Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  “ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ
POLITICS

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

Ethioreview newsEthioreview news—June 7, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

እነ አቶ ልደቱ አያሌው “ጦርነት ይቁም” በሚል ባዘጋጁት የአየር ላይ ትዕይንት ዋና ተሳታፊ የሆነውና ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ /ትህነግ እያለ የሚጠራው ቡድን በሸራሮ ደደቢት፣ በደርባ አባይ፣ በአዲ ገብሩና በዛና በኩል ሰራዊት ማስጠጋቱን በመጥቀስ የጠለምት አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ።

ከዝግጅት ባለፈም በጠለምት በርሃ አርማ ደጋ ደልዲማና መሰል ቦታዎች የታጠቁ ሀይሎች እንዲገቡና በህዝባችን ላይ እገታ፣ ስርቆት፣ ግድያንና ድብደባ እንዲፈጽሙበት ስምሪት የተሰጠ መሆኑን፣ ይህንንም ከተባዳይ ወገኖች መረጃ ማሰባሰቡን የገለጸው ኮሚቴው አድራጎቱ ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረበት ባሰራጨው መግለጫ አመልክቷል።

መግለጫው ባያነሳውም ለአማራ ሕዝብ ህልውና እንደሚታገሉ የሚገልጹ የፋኖ አደረጃጀቶች አቋም እያነጋገረ ነው። ትህነግ ጠለምትን ብቻ ሳይሆን ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራን የማስመለስ ዕቅድ እንዳለው እየታወቀ በአማራ ሕዝብ ስም ብረት ያነሱ በምን ውል አብረው ለትህነግ ጋር ለመስራት እንደተስማሙ ገሃድ የተነገረ ነገር የለም። ትህነግም ለአማራ መብት እንደሚታገሉ ለሚናገሩት አቋሙን ስለመቀየሩ በግልጽ ያስታወቀው ነገር የለም። ይህን አስመልክቶ ጥብቅ ጥያቄ የሚቀርበበትን ህብረት አስመልክቶ በተለይ የጎጃም ፋኖ በገሃድ አቋሙን አለማስታወቁ ቅሬታና መከፋፈልን እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል። ገለልተኞች በህዝበ ውሳኔ ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ደጋግመው ሃሳብ እንደሚያቀርቡ ይታወሳል። ሙሉ መግለጫውን ከስር ያንብቡ።

ጦረኛው እና ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ለዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት አጥብቀን እንቃወማለን፤ ለዘላቂ ሰላም እንታገላለን !!

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

(ከጠለምት አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳዩች ላይ የተሰጠ መግለጫ)

የጠለምት አማራ ሕዝብ ለሦስት አስርት ዓመታት የሚሻገር የመከራ ጊዜ፣ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ተጭኖበት መቆየቱ መላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የሚያውቁት እውነታ ነው፡፡

የ1987ቱ ሕገ-መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በኃይልና በጭፍለቃ ተይዘን ከእናት ግዛታችን ስሜን በጌምድር አማራ ተነጥለን ለመኖር ተገደን ነበር፡፡ በዚያ የሕወሓት አገዛዝ ዘመን፣ አማራዊ ማንነታችን የጥቃት ምንጭ ሆኖብን ዛሬ ይቅር ብንል እንኳ መቼውንም ልንዘነጋው የማይቻል በደል በትሕነግ ተፈጽሞብናል፡፡

ይህም ሆኖ ከበርካታ የሕዝብ ትግልና ውጣ ውረድ በኋላ እዚህኛው የትግል ምዕራፍ ላይ ብንደርሰም አሁንም ግልጽና ቀጥተኛውን ጥያቄችንን ወደኋላ የሚመልስ ውስብስብ መሰናክል እያጋጠመን በሰላማዊ መንገድ መታገላችንን ቀጥለናል፡፡

የጠለምት አማራ ሕዝብ፣ በጎረቤታችን ትግራይ ያለውን ጦረኛ እንቅስቃሴ በአንክሮ በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ አብሮነት፣ እንደተወሳኝ ጎረቤት በትግራይ ያለው ሁኔታ ያሳስበናል፡፡ በተለይም ሁኔታው እንደጠለምት የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የሕዝባችንን የዘመናት ሕዝባዊ የትግል ጥያቄ መሠረታዊ ጥቅሞቹን የሚነካ ከመሆን አልፎ ህልውናውን ለአደጋ የሚጥል ነው፡፡

በተለይም ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ለዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያደርገው ዝግጅት እንደጠለምት አማራ ብቻ ሳይሆን አጠቃለይ እንደ አማራ ሕዝብና እንደ ኢትዮጵያ ሁኔታው እጅግ ያሳስበናል፤ የሕገወጥ ቡድኑን አሁናዊ የጦረኝነት እንቅስቃሴዎችም አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሕግና አዋጅ ጠቅሶ ከግንቦት 6/2017 ጀምሮ ከፓርቲነት የሰረዘው ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን የፖለቲካና የታጣቂ ስምሪቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በክትትላችን በሸራሮ ደደቢት፣ በደርባ አባይ፣ በአዲ ገብሩና በዛና በኩል ሰራዊት አስጠግቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል፡፡

