ትህነግና ሻዕቢያ በቅንጅት አዲስ ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት ላይ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ “የተጣለባት ማዕቀብ በተነሳበት በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ጦር ሠራዊቷን መልሳ እያገነባች፣ የመከላከያ ኃይሏን እያጠናከረች እና ጎረቤቶቿ እንዳይረጋጉ ማድረጓን ቀጥላለች” የሚል ጠንካራ ሪፖርት ይፋ መሆኑ ለኤርትራና ለአዲሱ ጥምረት መልካም ዜና አልሆነም።
ውስን የፋኖን ኃይልና ትህነግን ይዞ ለጦርነት ክተት ያወጀው ሻዕቢያ፣ ቅድሚያ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲፈርስ ከእነ ደብረጽዮን ቡድን ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ተፈጻሚ መሆኑ አይዘነጋም። ይህንኑ ስምምነት ይፋ ያደረጉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት በተመሳሳይ የሻዕቢያ ወታደራዊ አመራሮች በአፋርና ትግራይ መካከል ያለው የትግራይ ሰራዊት ቅድሚያ መመታት እንዳለበት መመሪያ መስጠቱን አስታውቀው ነበር።
በትግራይ ሕዝብ ላይ በፈጸመው ጄኖሳይድና ካባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲከሰስ ክስ እየቀረበበት ያለው ሻዕቢያ ባዘዘው መሰረት ይሁን በሌላ አግባብ ባይታወቅም ፋራ በሚባል አክባቢ ከትግራይ የተነሳ ታጣቂ ኃይል አፋርና ትግራይ መካከል ባለውና በብ/ጄነራል ገ/እግዚአብሄር በየነ በሚመራው ሰራዊት ላይ ሰሞኑን ተኩስ ከፍቷል።
እማኞች ከሁለት ቀን በፊት ለቢቢሲ እንዳሉት “ሁለቱም ወገኖች ትግራይ ናቸው። የአገር ሽማግሌዎች መካከል ገብተው አሸማግለዋል” ብለዋል፤ እነዚሁ እማኞች ቀድመው የተኮሱት ከትግራይ ተነሳተው የመጡት ታጣቂዎች እንደሆኑ አመልክተዋል። በሰው ህየ
“በትግራይና ከትግራይ ውጪ ያሉ የትግራይ ኃይሎች ናቸው የተጋጩጥ። ምንም የሚያጋጭ ነገር የለም በሚል ከአፋር የመጡትን መልሰናቸዋል” ሲሉ ሽምግልናው ላይ የነበሩ አስታውቀዋል። አራት ጊዜ ብቻ ዲሽቃ ከመተኮሱ ውጪ ስላደረሰው ጉዳት ምንም እንዳልሰሙም ተናግረዋል።
ደግፌ ጎደፋይ የተባሉ አንድ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራር ተኩሱ ለማስፈራራት የተሞከረ እንደሚመሳላቸው ተናግረዋል። ” ሕዝቡ ለምን እንደተተኮሰ፣ የሚያውቀው ነገር የለም። ግን ፈርቷል። እርሻውን በጋት ማረስ አልቻለም። ስራውንም ማከናወን አልቻለም። ከትግራይ በኩሉ የመጡት ቢመለሱ መልካም ነው” ብለዋል።
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ያኮረፈው ሻዕቢያ በዓመቱ አጋማሽ ላይ የቀድሞ የሠራዊት አባላት ወደ የክፍሎቻቸው ለዳግም ሥልጠና እንዲመለሱ እና ሌሎች ዜጎቹ ከአገር ለመውጣት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ማጥበቁን ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።
በዚህም ከ60 ዓመት በታች የሆኑ በኤርትራ ሠራዊት ውስጥ ያገለገሉ ዜጎች ተመዝግብው ወደ ማሠልጠኛ እንዲገቡ፤ እንዲሁም ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ ተገቢውን ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ሳያገኙ ከአገር እንዳይወጡ ዕገዳ መጣሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህ ቢባልም ኤርትራ ባማስታወቂያ ሚኒስቴሯ አማካይነት ዜናውን አስተባብላለች። እንደውም የተለመደ ስም ማጥፋ እንደሆነ ነው ያመለከቱት።
ጉዳይ ግልጽ ባይሆንም ለዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ የሚመሰርተውና ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው “ሴንቸር” የሚሰኘው የምርመራ ቡድን የኤርትራ መንግስት ከሽብር ሃይሎች ጋር ግንኙነት እንደነበረው በሪፖርቱ አስታውሷል። ከዓመት በፊት በእስራኤል የሚታተም አንድ ጋዜጣ ሸዕቢያን ከኢራንና ከየመን ሃውቲ ጋር ግንኙነት እንዳላለውና ይህ ደግሞ ለአጋራቸው ስጋት እንደሆነ ሰፊ ሪፖርት አቅርቦ ነበር። ኤርትራ የኢራን ጥብቅ ወዳጅ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የቀረበው ይህ ሪፖርት እስራኤል ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመለስ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩልም በገሃድ መገለጹን ተከትሎ መውጣቱ ሪፖርቱን ሰፊ መነጋገሪያ እንዲሆን አስችሎታል።
