Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ” ሰባት የኦሮሞ ልሂቃን አስመራ ኢሳያስ አፉወርቂ ዘንድ [ለቅባት] ይሄዳሉ” አቶ ልደቱ አያሌው
News

” ሰባት የኦሮሞ ልሂቃን አስመራ ኢሳያስ አፉወርቂ ዘንድ [ለቅባት] ይሄዳሉ” አቶ ልደቱ አያሌው

Ethioreview newsEthioreview news—June 14, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሰባት የኦሮሞ ልሂቃን አስመራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር እንደሚሄዱ ታወቀ። ጉዞው “ቅባት” ለመቀበል እንደሆነ ገልጸው ዜናውን የጠቆሙት ኢሳያስ “ኦሮሙማ፣ ኩሽና ሴም” በማለት በአደባባይ በኢትዮጵያ ደም እንዲፋሰስና አገር እንዲረበሽ የያዙትን ዕቅድ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማልዘብ ነው። ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ አንዱ ናቸው።

የሚመሩትን ሕዝብ በስደት በትነው 34ኛውን የ”ነጻነት” በዓል ያከበሩት አዛውንቱ የኤርትራ ፕሬዚዳንት በዕለቱ የኢትዮጵያ መንግስትን ከኦሮሞ ጋር ለማያያዝና የኦሮሞን ሕዝብ ነጥለው የጥቃት ዒላማ ለማስደረግ ሆን ብለው “የኦሮሞን ህዝብ የማይወክል የኦሮሙማ ርዕዮተ ዓለም” የሚከተል መንግስት እንዳለ አስመስለው ማቅረባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል።

“አንድን ሕዝብ በስም ጠርቶ መፈረጅ ለጄኖሳይድ ማመቻቸት ነው” በማለት በተለያዩ አግባቦች ኢሳያስን የወቀሱ ” አካሄዱ ባይሳካም አደገኛ ነው። ይህ ደግሞ ፍርሃቻ የወለደውና አገሪቱን በሰሜንና ደቡብ ኃይሎች ለይቶ ለማባላት የታቀደ ሴራ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

ጉዞውን ያመቻቸው “ጦርነት ይቁም፣ አገዛዝ ያብቃ፣ሰላም ይምጣ” በሚል በቅርቡ የተሰራጨውን የአየር ላይ ትዕይነት ሕዝብ ያዘጋጁት አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አስመራ ከርመው የነበሩት አምባሳደር በርሃነ ገብረክርስቶስ፣ አቶ ነዓልም ዘለቀ እንደሆኑ ዜናውን ያጋሩት ወገኖች አመልክተዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

አቶ ልደቱ በ1987 ወቅት ትህነግን ሲሳደቡና ሲያወግዙ ቆይተው እንደተነቃባቸው በማስታወስ አሁንም ሻዕቢያን ሲያወግዙ የነበሩት አቶ ልደቱ በመጨረሻ የማንን አጀንዳ እያቀጣጠሉ እንደሆነ ይፋ መሆኑን አመልክተዋል።

ዓላማውና ተሳታፊዎቹ በተጭበረበር መልኩ ተነግሯቸው በቀጥታ ስርጭቱ ከተሳተፉ መካከል ለኢትዮሪቬው እንደጠቆሙት ሰባት የኦሮሞ ምሁራን ወደ አስመራ ካቀኑ በሁዋላ የሚዲያ ዘመቻ ይጀመራል።

በዘመቻውም አቶ ኢሳያስ ሆነ ብለው፣ ተዘጋጅተውበት፣ በጽሁፍ ባቀረቡት ኦሮሞን በጅምላ ፈርጆ የማስፈጀት ትርክት የተነሳውን ተቃውሞ አቅጣጫ የሚያስቀይሩ ፕሮፓጋንዳ በተደጋጋሚ ይሰራል። ይህ የሚዲያ ዘመቻ በእነ ልደቱና ጃዋር መሐመድ አስተባባሪነት እንደሚሰራ ዜናውን ያጋሩን አመልክተዋል።

