Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  የአብይ አሕመድ “ፈጣኑ ባቡር” ተሳፋሪዎች – የእድሜ ልክ ሽግግር መንግስት አዝጋሚዎች
News

የአብይ አሕመድ “ፈጣኑ ባቡር” ተሳፋሪዎች – የእድሜ ልክ ሽግግር መንግስት አዝጋሚዎች

Ethioreview newsEthioreview news—August 21, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያ ሁለት ሊታረቁ የማይችሉ ጎዳና ላይ ትገኛለች። አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር የሚከንፉበት “የፈጥነት ባቡር” ሲሆን፣ ሌላኛው መንገድ ደግሞ መልካቸውንና ቁመናቸውን መሽቶ ሲነጋ የሚቀያይሩ፣ ጠዋት ተጣምረው ከሰዓት በሚበተኑ፣ ቋሚ መርህና አማራጭ አሳብ ሳያቀርቡ በመቃወም ብቻ የሚያዘግሙበት የእድሜ ልክ የሽግግር መንግስት ናፋቂዎች ባቡር …

አብይ አሕመድ እንደሚሉት ፍጥነትና ተኝታ ለኖረች አገር ፍቱን መድሃኒት ነው። እሳቸው እንደሚሉት የተለየነውን ዓለም መቀላቀል የምንችለው በፍጥነት ጉዞና በከፍታ በመብረር ነው። ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ደስኩረው ማሳረጊያቸው “ሽግግር መንግስት፣ አዲስ ጥምረት፣ የተለያዩ የህብረትና የቅንጅት ስም ማስተዋወቅ፣ የምድሩን ጨርሰው በሰማይ ላይ ‘አንቀጥቅጥ’ ስለፍ አለን” የሚሉቱ ናቸው።

ሰውየው ኢህአዴግን ሲያፈርሱ የሮጡበት ፍጥነት ያልገባቸው ዛሬ ላይ በፍጹም ጥላቻ የተቀነባበረ ዘመቻ ላይ የተረባረቡት ኢትዮጵያን ለዚህ ሁሉ ጣጣ የዳረጋት የዘር ፖለቲካ እየከሰመ መሄዱ፣ በቀጣይም የዘር ፖለቲካ ሕዝብ ስለጠላው ለተቀናቃኞች ለቅሶ ሲባል እንደማይቀጥል ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ እንደሆነ የገባቸው እየተናገሩ ነው። የፍጥነትን ጉዳይ አስመልክቶ ስብሃት ነጋ የተናገሩት እጅግ ገላጭ ይሆናል።

“ጠዋት ስንነቃ ብዙ አዳዲስ ነገር ይዞ ይመጣል። እኛ በዚህኛው ጉዳይ ለመነጋገር ቀጠሮ ስንይዝ በላይ በላይ ብዙ ነገር ይደራረባል። ፍጥነቱን አልቻልነውም” በሚል ስብሃት ነጋ ትህነግ ወደ መቀለ ከተመለሰ በሁዋላ መናገራቸው ይታወሳል። ዶክተር ደብረጺዮንም በተመሳሳይ “ጠዋት እዚህ ሲባል…” ብለው ፍጥነታቸውን አልቻልነውም ብለው ነበር።

More stories

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

April 7, 2021

የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤ አንገታቸው የተቀላ መኮንኖች ፊልም ሊታዩ ነው

May 13, 2021

ከሱዳን የተነሳ የትህነግ ሃይል (ሳምሪ) ሳይዋጋ ሙሉ በሙሉ ተማረከ

August 11, 2021

የመንግስት ማጅራት መቺዎች ፈተና ሆነዋል – ሃላፊዋ አምነዋል

May 9, 2022

ስብሃት ነጋ የመጡበትና የኖሩበት የትህነግ ፖለቲካዊ ባህል በአንድ ጉዳይ ሶስት ወር በር ዘግቶ መገማገም ነው። በራሳቸው ታጋዮች በተደጋጋሚ ምስክርነት ሲሰጥ ለዓመትም የቆዩበት ጊዜ አለ። የሚያስገርመው ትህነግ ሊገማገም በር ዚዘጋ ሕዝብ ቁጭ ብሎ የመጠበቁ ጉዳይ ነው።

አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ይህ ባህል ተቀይሯል። ሁሉም ስራ ፍጥነቱ አስገራሚ ሆኗል። በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ጭምር የታየው የማድረስና የመፈጸም ብቃት ትህነግ ከኖረበት ባህል ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ መቸገራቸውን በመደነቅ የመሰከሩትም ወደው አልነበረም።

ከፋና ጋር አራተኛውን መጽሃፋቸውን አስመክቶ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ ስለፍጥነትና ሲናገሩ ከከፍታ ጋር በማያያዝ ነው። ለውጡን መከተል ያልቻሉና ለማደነቃቀፍ የሞከሩትም የተንጠባጠቡት በዚሁ የፍጥነትና የከፍታ ጉዞ መቀጠል አለመቻላቸው ነው።

በአንድ አውሮፕላን ውስጥ እባብ የተመለከተች የበረራ አስተናጋጅ፣ ለፓይለቱ እባብ ማየቷን ነገረችው። ፓይለቱም የእባቡን መኖር ሲሰማ የአውሮፕላኑን ከፍታ ጨመረ። ከዚያም የበረራ አስተናጋጇን “ሂጂና እይው” አላት። እንድተባለችው ሄዳ ስትመለከተው እባቡ እንዳልሆን ሆኖ አክትሞለታል። ተመልሳ ለፓይለቱ ያየችውን ነገረችው። ፓይለቱን ከፍታ ሲጨምር እባብ መተንፈስ እንደሚሳነውና ላይመለስ እነደሚሰናበት አስረዳት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለውጡ ከፍታውን መጨመሩና በፍጥነት መካሄዱ ሊያደነቃቅፉና የራሳቸውን የቀድሞ እሳቤ ሊመልሱ የፈልጉ ሳይሳካላቸው ሊንጠባጠቡ መቻላቸውን ለማስረዳት ነበር ይህን ምሳሌ ያነሱት። ከላይ የተገለጹት ሁለቱ ቱባ የትህነግ መሪዎች “ፈጥነቱን አልቻልነውም” ያሉት ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ለውጡን ተከትለው ወደ መቀለ ከተመለሱ በሁዋላ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የመደመር መንግስት የሚለውን መጽሃፋቸውን አስመልክቶ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ከዚህ ቀደም በመደመር ሐሳብ ላይ ያተኮሩ መደመር፣ የመደመር መንገድ እና የመደመር ትውልድ የተሰኙ ሦስት መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወቃል፡፡

ሃሳብ አልባ ፖለቲካ

የፖለቲካ መረጋጋት እና መግባባት መፍጠር ሌላኛው አስቻይ ሁኔታ እንደሆነ ጠቅሰው ፥ ይህም የፖለቲካ ስርዓት መረጋጋት የማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን በፍጥነት ለመምራት መሰረት እንደሚጥል አስረድተዋል።

ይህንን ለማሳካት የመደመር መንግስት እስካሁን ባለው ልምምድ ሆደ ሰፊነትን የሚከተል እንደሆነ እና አንዳንድ ነገሮችን ይቅር በማለት በዋናው ግባችን ላይ ማተኮር እና የጋራ ራዕይ በትብብር ለሚደረግ ጥረት የልብ ምት ነው ብሎ ያምናል ብለዋል።

በዚህ ውስጥ ሃሳብ አልባ የፖለቲካ ተግዳሮት ከብልጽግና ግብ እንዳንደርስ መደነቃቀፍን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

የመደመር መንግስት ብቸኛ ከዚህ ማምለጫ መንገዱ የሀሳብ ገበያ በመፍጠር፤ ይህም እንዲሰፋ እና እንዲሻሻል ማድረግ እንደሆነ ያብራራል ነው ያሉት።

