ጄኖሳይድ የፈፀመ አካልና ጄኖሳይድ የተፈፀመበት ህዝብ አንድ ላይ መኖር አይችሉም” በሚል አምባሳደር ፍስሃ አስገዶም በተናገሩት ንግግር ከፕሪቶሪያ ስምምነት ጋር ተያይዞ ብቅ ማለቱ ተሰምቷል። ዜናውን ያሰራጩት አምባሳደሩ “ጄኖሳይድ የፈፀመ አካልና ጄኖሳይድ የተፈፀመበት ህዝብ አንድ ላይ መኖር አይችሉም” ሲሉ ንግግራቸው አሁን ላይ አዲስ ቅንጅት ከጀመሩትና በከፍተኛ ወንጅለ፣ አስነዋሪ ተግባራት፣ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያና አስገድዶ መድፈር የሚከሰሰውን የሻዕቢያዋን ኤርትራን ስለማካተቱ አላብራሩም።

በጦርነቱ ወቅት የትህነግ የውጭ ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር  ፍሰሃ አስገዶም በዙም ምክክሩ ላይ “ትግራዋይ በፕሪቶሪያው ስምምነት አጥር ስር ለመኖር ፍላጎት የለንም” ሲሉ አሳባቸውን አስፍተዋ ማብራራታቸውን ከስብሰባው መረጃ ያገኙ ገልጸዋል።

ፍስሃ አስገዶም “የፕሪቶሪያውን ስምምነት የምንጠቀመው እንደ ማገገሚያ ቤት ነው። የምንጠቀምበት ከበሽታችን ተፈውሰን ሙሉ ጤናችን እስኪመለስልን ድረስ ነው። እናም የፕሪቶሪያው ስምምነትን እንደ ማቆያ የምንጠቀምበት ማገገሚያ ቤት ማለት ነው” በማለት በዙም ምክክራቸው ላይ ተናግረዋል።

የፕሪቶሪያውን የሰላም አማራጭ ስምምነት ትግራይን ገንጥሎ ነፃ ሃገር ለማድረግ የሚያስችል ጊዜ ላይ እስኪደርስ ድረስ ብቻ ለስልት  እንደሚጠብቁት አስረድተዋል። 

የሩቁ ቢቀር ትህነግ ትግራይን የመገንጠል ዕቅድ ይዞ ይንቀሳቀስ እንደ ነበር በቅርቡ ወ/ሮ ኬሪያ ለርዕዮት በሰጡት ቃለ ምልልስ ገሃድ አድርገዋል። የትህነግ ፖሊት ቢሮ አባልና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኬሪያ አንቀጽ 39 ክልሎች የሻቸውን መወሰን እንደያስችላቸው የተፈጠረ ህግ መሆኑን እየተማሩ በፖለቲካ ማደጋቸውን አስረድተዋል። ድርጅታቸው ሃምሳ ዓመት ያለ ኮሽታ አገር እንደሚመራና ጊዜው ሲደርስ አንቀጹን ጠቅሶ ፍቺ ሊፈጽም እንደሚችል አመልክተዋል። 

ይሁን እንጂ ይህ ያደጉበት የአንቀጽ39 አስትምርሆት እንደተባለው ባለመሆኑ “ፌዴራል ሆነን ብዙ ዓመት እንሠራለን፤ ኢህአዴግ ውስጥም የምንከተለውን አዲዮሎጂ እስከ 50 ዓመት ይቆያል የሚል አመለካከት ስለነበር በአብዛኛው የፌዴራሉን ክንድ የሚያፈረጥም ነገር ነበር የምንሠራው እንጂ ክልሎች እንደፈለጉ ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን አልገነባንም፤ እንዲሆኑም አላደረግንም፤ ተቋማቱ (የፖሊስ፣ የፍርድቤት ወዘተ ማለታቸው ነው) በፓርቲው ሳምባ ነበር የሚተነፍሱት፤ ባይሆንማ ኖሮ ይህ ሕገመንግሥት እያለ ለምን ጦርነት ውስጥ ገባን” የሚል ጥያቄ “የቆሙ” ላሉዋቸው አለቆቻቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