በተጨማሪም በጠለምት በርሃ አርማ ደጋ ደልዲማና መሰል ቦታዎች የታጠቁ ሀይሎች እንዲገቡና በህዝባችን ላይ እገታ፣ ስርቆት፣ ግድያንና ድብደባ እንዲፈጽሙበት ስምሪት የተሰጠ መሆኑን፣ ይህንንም ከተባዳይ ወገኖቻችን በሳባሰብነው መረጃ አረጋግጠናል፡፡

በተለይም በምዝክር፣ አምበል (ጻዕዳ ቀርኒ)፣ ማይተክሊት፣ ውህደትና እምባማድሬ በተሰኑ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ አከባቢዎች በሙሉ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሕወሓት የሚረዱ የቡድኑ ህገወጥ ታጣቂዎች የአካባቢው ስጋት ሆነዋል፡፡ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል እንደሚፈጸምም የክትትል መረጃ ያሳያሉ፡፡ በእነዚህ የጠለምት አማራ ግዛቶች ላይ ይኖር የነበረው ነባሩ ባለርስት አማራ ላይ እየደረሰ ባለው ዳግም የተነሳ እየተፈናቀለብን ይገኛል፡፡ እኛ እንደ ኢትዮጵያዊ አብሮነት ተፈናቃይ ተቀብለን ባለበት ሁኔታ ባለርስቱ አማራ ግን ዳግም ከቀየው እየተፈናቀለ ይገኛል።

በአጠቃላይ ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን በወታደራዊ፣ መረጃና የፖለቲካ ኃይሉ የየራሱን ስምሪት ወስዶ እየሰራ በመሆኑ፣ ይህም ዳግም ወደ ደም አፋሳሻ ጦርነት የመግባት፣ የጥፋት ስምሪት የቅድመ ዝግጅት አካል እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡

ስለሆነም ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ለዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት አጥብቀን እየተቃወምን፤ ለዘላቂ ሰላም እንደሚታገል ሰላማዊ የማንነት ታጋይ እንደጠለምት አማራ ሕዝብ ያለንበት ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ የሚከተለውን ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡-

  • ሕወሓት ፕሪቶሪያ ላይ ከፈረመው ባለ 15 አንቀፅ ሰነድ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታና ተዋጊዎቹ በሙሉ ወደ ተሃድሶ (ማሰልጠኛ) ካምፕ እንደሚገቡ ስምምነቱ አስገዳጅ ቢሆንም ይህ በአግባቡ አልተፈፀመም፡፡ አሁንም ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚህም አልፎ ሰራዊት እያስጠጋ፤ ተከዜን አሻግሮ ባስገባቸው ሕገወጥ ታጣቂዎቹ ሕዝብ ላይ ማንነት ተኮር በደል እየፈጸመ ይገኛል፡፡
    ይህም የስምምነቱን መሠረታዊ ዓላማ ግጭትን በዘላቂነት ማቆም የሚለውን ፍሬ ነገር በተጨባጭ የሚቃረን ጦረኝነት ነው፡፡ በመሆኑም በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት፤ ሰራዊት መበተንና ከማኀበረሰቡ ጋር መልሶ የማዋሃድ (DDR) ዕቅድ ያለአንዳች መጓተት እንዲፈጸም እንጠይቃለን፡፡
  • የሕወሓት ወታደራዊ ስልጠናዎች መቀጠል፣ የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ ለሌላ ዙር የጦር ወረራ የሚያደርገው ዝግጁነት ነው፡፡ ድርጅቱን ከዚህ መሰል የዳግም ጥፋት መንገድ የማስቆም ስራ በፌዴራል መንግሥቱ በኩል እንቅስቃሴዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ሁኔታዎች ሊያመጡ በሚችሉት አደጋ ልክ መፍትሔ ካልተሰጠ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የከፋ አደጋ ያመጣል የሚል ስጋት አለን፡፡ ቡድኑ ዳግም ለደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያደረገው ዝግጅት ለኢትዮጵያ ሐገረ-መንግሥት አደጋ፣ ለአካባቢውም ጠንቅ በመሆኑ ጦረኛ እንቅስቃሴዎቹን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡
  • የጠለምት አማራ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን በሚጨፈልቅ መልኩ ወደ ዳግም የባርነት አገዛዝ ለመውሰድ ሁኔታዎችን የማወሳሰብ፣ ሴራ፣ ሸፍጦች አሁንም ቀጥለዋል፡፡ በተለይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያድ) ስም የሚፈጸሙ ተግባራት አሳስበውናል፡፡ በአካባቢያችን የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ መያዶች በወረቀት ከሰፈረው ከምስረታ ዓላማቸው በሚቃረን መልኩ የፖለቲካ ዓላማ ማራመጃ ሆነው መታየት ላይ ናቸው፡፡  ይህም የዘመናት የማንነት ትግላችን እያወሳሰበው በመሆኑ የፌደራል መንግሥት የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን በሚመለከተው አካል እንዲፈጸምና እንዲታረሙ እንጠይቃለን፡፡ አካባቢው ሰላም እንዳይሆን እያባባሱ የሚገኙ መያዶችን ማሳያ ከተፈለገ በዝርዝር እንደምናቀርብ እናሳውቃለን!
  • የፌደራልና የክልል መንግስት ከዚህ በፊት በተስማሙት መሠረት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ሲባል በትግራይና በአማራ ክልል ‹‹አወዛጋቢ›› ብሎ ከጠራቸው አንዱ የጠለምት አማራ ሕዝብ የሚኖርበት ሦስት ወረዳዎችን ነው፡፡ ችግሩ በዘላቂነት መፈታት አለበት በተባለበት መንገድ እስከሚፈታ ድረስ፣ በሦስቱም ወረዳ የሚገኘው ሕዝብ ጊዜዊ ሕዝባዊ አስተዳደር በማዋቀር፣ የአካባቢው የመልማትና የፍትህ ጥያቄ እንዲቀላጠፍ መንግስትም አምኖ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ ይህም ሆኖ የጊዜዊ ሕዝባዊ አስተዳደር ምስረታው እስካሁን ተፈጻሚ አልሆነም፡፡ በእኛ በእኩል በጠለምት ሦስቱም ወረዳዎች ውስጥ፡- እውነተኛ ተፈናቃይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች በቁጥር ድርሻቸው ልክ የሚሳተፉበት ሕዝባዊ አስተዳደር እንዲቋቋምና ከሕዝባችን የማንነትና ወሰን ጥያቄ ጎን ለጎን የመልማት ጥያቄዎቹ፣ በኢትዮጵያዊ ዜግነቱ ሊያገኘው የሚገባ የበጀትና የልማት ማካካሻዎች እንዲሰጡት በድጋሚ እንጠይቃለን፡፡
  • በፕሪቶርያ ስምምነት መሠረት ተፈናቃይ ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ይታወቃል በምላሹ ግን ትምህርት ባለመከፈቱ የጠለምት አማራ ህጻናት ትምህርት ፍለጋ ከቀያቸው ተፈናቅለውብናል። የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ፣ አንቀጽ 26  ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው (The Right to Access to Education) በሚለው የሰብዓዊ መብት ድንጋጌና ሕገ-መንግሥታዊ መብት የመማር ዕድሉ ለልጆቻችን ሊፈጠርላቸው ይገባል፡፡ በተመሳሳይ የመልማት፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ በጠቅላላ የመሠረተ ልማት መብቶቻችን እንደ ማንኛውም የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ሊፈቀድልን የሚገባ በመሆኑ በቀጣይ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት እንዲያዝልን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።