በፖለቲካ ምሕዳር ውስጥ እውነት እና እውቀት እንዲሰለጥኑ ማድረግ እንዲሁም መርህ እና ሕጋዊ ሂደትን የሚከተል ተቋማዊ አሰራር ማስፋት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት እና የሀገራችንን ችግር ለመፍታት አማራጭ ሃሳቦች እንዲበራክቱና አማራጭ ሀሳቦችን በመደመር መፍትሔ መፍጠር ከሀሳብ አልባ ፖለቲካ ማምለጫ መንገድ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የመደመር መንግስት ከሌሎች የመንግስታት እሳቤዎች በውጤቱ ይለያል

የመደመር መንግሥት ከሌሎች የመንግስታት እሳቤዎች በውጤቱና ሂደቱ ይለያል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በተሰኘው አዲሱ መጽሐፋቸው ዙሪያ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የመደመር መንግሥት ዋነኛ ግብ ኢትዮጵያን ለውስን ግለሰቦችና ቡድኖች ፍላጎቶች ሳይሆን ለኢትዮጵያዊያን መሻቶች ማስረከብ ነው ብለዋል፡፡

ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማሳካት በሂደቱ አቅምና አቋም መደመር እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ በዚህም ሁሉም ኢትዮጵጵያውያን ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ እንዲሳተፉ በመደረጉ አጋር ተብለው የነበሩ ክልሎች በመደመር መንግስት የሀገር ባለቤት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በመንግስትና ዜጎች መካከል ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲኖርና ጤናማ ስርዓት እንዲገነባ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን፥ የበዛ ነጻነት ወደ ስርዓት አልበኝነት ስለሚመራ ሚዛናዊነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የታለመው ግብ ጋር ለመድረስ በመንግስት በኩል ሁሉንም ነገር በመጠቅልል አምባገነናዊ ስርዓት እንዳይፈጠርና ህጋዊነቱን በምርጫ ከዜጎች እንዲያገኝ ሚዛናዊነትን መከተል አስፈላጊ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

የመደመር መንግስት መገለጫ ምናባዊ ከፍታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በሰሩት ስራ በመርካት መቆም እንዳይኖር በምናባዊ ከፍታ አሻግሮ ማየትና ስራን መከወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሌላኛው የመደመር መንግስት መገለጫ የማድረግ አቅም መሆኑን ጠቁመው፥ የታቀዱ ህልሞችን መጨረስና መሬት ላይ ማውረድ ባህሪው ነው ብለዋል፡፡

የተላማጅነት ባህሪ የመደመር መንግስት ሌላኛው መገለጫው ሲሆን፥ ለዚህም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ጨምሮ ሌሎች ችግሮችን ወደ እድል የተቀየረበትን መንገድ አንስተዋል፡፡

“የመደመር መንግስት” የተሰኘው 4ኛ መጽሐፍ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፤ በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት ስራዎች ምስክርነት እየተሰጠባቸው ነው ብለዋል።

ለማሳያነትም እንጦጦ ሽሮሜዳ አካባቢ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ከ700 በላይ አዳዲስ የቢዝነስ ሱቆች መከፈታቸውን ጠቁመው፤ ይህም ለበርካታ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

የወንዝ ዳርቻ ልማት ለበርካታ ሰዎች የቢዝነስና የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመው፤ ለመላው አፍሪካ ልክ እንደ አረንጓዴ ዐሻራ ምልክትና አርአያ ሊሆን የሚችል ስራ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማት በተለያየ መልኩ ስራ መፍጠር፣ የሀገርን ገጽታና ምልከታ መቀየር እንዲሁም ጤናማነትን ማረጋገጥ የቻለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ለሁሉም አፍሪካ ምሳሌ መሆን የሚችል እንደሆነ አንስተው፤ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ መሪዎች ልዑካን እየላኩ ልምድ የሚቀስሙበትና የሚቀምሩበት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የከተማ ኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትና የገጠር ኮሪደርና ፕሮጀክቶች የሚጨበጡ፣ የሚታዩ ስራዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ስራዎቹ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሊኮሩባቸው የሚገቡ ልማቶች መሆናቸውን አንስተው፤ እጅግ የሚያኮራ በመደመር መንግስትና በህዝብ መካከል ባሉ የጋራ ራዕይ ስነቃ የተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ከፍተኛ ምሳሌያዊ ስራ ሆኖ ለብዙ ሀገራት የሚያገለግል፤ የመደመር ትውልድ በዘመኑ ውስጥ ያስቀመጠው አሻራ፣ የማይናወጥና አኩሪ ተግባር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