ወደ አስመራ እንዲሄዱ ከሚመለመሉት መካከል ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አንዱ መሆናቸው ሲታወቅ ስድስቱ ለግዜው ስማቸው አልተገለጸም። ሕዝቅዔል ገቢሳ ምልመላውን እንደሚያከናውኑም ተጠቁሟል።

አቶ ኢሳያስ “ኦሮሙማን” ርዕዮት አድርገው በሰሜንችና ደቡቦች ከፍለው ኢትዮጵያዊያንን በመከፋፈል ለማቀጣጠል አስበው የተናገሩትን ፌደራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙላቱገመቹና ከሰማኒያ በላይ የኦሮሞ ምሁራንና ባለሙያዎች እንዲሁም በርካታ ዜጎች ተቃውመው ነበር። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ከምሁራኑ ጋር የተቃውሞ ፊርማቸውን ያኖሩ ቢሆንም አቶ ሙላቱ በፓርቲያቸው ስም በሪፖርተር ቲዩብ ላይ ቀርበው የሰነዘሩትን የከረረ ተቃውሞ አስመክቶ ፕሮፌሰር መረራን አነጋግረው ነበር።

ታማኝ የኦፌኮ ውስጥ አዋቂ ለኢትዮሪቪው እንዳሉት “አቶ ሙላቱ እንዴት ኢሳያስ አፉወርቂን በዛ ደረጃ ይቃወማሉ፣ ይተቻሉ” በማለት ሕዝቅዔል መረራን ወቅሰዋል። መረራ “አንተም በመንገድህ፣ እኛም በሚመስለን” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ሙላቱ ለአቶ ኢሳያስ ንግግር የሰጡት አስተያየት ሻዕቢያ መቼም ቢሆን የኢትዮጵያ ወዳጅ ሊሆን እንደማይችል፣ ከተፈጠረ ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ ተላት ሲያደራጅና ሲያስታጥቅ የኖረ፣ የመንግስትነት ቅርጽ የሌለው ወዘተ በማለት ነበር። በርካታ ማሳያዎችን አንስተው ክፉኛ ፕሬዚዳንቱን የተቹት አቶ ሙላቱ ” ሰውየው ኢትዮጵያን ከማወክና ከማተራመስ የዘለለ አጀንዳ ኖሯቸው አያውቅም” በሚል እንደምታ ነበር አስተያየታቸውን የቋጩት።

“ሻዕቢያን ልክ እንደ አቶ ልደቱ ሁሉ ሲዘልፍ የነበረው የርዕዮት ቲዩቡ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ከአቶ ልደቱና ጃዋር ጋር በመሆን ሻዕቢያን በአቶ ስብሃት በኩል ወክሎ፣ ጄኖሳይደር ሲለው የነበረውን ጃዋርን አዝሎ የሻዕቢያን እጀንዳ ሲያራምድ መታየቱ በረከት ነው፤ አሰላለፉን ይፋ አድርጎታል” ያሉት የዜናው ሰዎች፣ ሰባቱ የኦሮሞ ልሂቃን አስመራ ደርሰው ሲመለሱ መድረክ ከሚሰጡዋቸው ሚዲያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ከዜናው ባለቤቶች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ሻዕቢያ መቶ ሺህ ዶላሮች ለዚህና ተመሳሳይ የፕሮፓጋንዳ ስራ መመደቡን የገለጹት የመጀመሪያው የአየር ላይ ትዕይንት ተሳታፊ ከሆኑት መካከል አንዱ ናቸው። እኚሁ ሰው እንዳሉት “ጦርነት ይቁም፣ አገዛዝ ያብቃ፣ ሰላም ይስፈን” በሚል የተዘጋጀው ፕሮግራም ዓላማው ሌላ ነው። የኦሮሞ ልሂቃኖቹም የተፈለጉት ለዚሁ ነው።

