Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Thoughts on an American-mediated settlement in Ethiopia

    January 26, 20220

    Pelé dies aged 82

    December 29, 20220

    As BRICS Accumulate Gold, Western Banks Continue to Short Sell

    October 15, 20240

    የአውሮፓ ሕብረት የ38 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

    November 10, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    አደዋ መንፈስ ነው ይጋባብን!!

    March 2, 20240

    ነፋስና የበረዶ ውሽንፍር የበላት ቡፋሎ ከተማ ‘የጦርነት ቀጠና’ 

    December 27, 20220

    «የኢትዮጵያ አንድነት የሚቆመው በጋራ ስንሠራ ነው ብለን ተስማምተናል”

    February 12, 20220

    “የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

    December 8, 20210

    ካረን ባስ – አቋማቸውን አስተካከሉ፤ ጠ/ሚ አብይን በማንሳት ጉዳይ እንደማይስማሙ ይፋ አድረጉ

    November 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ኢሳያስ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ፍሬዎችን ተግባር ላይ እንድታውል መከሩ፤ ምክራቸው ጤናቸውን ለሚጠራጠሩ ምላሽ ነው ተብሏል
News

ኢሳያስ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ፍሬዎችን ተግባር ላይ እንድታውል መከሩ፤ ምክራቸው ጤናቸውን ለሚጠራጠሩ ምላሽ ነው ተብሏል

Ethioreview newsEthioreview news—July 20, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መናገርና መተንተንን የፖለቲካ ስትራቴጂ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ፕሮፌሰር አስመሮም ኢትዮጵያን በወራሪነት ከፈረጁበት ቃለ ምልልስ ጋር የተዘመደ መግለጫ ሰጡ፡፡ ኢትዮጵያን የማተራመስ አጀንዳ በመያዝ እየፈጸሙ ስላለው ተግባር ሳይተነፍሱ ራሳቸውን መላዕክ አድረገው ማቅረባቸው የሚነሳባቸውን የጤና ችግር ጉዳይ አጉልቶባቸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ አምባሳደር ኃይሌ መንቆሪዎስ ጦርነት ከተነሳ ጉዳቱ ከፍተኛ እንደሚሆን ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ሲያስታውቁ ” ኤርትራ ተወረርኩኝ፤ እርዳታ እሻለሁ ካለች፣ ወረራውን ለመቀልበስ ከየትኛውም አገር ድጋፍ የመጠየቅ መብት አላት” ሲሉ ኢትዮጵያን ወራሪ አድርገው መሳላቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትለው በብቸኛው የአገራቸው ብሄራዊ ቴሌቪዥን ሑለት ሰዓት በፈጀ መግለጫቸው በተመሳሳይ ኢትዮጵያን በወራሪነት ፈርጀዋል። በጅምላ ሲያስጨፈጭፉት ለነበረው የትግራይ ሕዝብና ፋኖ ጥብቅና ቆመዋል።

የእነ ደብረጽዮን ቡድን ከሻዕቢያ ጋር በይፋ ግንኙነት መፍጠሩን፣ ይህም አደባባይ የሚታወቅና እየተሰራበት ያለ ጉዳይ ሆኖ ሳለ ኢሳያስ ለአፍታም አላነሱትም።። አምባሳደር ኃይሌ መንቆሪዎስ ግን ኤርትራ ከፋኖና ከከፊል የትግራይ ኃይሎች ጋር ግንኙነት መፍጠሯን እንደሚያውቁ መስክረዋል።
የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ሻዕቢያ) ከፍተኛ አመራር የነበሩት አምባሳደር ኃይሌ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር መጠየቋን ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያና ግብጽ ጣልቃ እንደሚገቡ ተናግረው፣ “…..ኤርትራ እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ እንደሆነ መረጃ አለኝ። በከፊል በትግራይ ግንኙነት እየፈጠሩ ነው፤. . . በአማራም ከፋኖዎች ጋር እንዲሁ ግንኙነት አላቸው” ሲሉ የሚያውቁትን የአደባባይ ሃቅ ይፋ አድርገዋል።

More stories

በትግራይ የሕዝብ ጩኸት “ጦርነት መሸከም አንችልም” ገንዘብ ያላቸው እየተሰደዱ ነው

March 15, 2025

«ሠራዊቱ ጠላትን በአጭር ጊዜ ደምስሶ ለወገኑ የድል ብሥራት ለማቅረብ በከፍተኛ ወኔ እየገሰገሰ ነው»

November 28, 2021

ደኅንነትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰዱ አስታወቁ

March 30, 2023

የጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር ” ካሁን በሁዋላ በስሜ ጠብ መንጃ ይዞ የሚነቀሳቀስ ሃይል የለም”