በሕወሓት በኩል ጠለምትን በተመለከተ ይቀርቡ የነበሩ የጊዜዊ ሕዝባዊ አስተዳደር ምስረታው የ‹‹ይራዘምልን ጥያቄ›› ዓላማው ሂደቱን የማወሳሰብ ሴራ ወደ ኃይል ለማምራት የሚደረግ ጊዜ የመግዛት ድብቅ  ፍላጎት ስለመሆኑ፣ አሁናዊ ግልጽ የጦርነት ዝግጅታቸው አስረጅ ምሳሌ ነው፡፡

በመሆኑም አማራነታችን የህልውና አደጋ ላይ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ዓለማቀፉ ማኀበረሰብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን፡፡
በመጨረሻም፣ የጠለምት አማራ ሕዝብ ለዘመናት ባሳለፈው የማንነት ትግል ነጻነት በነጻ እንደማይገኝ ከተግባር የተማረው እውነታ ነው፡፡ ጦረኛውና ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን የተገንጣይነት ስሜቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጨመረበት በዚህ ጊዜ የትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እንቅስቃሴውን እውን ለማድረግ ተከዜን ማዕከሉ ማድረግ የፖለቲካ አልፋና ኦሜጋው ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የጠለምት አልፎም ወልቃይት-ጠገዴን አማራ ዳግም በመውረር ሊያጠፋን ይፈልጋል፡፡ መቼውንም ቢሆን ሕዝባችን ይህ እንዲሆን አይፈቅድም፡፡

ትግላችን የማንነትና የወሰን ብቻ ሳይሆን ከዚህ ከፍ ባለ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ አንድነትን መጠበቅ በመሆኑ መላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት አደጋ የሆነውን ጦረኛውና ሕገወጡን ሕወሓት የጦርነት ዝግጅት ለመቃወም፤ ለዘላቂ ሰላምና የአገር አንድነት ከጎናችን በእንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ

ግንቦት 26/2017 ዓ.ም ማይጠምሪ -ጎንደር- ኢትዮጵያ


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ዳውድ፣ መረራና ጃልመሮ ወደ ብልጽግና በሚደረግ ፍልሰት ሳቢያ እየተመናመኑ ነው፤ “ጃዋር ለኦፌኮ ስጋት ሆኗል”
የካፒታል ገበያ አዋጅ የያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2