Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  የካፒታል ገበያ አዋጅ የያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች
law

የካፒታል ገበያ አዋጅ የያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች

Ethioreview newsEthioreview news—June 7, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

መግቢያ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ስር ነቀል የሚባል ለውጥ ለማምጣት ያለመ ሕግ ነው። ይህ አዋጅ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚደግፍ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ እንዲቋቋምና እንዲዳብር የሚያስችሉ መሠረታዊ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን ዋና ዋና ዓላማዎቹም የካፒታል ፍሰትን ማሳለጥ፣ የቁጠባና የኢንቨስትመንት ባህልን ማሳደግ፣ እንዲሁም ቀልጣፋና ፍትሀዊ የገበያ ሥርዓት መፍጠር ናቸው። በዚህ አጭር ጽሁፍ አዋጁ የያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።

የካፒታል ገበያ ምንነት
በአዋጁ አንቀጽ 2(5) እንደሰፈረው የካፒታል ገበያ ማለት እንደ አክሲዮን፣ ቦንድ፣ ተዛማጅ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ወይም እነዚህን የመሰሉ የተለያዩ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት የሚደረግበት ገበያ ነው።

የካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራ በኢትዮጵያ

የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ያለውን ታሪካዊ ዳራ ስንመለከት በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት በ1889 ዓ.ም የኢትዮ ጂቡቲን የምድር ባቡር ለመዘርጋት የ40 ሚሊዮን ፍራንክ አክሲዮን በፈረንሳይ አገር መሸጡን በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቧል። በአጼ ኃይለ-ሥላሴ ዘመን ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለማቋቋም ሙከራዎች አድርጋ ነበር፤ በ1948 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቄራዎች /Ethiopian Abattoirs/ የተባለው ድርጅት የመጀመሪያውን አክሲዮን ለአደባባይ ምዝገባ አውጥቶ ነበር፤ይህ በሀገሪቱ የፋይናንስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።በ1957 ዓ.ም የአዲስ አበባ የአክሲዮን ንግድ ማህበር /Addis Ababa Share Dealing Group/ የተቋቋመ ሲሆን ይህ ቡድን ብሔራዊ ባንክን እና ሌሎች ግለሰቦችን በማቀፍ የዋስትና ገበያን ለመቆጣጠር ዓላማ አድርጎ ነበር። ምንም እንኳን እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም ጠንካራ የሕግ ማዕቀፎች እና የቁጥጥር አካላት ባለመኖራቸው የተደራጀ የአክሲዮን ገበያ ሊኖር አልቻለም። ግብይቶች የሚካሄዱት በንግድ ባንክ በኩል በከፊል መደበኛ ባልሆነ መንገድ ነበር።

More stories

ግማሽ ሚሊየን ብር በጥሬው ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

February 1, 2022

ዐቃቤ ህግ በቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የክስ መዝገብ ሌሎች ድርጅቶችን አካቶ ለመቅረብ ጠየቀ

July 7, 2023

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመው የሚኒስቴሮች ግብረ-ሀይል ስራውን በይፋ ጀምሯል

November 29, 2021

ሰው በማገት ወንጀል የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች 22 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው

February 16, 2022

አዋጁ የያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል ፡-
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (Ethiopian Capital Market Authority) መቋቋም አዋጁ በአንቀጽ 3(1) ስር የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠር፣ የሚመራና የሚያስተዳድር ራሱን የቻለ ህጋዊ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግስት ተቋም ሆኖ እንደተቋቋመ ይደነግጋል።

የባለስልጣኑ ዓላማዎች በአዋጁ አንቀጽ 5 ስር የተዘረዘሩ ሲሆን እነዚህም፡-

  • ኢንቨስተሮችን መጠበቅ ወይም ከለላ መስጠት፣
  • ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የማውጣትና የግብት ስርዓት ፍትሀዊ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽነት በሰፈነበት ሁኔታ የሚካሄድበትን የካፒታል ገበያ ስነ ምህዳር እንዲኖር ማድረግ፣
  • መዋቅራዊ የአደጋ ስጋቶችን በመቀነስ የካፒታል ገበያው ተአማኒ እንዲሆን ማድረግ፣
  • የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንቶችን የሚያበረታታ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የካፒታል ገበያን ማስፋፋት ናቸው።

የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት ፡- ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚያስችሉ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 6 ስር ተዘርዝረው እናገኛቸዋለን፤ እነዚህም የገበያ ተዋናዮችን መመዝገብ፣ ከምዝገባ መሰረዝና ፈቃድ መስጠት በአንቀጽ 6(1)፣ 6(18))፣ የገበያውን ህግና ደንብ ማውጣትና ማስከበር በአንቀጽ 6(16)፣ የኢንቨስተሮችን ጥቅም ማስጠበቅ በአንቀጽ 6(27))፣ እንዲሁም የገበያውን ግልጽነትና ቀልጣፋነት ማረጋገጥ በአንቀጽ 6(17))፣ ፈቃድ የተሰጠው ሰው የሚያከናውነው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግብይት ወይም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ የግብይት መድረኮች የሚካሄድበትን አግባብ መቆጣጠር በአንቀጽ 6(15)) ስር ሰፍረው የምናገኛቸው ናቸው።

