የትግራይ መወጠርና የሕዝቡ ጭንቀት አሁን አሁን ሊደበቅ ከማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው። ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከኮር በላይ ናቸው የተባሉ ወታደራዊ አዛዦች በቀጥታ ጣልቃ ገብተው የሽግግር አስተፋደሩ እንዲፈስርስ መወሰናቸውን ተከትሎ የተጀመረው ልዩነት ነው ዛሬ ከፍተኛ ስጋት የሆነው። በተለይም ሻዕቢያ በይፋ በትግራይ ጦሩን እያሰማራ መሆኑን ተክትሎ፤
እነ ዶክተር ደብርጽዮን የሚመሩት የትህነግ አንድ ስንጣቂ ከተጠቀሱት መኮንኖች ጋር ሆኖ በክልሉ ያለውን አዲሱን አስተዳደር ማስወገዱ ብቻ ሳይሆን ከሸዕቢያ ጋር የመሰረተው ኢሕገመንግስታዊ ግንኙነት ስጋቱን ካባሱት ጉዳዮች መካከል ዋንኛው ነው።
መኖር ከልጆችህ፣ከወንድሞችህና ከቤተሰብህ ጋር ነው፤ ስለ ተሰዋችሁልን እየኖርን ነው የሚል አባባል ስህተት ነው። ወንድሞችህና ልጆችህ ስለተሰዉ የምትኖር ከመሰለህ በፕሮፓጋንዳ ተታልሃል ማለት ነው። ወንድምህ ከሞተ አጋዥ ነው የምታጣው። ልጅህ የጥይት እርሳስ እራት ከሆነ የሚጦርህ ታጣለህ፣ታዝናለህ፣የመኖር ትርጉም ይጠፋሀል! ወንድሜ ስለሞተ እኔ እየኖርኩኝ ነው ካልክ የመኖር ትርጉም አታውቀውም ማለት ነው። እንድትኖርማ ወንድሞችህ ወይም ልጅህ በሰላም በህይወት መኖር አለባቸው። ወደው አይደሉም ትል ይሆናል ግን እያየሀው ጦርነት እያወጀ የምትደግፈው ገዢ ካለ መኖር ሳይሆን እድልህ ሞት ነው። ልጆቼን አልሰጥም ብለህ ጦርነት አስቀር፣ ህዝብ ወደ ጦርነት እንዳይገባ አስቀድሞ ለሚከላከል አካል ደግፍ፣ምረጥ። ልጆችህን እንደማትሰጥ ካወቀ ጦርነት አይጋብዝብህም። መኖር ከወንድሞችህና ከልጆችህ ጋር ነው። በመምህር Abraha Desta
እነ አቶ ጌታቸውን ይደግፋሉ የሚባሉትና ከጅምሩ ወታደራዊ አመራሩ በፖለቲካው ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት የተቃወሙት ወገኖች፣ ወዲያውኑ ወደ ትግራይ ድንበርና አፋር ሐራ መሬት ላይ በመስፈር ራሳቸውን እያደራጁ መሆናቸውን በይፋ ማስታውቀቃቸው አይዘነጋም።
የከፍተኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት የእነ ዶክተር ደብረጽዮንን ቡድንን በመደገፍ የታጣቂዎቹ ኃይሎች በይፋ ድጋፍ ሲሰጡ ስብሰባ ረግጠው ከወጡት መካከል ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ይጠቀሳሉ። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የኮር አመራሮች የተካተቱበት ይህ ኃይል ነጻ መሬት ላይ መስፈሩን ተከትሎ ብዙ ቢባልም በወቅቱ በይፋ የሰጠው መረጃ አልነበረም። ይሁንና በቅርቡ ለቢቢሲ ትግርኛ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ጀነራሉ “እኛ የምንሠራው ፓርቲ፣ እኛ የምናቋቁመው ወታደራዊ መንግሥት የለም” ሲሉ የአነ ደብረጽዮንን ሃይል በማስወገድ ገለልተኛ ኃይል ለመገንባት ወደ በረሃ መውጥታቸውን ለቢቢሲ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
“አሁን በትግል ላይ ነን ያረጀነውም በትግል ነው” ያሉት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር “ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም” ሲሉም አላቸውን በዚሁ በቢቢሲ ትግርኛ ላይ አስታውቀዋል።
“ራሱን ችሎ ወደ ሕዝብ ይግባ እና ይወዳደር፣ ህወሓት ይጥፋ አይጥፋ የራሱ ጉዳይ ነው። ይቀጥል አይቀጥል የራሱ ጉዳይ ነው። እኔን የሚመለከተኝ የትግራይ ሕዝብ ጉዳይ ነው።” ያሉት ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ፣ እስካሁን ሦስት አራት ግንባሮች እንዳላቸውና እነሱን ተከትሎ ባለውጣው ሠራዊት ውስጥም ብዙ ኃይሎች እንዳሏቸው አመ፤ክተዋል።