ሰሞኑን በትግራይ ተሰማ የተባለውን ተኩስና በአንዳንድ አካባቢ ትንኮሳ መኖሩ ከተሰማ በሁዋላ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “የምትችሉ ሁሉ ጦርነት ሳይጀመር ምክሩ” ሲሉ የተደመጠው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ከኢትዮኢንሳይደር ወስደን እንዳለ አትመነዋል። ከስር ያንብቡ
የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26፤ 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በሁለት ክፍል የቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ቅድሚያውን እና ሰፊውን ጊዜ የሰጠው፤ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች ነበር።
ሶስት ሰዓት ገደማ ከፈጀው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ውስጥ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ የተመደበለት አንድ ሰዓት ያልሞላ ጊዜ ነበር። በዚህኛው የማብራሪያ ክፍል ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ ትግራይ እና ኤርትራን የተመለከቱት ይገኙበታል።
“የትግራይ ህዝብ መቶ ፐርሰንት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት አብይ፤ ከህዝብ ፍላጎት እና አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። “[ዓለም] ብዙ ውጊያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም፣ ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል።
አብይ በማብራሪያቸው “አንዳንዶች” ሲሉ የገለጿቸው ግለሰቦች፤ “የሚያግዙን ሰዎች እና ሃገራት አሉ” ብለው እንደሚያስቡ ጠቅሰዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ “ትላልቅ ውጊያዎች” እንኳን “መደጋገፍ ችግር ሆኗል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የእዚህ ምክንያቱ ደግሞ “ከራስ ተርፎ ሰው ለማገዝ የማያስችል” ሆኗል ያሉት የዓለም ኢኮኖሚ እንደሆነ አስረድተዋል።
“እነዚህ ሀገራት እንኳን እናንተን እራሳቸውን ማገዝ አይችሉም። ሞራል ቲፎዞነት እና ማገዝ ለየብቻ ነው፤ ስታዲየም ተቀምጦ ማጨብጨብ እና ኳስ ሜዳ ገብቶ መጫወት ለየብቻ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከሌሎች ሀገራት “እገዛ እናገኛለን” ብለው ማሰብ “ስሁት ግምገማ ነው” ሲሉ ተችተዋል።
በእነዚህ ግለሰቦች ዘንድ “የአለምን ነገር” እና “የዘመኑን የውጊያ ስልት” “አለመገንዘብ” እንደሚስተዋል የተናገሩት አብይ፤ “እንደ ድሮው ተራራ መያዝ፣ ተራራ መልቀቅ ብቻ ማሰብ” ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋል። ለዚህ በቅርቡ በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተካሄደውን ጦርነት በማሳያነት አንስተዋል። “ኢራንን እና እስራኤልን ያዋጋው ተራራ አይደለም፤ ዘመን ተቀይሯል” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
“መንግስት በሸኔ እና በፋኖ ተወጥሯል” የሚል አመለካከት ያላቸው ሌሎች ሰዎች ደግሞ፤ “መንግስት ወታደር ስለተበታተነበት። ጊዜው አሁን ነው” እንደሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። “እነዚህ ሰዎች ታሪክ መለስ ብለው ማየት በቂያቸው ነው” ያሉት አብይ፤ ይህንኑ ለማስረዳት የጣሊያን እና ሶማሊያን ወረራዎች አስታውሰዋል።
“ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወር፤ እንኳን የተበተነ – ወታደር አልነበረንም። ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር ወታደር አልነበረንም፤ ከበሮ ነው የነበረን። ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል የግድ ሰልፍ የያዘ ወታደር አያስፈልጋትም። ታሪኳ እሱን አያሳይም። እኛ የተሻለ አቅም አለን ግን ያም ቢሆን፣ ሌሎቹም ቢሆን በዚያ መሰላት የለበትም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