የካፒታል ገበያ ተዋናዮችና ፈቃድ አሰጣጥ

አዋጁ በካፒታል ገበያው ውስጥ የሚሳተፉ የተለያዩ ተዋናዮችን ይለያል፤ በአዋጁ አንቀጽ 2(6) እንደተደነገገው የካፒታል ገበያ ተዋናዮች ማለት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጪዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ፣ ተገቢነት ያላቸውን ውሎች ያደረጉ ብቁ የሆኑ ተጓዳኝ ወገኖች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያዎችን እንደሚያካትት ይደነግጋል። እነዚህ ተዋናዮች በገበያው ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከባለስልጣኑ ፈቃድ የማግኘት ግዴታ አለባቸው (አንቀጽ 6(1))። ፈቃድ አሰጣጥን በተመለከተ ዝርዝር መስፈርቶች በአዋጁ አንቀጽ 39 ስር የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አስቀማጭና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ ፈቃድ አሰጣጥ የሚገልጽ ሲሆን በአንቀጽ 55 እስከ 58 ደግሞ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሚሰጥበትን መስፈርት ይደነግጋል። ለሁለቱም አካላት የጋራ የሆኑ መስፈርቶችን ስንመለከት ዝቅተኛ የካፒታል መጠን፣ የተገቢነት መስፈርት፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ መልካም ስም ወዘተ… ይገኙበታል፤

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ/Security/ ምዝገባና ግብይት

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ምዝገባ እና ግብይትን ከማየታችን በፊት ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ምንድን ነው የሚለዉን ማየቱ ስለጽንሰ ሃሳቡ ለመረዳት ያግዘናል። በአዋጁ የትርጉም ክፍል በአንቀጽ 2(62) በስፋት እንደቀረበው ሰነደ መዋዕለ ንዋይ /security/ ማለት በማንኛውም ህጋዊ መልክ ያለ በገንዘባዊ ግብይት የድርሻ ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ እና በባለስልጣኑ ፈቃድ የሚተላለፍ ሆኖ የሚከተሉትን ማለትም፡-