“የኦሮሞው መንግስት በሰላማዊ መንገድ ቢነገረው፣ ቢለመን፣ በውይይትና ንግግር ቢጋበዝ፣ የሰላም አማራጭን ሁሉ በመዝጋቱ ትግሉን ወደ እንቢተኛነት እንድናሸጋግር አስገድዶን ጦርነት ገብተናል” በሚል የሕዝብን ስሜት ለመሳብ እንደሆነ በውይይቱ ተሳስተው የተሳተፉ መሆናቸውን ያመለከቱ አስታውቀዋል።

እነዚሁ ክፍሎች እንዳሉት አቶ ልደቱ፣ ቴዎድሮስ ጸጋዬ፣ አቶ ጃዋር የብሄርሰብ ድርጅቶችና በወፍ በረር አንዳንድ ፓርቲዎች በውይይቱ ወቅት እንዲሳተፉ የተደርገበት ምክንያትም አካሄዱ ሁሉን አቀፍ እንዲመስል ነው። ኢሳያስን ወክለው በወቅቱ ተናጋሪ የነበሩት አቶ ስብሃት መጋበዛቸው ከጉዳይ ጀርባ ሻዕቢያ እንዳለ ግልጽ የሚያደርግ ሲሆን “የሰላም ምልጃ” በተባለበት መድረክ እሳቸውም ሆኑ ጠብ መንጃ ያነሱ ኃይላት ተወካዮች እንደሚገኙ የሚያቁት አዘጋጆቹ ብቻ እንደነበሩ ተመልክቷል።

በቅርቡ በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት ለማቀጣጠል በሶማሌ የኦጋዴን ነጻ አውጪን እና ሂጎታ የተባለውን የፈረሰ ንቅናቄ በማንቀሳቀስ፣ በደቡብ ኤጄቶ በጸጥታ መዋቅር ውስጥ በመግባት ዳግም ለማደረጃት፣ በኦሮሚያ የጃል መሮን ኃይል፣ በአማራ ክልል ያሉትን የፋኖ አድረጃጀቶች ወደ አንድ በማምጣት ለማቀናጀት ጥረት ሲደረግ መቆየቱ አይዘነጋም።

“ልሂቃኑ አስመራ የሚሄዱበት ዕቅድ በሚስጢር የሚወጠን ጉዳይ በመኖሩ እንጂ የአፍ ወለምታ ብቻ ቢሆን በመግለጫ ወይም በቃል ይቅርታ ማለት ያቻል ነበር” ያሉት እነዚሁ ወገኖች ” በዚህ ጉዳይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሁሉ የወጡበትን ሕዝብ ለማስጨረስ ከመማማል ጀምሮ በአገር ላይ ክህደት መፈጸም በመሆኑ በጥንቃቄ እንከታተለዋለን” ብለዋል። ኦነግ ሁለት አስርት ዓመታት ኤርትራ ውስጥ በቆየበት ወቅት አንድ ሆኖ ገብቶ አምስት ቦታ ተከፍሎ ከመውጣት የዘለለ ያተረፈው ነገር ባለመኖሩ ክዚያው እንዲማሩም አሳስበዋል።

“ይህ ከሆነ በሁዋላ ውጤቱ ሲገመገም ኦሮሚያ ላይ የተፈለገው ውጤት አልመጣም። አማራ ክልልም በተጠበቀው ፍጥነት ከትሀንግ ጋር ተናቦ የመስራቱ ጉዳይ ሰንካ ገጥሞታል። በዋናነት በሁለቱ ክልሎች የታሰበው ባለመሆኑ የኦሮሞ ልሂቃኑ ሊቀቡ ወደ አስመራ ይሄዳሉ” ሲሉ የዜናው ባለቤቶች ገልጸዋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ተዓምረኛው ቪሽቫሽ ኩማር – ከአሰቃቂው የአውሮፕላን አደጋ በሕይወት የወጣው ብቸኛ ነብስ
ኢራን ቁልፍ ሰዎቿን ያጣችበትን ጥቃት ለመበቀል እየሞክረች ነው፤ እስራኤል “አላቆምም” ብላለች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2