April 28, 2023

ይህ እየታወቀ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸውን ከደሙ ንጹህ አድርገው ኢትዮጵያን ወራሪና በኤርትራ ጥቅም ላይ ያነጣጠረች አገር አድርገው ሲወነጅሉ ተደምጠዋል።

የሙግት ጥያቄም ሆነ ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ጥያቄ የማይቀርብላቸው ኢሳያስ አፉወርቂ፣ ዘወትር ምክንያት ፈልገው ንግግር ካደረጉ ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ሰው ሀገር ጉዳዮች ሰፊ ጊዜ ወስደው በመናገርና በመተንተን የሚታወቁት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ትላንት ምሽት ኢትዮጵያን ወራሪ አድርገው ሲስሉ ለመከላከል መዘጋጀታቸውንም በማስታወስ ነው።

አገራቸውንና ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፈው በመስጠት በኢትዮጵያ ባንዲራ ታጅለው ኢትዮጵያን የሚደበድቡና እንድትፈርስ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሚዲያዎችም የሚያውቁትን ሃቅ ትተው “ኢሳያስ እንዲህ አሉ” በሚል መግለጫቸውን እያራገቡላቸው ነው።

በቅርቡ “ነጻነት” በሚል በሚከበረው የኤርትራ በዓል ላይ ፕሬዝዳንቱ ለገራቸው ሕዝብ ስለራሳቸው ጉዳይ ምንም ሳይሉ፣ ስለ ኢትዮጵያ እና ቀጠናው ጉዳይ ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር አይዘነጋም። አብዛኞችን የሚያስገርመው ግን ከመንግስት ወገን ለሳቸውም ሆነ በእሳቸው ዙሪያ ያሉ ለሚሰነዝሩት ክስ “የዝምታ ፖለቲካ” መምረጡ ነው፤

ትላንት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ንዴትን በቀላቀለ ሁኔታ በማይመጥኑ ቃላት የኢትዮጵያን ስም ሲያነሱና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የባህር በር ጥያቄ ማንሳታቸውን “የልጅ ጨዋታ” በሚል ሲያቃልሉ ተሰምተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወደ ጉዳይ ሲያነሱላቸው በጅቡቲ እንጀራ ጣልቃ መግባት እንደማይፈልጉ መናገራቸውን አብይ አHመድን ” ልጅ” ባሉበት አንድበታቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ ሲያጣጥሉት ነው ያመሹት ኢሳያስ ፣ጥያቄውን ” የህጻን ጨዋታ ነው፣ ማሳሳቻ ነው፣ የረከሰ ውሸት ነው ፣ የውስጥ ጉዳይ ማዳፈኛ ነው ፣ ጀርባው የተባበሩት አረብ ኤሜራት የወደብ ማስፋፋት አጀንዳ ነው ” በሚል ሲቀባቡ ተደምጠዋል።

ይህንኑ ዲስኩር “ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም የሚሉ ኢትዮጵያዊያን የተባሉ ‘ኢሳያስ ሃቁን አፈረጡ’ ” በሚል ሲያራግቡት ” አንዳንድ የትግራይ አክቲቪስቶች ደግሞ ከበሮ ጭምር እየመቱ አዳንቀዋል። እነዚህ ክፍሎች ኢሳያስን “ጄኖሳይደር” በማለት ሲከሱና በትግራይ ላላቁት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተጠያቂ ሲያደርጉ የነበሩ መሆናቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የባህር በርን ጉዳይ አለም አቀፍ አጀንዳ ማድረጓን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለጥያቄዋ ድጋፍ ማድረጋቸው በተለያዩ ታዋቂ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል። ይህ የዲፕሎማሲ አካሄድ ውጤታማ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘወትር መግለጫው ላይ እግረ መነገዱን ጠቆም የሚያደርገው ጉዳይ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን እንዳላስደሰተም። በርካቶች እንደሚሉት ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

በዚሁ መነሻ ” ፈረንሳይ ከኛ ጋር ናት፣ አሜሪካ ፣ ኤሚሬት፣ አውሮፓ ህብረት ከኛ ጎን ናቸው ማለት ጭንቅ እንጂ የድል መንገድ አይደለም ” በማለት ለማጣጣል የሞከሩት ኢሳያስ፣ ነገሩን አዙረው ” ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግራችሁን ፍቱ ” ሲሉ ተደምጠዋል። እሳቸው በትግራይ፣ በኦጋዴን አማራና ኦሮሞ ታጣቂዎችን በማስለጠን፣ በውክልና በሚያገኙት እርዳታ እየስታጠቁ ኢትዮጵያን የማተራመስ የማይቆም አጀንዳቸውን ለምን እነደማያቆሙ የሚጠይቃቸው የለም።

በማተራመስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሰነሰለታቸውንና ኤምባሲያቸውን ተጠቅመው በዶላር አጠባ፣ በኮንትሮባንድና ዝርፊያ የተሰማራው መንግስታቸው ከማጅራት መቺነት ወጥቶ መቼ እንደመንግስት እንደሚያስብ ፍንጭ ሰጥተው አያውቁም።

በኢትዮጵያ በኩል ሀገራቸው ላይ የጦርነት  ስጋትና ዛቻ እንዳለ በማመላከትም ” እራሳችንን እንጠብቃለን ” ሲሉ ከአምባሳደርሩ ጋር የተመሳሳለ የፍረጃ ክስ ለሕዝባቸው የገለጹት ኢሳያስ፣ ኢትዮጵያ ለባሕር ስትል ኤርትራንም ሆነ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር የመውጋት አንዳችም ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ማሳወቋን ጆሮ ዳባ ብለዋል።

ኢትዮጵያ አንድም ጊዜ የአሰብን ስም አንስታ እንደማታውቅ፣ የባህር በር ጉዳይ የህልውናዋ ጉዳይ መሆኑን በመግለጽ በዓለም የንግድ ህጎች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ይህንኑ ፋልጎቷን ለማሳካት እንደምጸራ ይፋ ከማድረጓ አንጻር በመንግስት ደረጃ የተመዘገበ የጦርነት አዋጅ ይህ እስከታተመ ድረስ አልተደመጠም። ይልቁኑም ኤርትራ ተቃዋሚዎችን በማደራጀት፣ የኢትዮጵያን ክልል ዘለቃ በመግባት ሰብአዊ መብት እየጣሰች በመሆኑ ዓለም “አንድ ይበል” የሚል ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት መላኳ ነው በይፋ የሚታወቀው።

አምብሳደር ኃይሌም ይህ ደብዳቤ እሳቸው ለሚሰሩበት ድርጅት መላኩን እያወቁ በዝምታ አልፈውታል። ይልቁኑም “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊተማመነባቸው የሚችሉ የአገር ውስጥ ኃይሎች ተከፋፍለዋል” በሚል ሻዕቢያ በጣልቃ ገብነት እየሰራ ያለውን ሴራ አኘው አሳይተዋል። አክለውም “ኢሳይያስ በህወሓት እና በአማራ አማካኝነት በሁሉም በኩል ዐቢይን ለመክበብ እየሞከረ አይደለም ማለት አይቻልም” ሲል ራሳቸውን ዳር የቆሙ በማስመሰል በትክክል መሬት ላይ የሚሞከረውን መስክረዋል።

ይህን ሁሉ እያደረጉና በራሳቸው ሰዎች ሳይቀር እየተመሰከረባቸው ያሉት ፕሬዜዳንት ኢሳያስ “ኢትዮጵያ ተመድ ሄዳ ከሳናለች ክሱ አስነዋሪና አሳፋሪ ነው ” ሲሉ ተደምጠዋል። ኢሳያስ ጦራቸው የኢትዮጵያን አስር ኪሎ ሜትር ርቆ መግባቱን ሴንቸሪ ያወጣው ሪፖርት ሰሞኑን ማጋለጡ አይዘነጋም።
ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነትም ሲናገሩ የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲፈረም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳሻከረች በይፋ የሚታወቅ መሆኑበመሸምጠጥ ነው።

” ኤርትራን ከመክሰሳችሁ በፊት የፕሪቶሪያን ውል ተግብሩ ፤ የውስጥ ችግራችሁን መፍታት አስቀድሙ ፤ ለምን ስምምነቱ በቅን ልቦና አልተተገበርም ለምን ፋኖ ላይ ጦርነት ከፈታችሁ ” የሚል መጨበጫ የሌለው የወቀሳ አስተያየት ሰንዝረዋል።
ፕሬዚዳንቱ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም ” ተኮላሊፍና” ወይም “ከሸፈብን” ሲሉ ትህነግን ከምድር ላይ የማጥፋት ዕቅዳቸው በመሰናከሉ በይፋ ከመንግስት ጋር ያላቸውን ትብብር ማቆማቸውን ይፋ ማስታወቃቸው የቅርብ ጊዜ ጉዳይ እንደሆነ ዘንግተዋል።