መደመር በሁሉም ሕብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ እሳቤ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የመደመር መንግሥት” የተሰኘውን አዲሱ መጽሐፋቸውን በተመለከተ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ መደመር የተሟላ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓታዊ ምላሽን የሚያረጋግጥ ሰፊ ጉዳዮችን በውስጡ የያዘ ጉዳይ ነው።

መደመር ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት፣ ሥርዓታዊ ምላሽ ለመስጠት የተነደፈ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እሳቤ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

የመደመር እሳቤ ‘ከደቡብ አፍሪካው ኡቡንቱ’ እና ‘ከግሪኩ ወርቃማው አማካይ’ የተለየ መሆኑን አንስተው÷ ስለግለሰቦች ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ውስብስብ ችግሮችን ሥርዓታዊ መፍትሔዎችን ለማምጣት የተነደፈ ነው ብለዋል፡፡

በተፈጥሮ ያለው የሃብት እጥረት፣ ከሰው ተፈጥሯዊ ባህሪ የተነሳ ፉክክር እንደሚፈጠር እና ሰው መልካም እና ለሌሎች አሳቢ በመሆኑ ደግሞ መተባበር እንደሚፈጠር ፤ሁለቱም እኩል ሆነው ሚዛናቸውን ካልጠበቁ ደግሞ መልሰው ችግር እንደሚፈጥሩ አንስተዋል።

ትብብር የሌለበት ሕይወት ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ እና ትብብር ሲበዛ ደግሞ ስንፍና እንዲበራከት እና ፈጠራ እንዲቀንስ፤ ለለውጥ ዝግ እንዲሆን እንደሚያደርግ ገልጸው÷ ፉክክር ሲበዛ ወደ ግጭት እና ወደ መጠፋፋት እንደሚያመራ እና ይህም መልሶ ችግር እንደሚፈጥር አመልክተዋል።

የመደመር መንግስት ሙሉ ዕይታ በግልጽ ለመረዳት ሙሉ ዕይታ መኖር፣ የተሰናሰለ ተግባር፣ ገቢር ነበብነት እሳቤ ሊኖረን ይገባል ነው ያሉት።

መደመር በሁሉም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ እሳቤ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የእኛ የሚለየው የነበረንን የመደመር እሳቤ ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ ተንትነን፤ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እሳቤ አድርገን መቀመራችን ነው ሲሉ አብራርተዋል።

የመደመር እሳቤ ሀገር በቀል ነው የምንለው ሁላችንም በዚህ እሳቤ የኖርንበት፣ የሰራንበት እና የቀጠልንበት በመሆኑ እንደሆነ እና ከኢትዮጵያ ውጪ በዝርዝር ‘መደመር’ በሚል መጠሪያ፣ በውጤት እና በሂደት ስለ አንድ ሀገር መንግስትና ኢኮኖሚ ደረጃ በሚያስቀምጠው መልክ የትም ሀገር በንድፍ ደረጃ የሌለ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፋና መረጃዎች ከሌሎች የግል እየታዎች ጋር አንድ ላይ የቀረበ


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የወለኔ አርሶ አደሮች ኅብረት ፓርቲ ዕውቅና ተከለከልኩ አለ፤ የሕግ “ጥሰቶች ፈጽሟል”
በታጣቂዎች [ጎጃም ፋኖ] ታፍነው የከረሙት የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አባል ተገደሉ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2