“ትልቁ ኃይላችን የሚገኘው ትግራይ ውስጥ ነው” ሲሉ ያስታወቁት ጀነራሉ፣ ሻዕቢያ ትግራይን ተንተርሶ፣ ከሌላኛው ቡድን ጋር ሆኖ ውጊያ ቢከፍት እርምጃቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ተጠይቀው፣ “አሰላለፋችን ከሕዝብ ጋር ነው። እነርሱ [የህወሓት አመራሮች] ከጌቶቻቸው ጋር ሊሄዱ ይችላሉ፤ እኛ ግን ከሕዝብ ጋር ነው የምነቀረው” ሲሉ በይፋ አቋማቸውን ከሕዝብ ይፋ አድርገዋል። በዚሁ መነሻ ሻዕቢያ ከትህነግ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ባድረገው ስብሰባ ይህ አፋር ላይ ያለ ኃይል ቀድሞ እንዲደመሰስ መመሪያ መስጠቱን እዛው ስብሰባ ከተካፈሉት ውስጥ አብረዋቸው የሚሰሩ እንደገለጹላቸው ጠቅሰው አቶ ጣእመ ይፋ ማናገራቸው አይዘነጋም።
እንግዲህ እነዚህ ኃይሎች ናቸው ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳያመሩ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ እየተነገረ ያለው። ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ለጀርመን ድምጽ እንዳለው ሊፈጠር የሚችል ቀውስ ለማስቀረት በትግራይ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት ሊደረግ ይገባል።
በአዲስ አበባ ሰሞኑን በተካሄደ ውይይት በተመሳሳይ ችግር በውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ያሳሰቡ ወገኖች፣ የፊደራል መንግስትን ሲወቅሱ ተደምጧል። የመሳሪያ አቅራቢና ጦርነት አቀጣታይ ኝኙነትን ሳይቀር በማንሳት የትግራይ ሕዝብን መማገድ ምንም የማይመስላቸው አመራኦች እንዳሉ ሞንጆሪኖንና ወንድማቸውን ጠቅሰው ኮንነዋል።
የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ መኮንኖች ባለፈው ጥር 15 ቀን 2017 ዓመተምህረት ለአንድ የህወሓት ክንፍ ያጋደለ የተባለ የአቋም መያዛቸውን ተከትሎ እንዲሁም ቀጥሎ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በኃይል ከስልጣን እንዲወርዱ አድርገዋል ተብሎ በትግራይ ሐይሎች መካከል መከፋፈሎች መፈጠራቸው ይነሳል።
ይህ ደግሞ የትግራይ ሐይልች ከፍተኛ አዛዦች ያሉበት ሌላ ታጣቂ ኃይል እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፥ በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ለወራት የቆየው ይህ አዲስ ሐይል ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ማድረጉም ተነግሯል። የተለያየ ፖለቲካዊ አቋም የሚያንፀባርቁት እነዚህ ለሁለት የተከፈሉ አስቀድሞ አንድ ላይ የነበሩት ታጣቂዎች ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳይገቡ የሚል ስጋት የገባቸው በርካቶች ቢሆንም ሳልሳዊ ወይም “ሶስተኛው ወያኔ”የሚብላወ ድርጅት አሳስቧል።
ይህ ተከትሎ በትግራይ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለ የእርስበርስ ግጭት ስጋት፥ ወደተሟላ ጥፋት ሊመራ እንደሚችል የሚገልፅ መግለጫ ትላንት ያሰራጨው በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ የተያዘው አካሄድ በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።የሕወሓት ባለሥልጣናት ክፍፍል የቆየ ነዉ ተባለ
የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ብርሃነ አፅበሃ በሁለቱ ታጣቂ ሐይሎች በኩል እየተደረጉ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እና እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ፍጥጫው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ማሳያዎች ናቸው ይላሉ። ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጥፋት ሳያስከትል እንዲቆም እንዲሁም በትግራይ ያለው አሳሳቢ ፖለቲካዊ ሁኔታ መፍትሔ የሚሆን ሁሉ አካታች ብሔራዊ ውይይት መደረግ አለበትም ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳስቧል።ህወሓት የጠራው ጠቅላላ ጉባዔ እና በፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል
ከህወሓት ክፍፍል በኃላ የትግራይ ሐይሎች አባላት የነበሩ ታጣቂዎች እንዲሁም ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፥ የተለየ ፖለቲካዊ አመለካከት በመያዝ በትግራይ አለ ያሉት ስርዓት ለማስወገድ በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ራሳቸው እያደራጁ መቆየታቸው መረጃዎች ያሳያሉ።
በእነዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ በቅርቡ ተናግረው የነበሩት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በማንኛውም ፖለቲካዊ ልዩነት በሰላም መፍታት ይገባል ሲሉ ገልፀው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ አሳሳቢ መሆኑ በማንሳት መፍትሔ እንዲበጅ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች እና የዴሞክራሲና ማሕበራዊ ፍትህ ድምፅ የተባሉ ሁለት ሲቪክ ተቋማት በቅርቡ መግለጫ ማውጣታቸው የጀርመን ድምጽ አስታውቆ ነበር።
አነ ወይዘሮ ካሚላ ኢብራሂምን ጨምሮ በርክታ የትግራይ ታዋቂ ፖለቲከኞች የትህነግ ኃይል ከሻዕቢያ ጋር መግጠሙን እየኮነኑ ነው። በተለይም የሰሜን ዕዝ መመታቱትን ተከትሎ ትግራይ በመግባት እጅግ ዘኛኝ ጭፍጨፋ፣ የመንጋ አስገድዶ መድፈር፣ ዘርፊያና ውድመት የሚከሰሰው ሻዕቢያ በአገር ውስጥ ዕርቅ አውርዶ ለፍርድ ከማቅርበና ፍትህ ከማውረድ ይልቅ ከሱው ጋር አብሮ መስራት እጅግ አሳፋሪ እንደሆነ የሚገልጹ ይባዛሉ።
አቋማቸውን ቀይረው ለሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩ የትህነግ ልሳኖችና ደጋፊዎች ፈግሞ አሁን የተጀመረውን አዲስ ኝኙነት “የተቀደሰ” በማለት እያወደሱት ይገኛሉ።
በቅርቡ የተመሰረተውና አቶ ጌታቸው የሚመሩት ስምረት ፓርቲ በይፋ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው የተነገረላቸው ታጣቂ ኃይሎች መሪ “ መንግስት የት እንፋለን ያውቃል” ሲሉ መናጋራቸው ደግሞ ሻዕቢያን እንዳሳሰበው ጉዳዩን የሚከታተሉ ይናገራሉ።
ሻዕቢያ ከትህነግ ብጋር የያዘው የጦርነት ዕቅድ በአፋር በኩል ተቅዋሚ በማደረጃት የጅቡቲ ወደብ መንገድን በመዝጋት ኢትዮጵያን ማንቁርቷን መዝጋት እንደሆነ የትግራይ ኃይሎች መረጃ ማፈትለካቸው አይዘነጋም። መንግስትም ሰፊ ኃይል በአፋር በኩል ማሰለፉና በቡሬ በኩልም ወደ አሰብ ለማኮብከብ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል ሻዕቢያ ከኢትዮጵያ ምን እንደሚፈልግ የማይገባቸው ኢትዮጵያዊያን “ስለምን ሻዕቢያ ዕድሜውን ሁሉ ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን በማደረጃት አገራችንን ያተራምሳል? በመቶ ንሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ተወላጆችን አቅፈን እየኖርን ምን በድለን ነው በክፉ የምንታየው? ወደ አገራቸው እንዲገቡ ሶባል አልቀሰን ሸኝተን፣ ንብረታቸውን በአደራ አስቀምተን ስናበርቃ መንግስታቸው ኢትዮጵያ ላይ በዚህ ደረጃ ሶነሳ ዝም ማለታቸው እንቆቅልሽ ነው ወዘተ “ የሚሉ አሳቦችን ዜጎች እያሰሙ ነው።



