ታጣቂዎቹ ለቤተሰብ ‘1.6 ሚሊየን ብር ካልከፈላችሁ አንለቀውም’ በማለት ስልክ በተደጋጋሚ በመደወል ይጠይቁ እንደነበርና በኃላም ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ወሰዱ፤ የካውንስሉ ከፍተኛ አመራሮች ታጣቂዎቹ ለቤተሰብ በደወሉበት የስልክ መስመር መልሰው በመደወል ግለሰቡን ለማስለቀቅ ድርድር ሲያደርጉ ቢቆዩም ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።

ሰላም እና እርቅ ለማወረድ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ላይ የነበሩ አባት በታጣቂዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል ሰላም ካውንስል ገለጸ። ” የካውንስሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ “ታጣቂዎቹ የሰላም ካውንስል አባሉን አግተው 1.6 ሚልየን ብር እንዲከፍሉ ለቤተሰቦቻቸው በስልክ ጠይቀው 250 ሺ ብር ከተከፈላቸው በኃላ ስልክ ደውለው ገለናቸዋል ብለዋል ” ብለዋል። ከገዳዮቹ በኩል የተሰማ ነገር የለም። ሟችን የሚያውቁ በተባለው መልኩ ሕይወታቸው ማለፉን መስክረዋል።
በአማራ ክልል ሰላም ካውንስል የሰሜን ጎጃም ዞን የሰላም ካውንስል መሪ የነበሩት መልዓከ ምህረት ነቃጥበብ ገነት በክልሉ የተፈጠረውን የሰላም እጦት በእርቅ እንዲፈታ ሲሠሩ እንደነበር ካውንስሉ ባሳራጨው መግለጫ ገልጿል።
በመግለጫው ችግሮች በሰላም እንዲፈቱም በሕዝባዊ ስብሰባዎች እና በሰላም ጉባኤዎች ላይ ሟች ሲያስተምሩም ነበር ተብሏል።
መልዓከ ምህረት ነቃጥበብ የታጠቁ ኃይሎች ከመንግሥት ጋር እንዲወያዩ፣ ሰላም እንዲሰፍን እና የክልሉ ሕዝብ ስቃይም እንዲያበቃ ሲማጸኑ መቆየታቸውን ያስታወቀው ካውንስሉ፣ በመግለጫው ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር ማስረጃ አቅርቧል።
“የሰላም ዓላማ የሚጻረሩ አካላት ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም ምሽት ላይ እኒህ አባት ከሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታጥቀው በመግባት አፍነው ወስደዋቸዋል” ያለው መግለጫ ክብራቸውን በማይመጥን መልኩ ዳህና ማርያም ወደ ተባለው የታጣቂዎች ምሽግ በመውሰድም ለስቃይ ሲዳርጓቸው መቆየታቸውን ገልጿል። ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም ደግሞ እኒህን ሰላም ወዳድ አባት በግፍ መግደላቸው መታወቁንም አመልክቷል።
የካውንስሉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ዛሬ ለቲክቫህ እንዳሉት መልዓከ ምህረት ነቃጥበብ ገነት ሀምሌ 1 ቀን 2017ዓ.ም የታጠቁ ሀይሎች ከሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ገብተው በመውሰድ ለ1 ወር ከ 5 ቀን ያህል ሲያሰቃዩቸው እንደቆዩ ቆይተዋል።
ታጣቂዎቹ ለቤተሰብ “1.6 ሚሊየን ብር ካልከፈላችሁ አንለቀውም” በማለት ስልክ በተደጋጋሚ በመደወል ይጠይቁ እንደነበርና በኃላም ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር እንደከፈሉ ነው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ያስረዳሉ።
የካውንስሉ ከፍተኛ አመራሮች ታጣቂዎቹ ለቤተሰብ በደወሉበት የስልክ መስመር መልሰው በመደወል ግለሰቡን ለማስለቀቅ ድርድር ሲያደርጉ ቢቆዩም ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ኃላፊው ለቲክቫህ ከተናገሩት ለመረዳት ተችሏል።
የካውንስሉ አመራሮች ከታጣቂዎች ጋር ሲያደርጉት በነበረው ድርድር ታጣቂዎቹ “ስለ ሰላም በቤተክርስቲያን ለምን ይሰብካል ” በሚል እንደያዟቸው አስታውቀው ነበር። ከእገታው እንዲለቀቁ የተጠየቀውን 1.6 ሚልየን ብር መክፈል ግድ እንደሆነ መናገራቸውን አቶ እያቸው ገልፀዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ግድያው መፈጸሙና ለቤተሰብ መነገሩ ተመልክቷል።
መልዓከ ሰላም ነቃጥበብ ገነት በአድባራት እና ገዳማት ለ17 ዓመታት ያገለገሉ መንፈሳዊ አባት፤ ስለሀገርና ስለሕዝባቸው ወቅታዊ ችግርም መፍትሔ ለመፈለግ የበኩላቸውን ጥረት የሚያደርጉ ነበሩ ብሏል ያለው የካውንስሉ በመግለጫ፣ “የእኒህ አባት ግድያ ካውንስሉን ሰላምን ለማስፈን ከሚሠራው አላማው ለአፍታም እንኳን ወደኃላ አይጎትተውም” ብሏል። በሰላም ወዳዱ አባት ግድያ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማውም ካውንስሉ በመግለጫው አስታውቋል።
ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም ደቡብ አቸፈር ዱርቤቴ ከተማ በሚገኘው የሟች የመኖሪያ ቤት በመገኘት የምስለ ቀብር ሥነ ሥርዓት እንደሚካሄድም ካውንስሉ ገልጿል። መግለጫ አያይዞም የሰላም ዋጋ በመስዋዕትነት የሚመጣ መኾኑን ትምህርት ለመስጠት በጋራ መሰለፍ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።