ሌላው ኢሳያስ ለኤርትራ ሕዝብ በይፋ የተናገሩትና ሰሚዎችን ያሳቀው ጉዳይ ቢኖር የዴሞክራሲ ፍሬዎችን አንስተው ምክር መለገሳቸው ነው። ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያ፣ የዕምነት ነጻነት ፣ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በጀት፣ ህግ አውጪና ተርጓሚ፣ ኢንተርኔት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት ወዘተ የማይታወቅባትን ኤርትራ የሚመሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ” በኢትዮጵያ መታየት ጀምሮ የነበረው የለውጥ ተስፋ ጨልሟል ፤ የፖለቲካ ፓርቲ ብሎ የለም ” የሚል ንግግር አሰምተዋል። ይህን ሲናገሩ ጠያቂዎች ሆነው የተመደቡት ሁለት አጃቢዎቻቸው የሰውነት እንቅስቃሴ እንኳን አይታይባቸውም።

ያለአንዳች ተቀናቃኝ ከ30 ዓመት በላይ  ኤርትራን እየገዙ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ሁል ጊዜው የትላንት ምሽቱ ቃለ ምልልሳቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ሌሎች ሀገራት ጉዳይ በመተንተን አሳልፈዋል።

ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እስኪፈረም ድረስ ኢትዮጵያን እና አስተዳደሯን ሲያሞካሹ እንደቆዩ በአደባባይ የሚታወቅ ሀቅ ነው። ዕርቅ በተፈጸመ ማግስት ከአራት መቶ ሺህ በላይ ኤርትራን ለቀው በድንበር ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውም አይዘነጋም።

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አገሩን ጥሎ የሚፈልሰው የኤርትራን ሕዝብ እድሜ ጾታ ሳይለዩ በየአገሩ በስደት የሚኖሩት፣ አብዛኞች በባህር ላይ የሚያልቁትና በበረሃ የሚሞቱት የኢሳያስን አስተዳደር በመጥላት መሆኑ እየታወቀ ስለ ኢትዮጵያ ለውጥ ማንሳታቸው ጤናቸውን ለሚጠራጠሩ ማረጋገጫ ሆኗል።

“በኤርትራ ሰዓት ቆሟል” በሚል የወጡ ዶክመንታሪ ፊልሞች እንደሚያሳዩት በአስመራ የኤቲኤም የመክፈያ ስርዓት በቅ ነው። ኢንተርኔት በስለፍና በቀጠሮ ነው። ቲክቶክና የማህበራዊ ሚዲያ ምስሎች ማውረድና መጫን አይታሰብም። ሰዎች የሚኖሩት በገደብ ነው። እንደፈለጉ መውጣትና መግባት አይቻልም። ከተማዋ ቀለም እንኳን በአግባቡ አልተቀባችም። የመንገድ እድሳትና አዳዲስ ነገሮች የሉባትም። በተለይም ወታቶች ብዙም አይታዩባትም። እንዲህ ያለውን አገር ከጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን ከማሳደግ ይልቅ በውክልና ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሁሉ የተዋጉት ኢሳያስ፣ ፕሮፌሰርሩ እንዳሉት ኢትዮጵያን ከውስጥ ባንዶች ጋር ሆነው ለማፍረስ እየሰሩ ነው። ይህንን የተረዱ ” ኢሳያስ እያሉ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም” በሚል ደምድመዋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios
የአሜሪካ ኤምባሲ የጉብኘት ቪዛ የተደረገ የፖሊሲ ለውጥ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia

June 10, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
News

ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

June 5, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐚𝐧𝐝 𝐍𝐢𝐠𝐞𝐫𝐢𝐚 𝐃𝐞𝐞𝐩𝐞𝐧𝐏𝐚𝐫𝐭𝐧𝐞𝐫𝐬𝐡𝐢𝐩 𝐭𝐡𝐫𝐨𝐮𝐠𝐡 𝐁𝐢𝐥𝐚𝐭𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐓𝐚𝐥𝐤𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐋𝐞𝐠𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐨𝐩𝐞𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐀𝐠𝐫𝐞𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭

June 10, 20260
News

Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia

June 10, 20260
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
Load more
Recent Posts
  • 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐚𝐧𝐝 𝐍𝐢𝐠𝐞𝐫𝐢𝐚 𝐃𝐞𝐞𝐩𝐞𝐧𝐏𝐚𝐫𝐭𝐧𝐞𝐫𝐬𝐡𝐢𝐩 𝐭𝐡𝐫𝐨𝐮𝐠𝐡 𝐁𝐢𝐥𝐚𝐭𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐓𝐚𝐥𝐤𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐋𝐞𝐠𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐨𝐩𝐞𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐀𝐠𝐫𝐞𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 June 10, 2026
  • Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia June 10, 2026
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news