  • በኩባንያ ካፒታል ውስጥ የወጡ ወይም የሚወጡ አክሲዮኖችን፣
  • በኩባንያ የወጡ ወይም የሚወጡ ባለዕዳነትን የሚፈጥሩ ወይም የሚያረጋግጡ ማናቸውም ሰነዶችን፣
  • ብድሮች፣ ቦንዶችና ሌሎች ወደ ኩባንያ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ሰነዶችን፣
  • ሁሉም በመንግስት እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች የወጡና ለግብይት የሚውሉ የህዝብ የብድር ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን እንደሚያካትት ተመላክቷል።
    በሌላ በኩል ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ፣ የሀዋላ ወረቀት፣ የንግድ ወረቀቶች፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ጥሬ ገንዘብ ማስተላለፍ እና በባንኮች መካከል እርስ በርስ ብቻ የሚተላለፉ ሰነዶችን፣ የመድን ፖሊሲዎችን እና ለተጠቃሚዎች ከጡረታ ክፍያዎች የሚመነጩ መብቶችን እንደማያካትት በዚሁ ድንጋጌ ስር ተመላክቷል። ከዚህ በመቀጠል የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ምዝገባ እና ግብይት ሂደትን እንመለከታለን። ይኸዉም፡-
    * ለህዝብ የሚሸጥ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ለሽያጭ ወይም ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በባለስልጣኑ መመዝገብ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 75(1) ስር ተደንግጓል።
    * የሰነደ መዋዕለ ንዋይ አውጭ ማንኛውንም ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ለህዝብ ለሽያጭ ከማቅረቡ በፊት ትክክለኛ፣ ግልጽ እና የተሟላ የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በባለስልጣኑ ማስፀደቅ እንዳለበት በአዋጅ አንቀጽ 76(1) እና (2) ስር ተደንግጎ እናገኘዋለን ።
    * የገበያውን ግልጽነት ለማረጋገጥ ኩባንያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ለባለሀብቶችና ለሕዝብ ይፋ የማድረግ ግዴታ ይጣልባቸዋል።
    የኢንቨስተሮች ጥበቃ
    * አዋጁ የኢንቨስተሮችን ጥቅም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። ይህም ከታች በተጠቀሰው መልኩ ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶችን በመደንገግ ይገለፃል።
    * የገበያ ማጭበርበርን /Fraudulent transaction/ በአንቀጽ 98፣ የውስጥ አዋቂ ንግድን (Insider Trading) በአንቀጽ 95 እና ሌሎች ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ድንጋጌዎች ተካተዋል።
  • ቅጣትና አስተዳደራዊ እርምጃዎች
  • አዋጁንና በአዋጁ መሠረት የሚወጡ ደንቦችን የሚተላለፉ አካላት ላይ የሚጣሉ የእስራት እና የገንዘብ ቅጣቶች በአዋጁ አንቀጽ 106 ስር እና ሌሎች አስተዳደራዊ እርምጃዎች በአዋጁ አንቀጽ 107 ስር ተደንግገው እናገኛቸዋለን። ይህም የሕግ ተገዥነትን ለማረጋገጥና የገበያውን ሥርዓት ለማስጠበቅ ያግዛል። ከቅጣቶች መካከል ለምሳሌ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ያቋቋመ ከ100,000.00 እስከ 150,000.00 የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በአንቀጽ 106/2/ ስር ተደንግጎ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ማንኛውም ሰው ፈቃድ በሌለው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ የሌለው መሆኑን እያወቀ የተገበያየ እንደሆነ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ቅጣት እንደሚወሰንበት በአዋጁ አንቀጽ 106/3/ ስር ሰፍሮ እናገኘዋለን። ከአስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል በአንቀጽ 107 ከተመለከተው ጠቅላላ እርምጃ ባሻገር በአንቀጽ 33 ስር የተመላከተው በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች ላይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የሚዘረዝረው ሲሆን እነዚህም፡-
  •  ዋጋን ማመላከት እንዳይችል የሚያደርግ ከፍተኛ የግብይት መስተጓጎል ሲከሰት
  •  ተጨባጭ ወይም ተገማች የሆነ ገበያን የማዛባት ተግባር ሲፈጸም
  •  ለህዝብ ጥቅም ሲባል ወይም ኢንቨስተሮችን ለመጠበቅ ጠቃሚ ወይም አስፈላጊ ነው ብሎ ባለስልጣኑ ሲያምን ባለስልጣኑ በጽሁፍ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለተወሰነ ጊዜ ገበያው እንዲዘጋ ሊወስን ይችላል፣ ይህም በአንቀጽ 33/1/ ስር ሰፍሮ እናገኘዋለን።
  • በተጨማሪም በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ስር የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ባለስልጣኑ የገበያ ፈቃዱን ለተወሰነ ጊዜ ወይም አንድ ተግባር እስከሚፈጸም ድረስ ሊያግደው እንደሚችል ተመላክቷል። ይኸውም፡-
  •  ከተሰጠው የስራ ወሰን ወይም ከተፈቀደለት የስራ ዘርፍ ውጪ የሆነ ተግባር ከፈጸመ
  •  ከተሰጠው ፈቃድ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ቅድመ ሁኔታዎች ከጣሰ ወይም ካላከበረ
  •  ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ከሰጠ የሚሉት ናቸው።

የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት መቋቋም

አዋጁ በአንቀጽ 64 ስር የካፒታል ገበያ አስተዳዳራዊ ፍርድ ቤት መቋቋሙን ይደነግጋል። በአዋጁ አንቀጽ 65 ስር እንደተመላከተው አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በባለስልጣኑ ወይም የባለስልጣኑን ስልጣንና ተግባር በሚያስፈጽም ሰው በተላለፈ ውሳኔ ላይ የቀረበን ይግባኝ የመስማትና የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ከተመለከተ በኋላ፡-

  • የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ እንዳለ ሊያፀናው፣ ሊያሻሽለው ወይም ሊሽረው፣
  • ትክክለኛ ነው ብሎ በወሰነው አቅጣጫ ጉዳዩን እንደገና እንዲያየው ወደ ባለስልጣኑ ሊመልሰዉ ወይም
  • ትክክለኛ ነው ብሎ ያመነውን ማናቸውም ትዕዛዝ ሊሰጥ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 73(5) ስር ሰፍሮ እናገኘዋለን።

ሌላው በአዋጁ የተካተተው ነጥብ በአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ አካል ውሳኔዉን ባወቀ በ30 /ሰላሳ/ ቀናት ውስጥ በህግ ጉዳይ ላይ ብቻ ይግባኙን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 74 ስር ተደንግጎ እናገኘዋለን።

ማጠቃለያ
የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የካፒታል ገበያ እንዲፈጠር፣ እንዲያድግና እንዲጠናከር የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ በማቅረብ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠን ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። አዋጁ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ለመሳብ፣ የንግድ ድርጅቶች የፋይናንስ አማራጮችን እንዲያገኙ ለማድረግና የሀብት ክፍፍልን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን እንደሚያስችል ታምኖበት በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። በመሆኑም ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ለአዋጁ መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል።

የፍትሕ ሚኒስቴርን


law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ
የባህር በር አልባ የተደረግንበት ውሳኔ ኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመ ልዩ ግፍ መሆኑን አብይ አሕመድ ለህዝብ አስታወቁ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2