ይህ ሁሉ ዝግጅት ከከሸፈ በሁዋላ አሁን ላይ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከመጥፋት የዳነው ትህነግ ለሁለት ተከፍሎ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በተደረገው ውይይት ስምምነቱን “ማድፈጫ” በማደረግ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደሩ አብራርተዋል፡፡

እንደ አምባሰደር ፍሰሃ አስገዶም ትግራይ ተነጥቃለች የሚሉትን ወይም ምዕራብ ትግራይ ሲሉ የሚጠሩትን ክፍል፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ስር በመሆን ለማስመልስ እንደሚሰሩ መናገራቸውም ታውቋል፡፡ ይህን የሰሙ የአማራ ታጣቂ ኃይሎችም ሆኑ ከትህነግ ጋር እየሰሩ ያሉ ፋኖዎች ምን ለማስፈጸም እንደሆነ ሊያስቡበት እንደሚገባ ጠይቀዋል።

ትህነግ ከፌደራል ሕግ ጋር የሚጣረስ ስራ እየሰራ፣ የፌደራል ተቋማትን አሰራር እየጣሰ፣ ከመርህ ውጭ ከኤርትራ ጋር እየሰራ መልሶ “የፕሪቶሪያ ስምምነት አልተከበረም” በሚል ደጋግሞ ድምጹን የሚያሰማው ይህንኑ አሁን ይፋ የሆነውን ዓላማውን ለማስፈጸም እንደ ስልት እንደሚጠቀምበት ዜናውን ይፋ ያደረጉ አስታውቀዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብም ሆነ በክልሉ የሚሰሩ ተቀናቃኝ ድርጅቶች የፕሪቶሪያ ሕግ አፈጻጸም ምን ምን ጉዳዮችን እንደሚያካትት፣ ምንን እንደሚከለክል በማጥናት ሕዝቡን እንዲያስተምሩም መክረዋል። 

ትግራይን አገር ለማድረግ ምክንያት ስለሚያስፈልግ “ትግራይ ጄኖሳይድ” በሚል በተደጋጋሚ የሚነሳው ለዚሁ አምባሳደሩ በምክክሩ ላይ ይፋ ላደረጉት ስልታዊ እንቅስቅሴ ማስደገፊያ እንደሆነ ያመልከቱ በቅርቡ አሜሪካ የወሰነችውን ውሳኔ አስታውሰዋል። በወቅቱ የተላለፈው ውሳኔ የትህነግ ደጋፊዎችና መሪዎች መቃወማቸውን እነዚሁ ወገኖች ይጠቅሳሉ፡፡ የተቃውሞው መነሻም ጉዳዩ ከላይ ለተገለጸው ምክኛት በመሆኑ እንደሆነ ህጉን ሲቃወሙ የነበሩ ሲያስታውቁ ነበር።

በሁለቱ ወገን የነበረው የክስና መከላከል ሂደት በተጧጧፈበት ወቅት ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው  HR_4350  ውስጥ  አንቀፅ 6464 ከረቂቅነት መሰረዙ ሲሰማ በወቅቱ ህጉን ሲቃወሙ ለነበሩ ዜጎች ሰበር ዜና ነበር። 

በወቅቱ እንደተሰማው የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ሴናተር  ጂም ኢንሆፍ ለካውንስሉ  በላኩት መረጃ አንቀጹ መሰረዙን አስታውቋል።

ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በሴኔት ቢሮ የታሰበው HR_4350 ውስጥ  የተሰረዘው አንቀፅ 6464 ከረቂቅ Determination of potential Genocide or crimes Against Humanity  የሚለው ነበር።

The “declaration of genocide in Tigray” amendment has been removed from the National Defense Authorization Act (NDAA).  የሚለው ዜና ይፋ ሲሆን ካውንስሉ እንዳለው፣  ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ዲያስፖራዎች፣  አፍሪካዊያን እና መላው የ NoMore እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ለአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስልክ በመደወል ኢሜይል በመፃፍ እንዲሁም ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄድ ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ ነው።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ኢትዮጵያን ትልቅ አገር ናት፤ ኃላፊነቱም ከባድ ነው ” የቁንጅና ንግስት ሀሴት ደረጄ
At 34, Time to Tend to Matters at Home?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2