Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የከፍተኛ መኮንኖች ሹመት ለላቀ ተልዕኮ እንደሆነ ተሰማ፤ ኤርትራ ለአሜሪካ እደራደራለሁ አለች
News

የከፍተኛ መኮንኖች ሹመት ለላቀ ተልዕኮ እንደሆነ ተሰማ፤ ኤርትራ ለአሜሪካ እደራደራለሁ አለች

Ethioreview newsEthioreview news—September 27, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“በቅርቡ ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የተሰጠው የማዕረግ ዕድገት ተጨማሪ ግዳጅ እና ተልዕኮንም ታሳቢ ያደረገ” መሆኑ የአገር መከላከያ የሰው ኃብት አመራር ዋና መመሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ አስታወቁ። የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው በቀይ ባህር ጉዳይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ለአሜሪካ አስታወቁ።

ይህ የተገከጸው ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመና መዘጋጀት ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል ጌትነት አዳነ በጋራ በቅርቡ የተሰጠውን የጦር መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት አስመልክቶ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በተላለፈ ቃለ ምልልስ ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፤ ማናቸውንም የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበርና ለመጠበቅ፣ ይህንንም በማከናወን ረገድ ሊፈጠር የሚችል የደኅንነት አጣብቂኝ በብቃት ለመወጣት በቂ ዝግጅት እንዳለውም በምልልሱ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኒኩሌር ሃይል ግንባታ የመሳሰሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እንዳላት በማስታወሰ፣ በውሃ የመጠቀም መብትና የወደብ ጥያቄን የመሳሰሉ ከፍተኛ ብሔራዊ ጉዳዮች እንዳላት በማስታወስ ስለ አገር መከላከያ ዝግጅት አስፈላጊነት ያወሱት መዘጋጀት ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል ጌትነት አዳነ ተናገሩ።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

መንግስት ስልሳ ስድስት ለሚሆኑ ከፈተኛ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት መስጠቱን ተከትሎ በሻዕቢያ በሚደገፉና በግልጽ በሚታወቁ ግለሰቦች፣ ሚዲያዎች፣ በውጭ አገር ባሉ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች፣ በአክቲቪዝም ስም በሚቀሳቀሱና በግልጽ ሻዕቢያ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተሰላፊዎች ዘንዳ ከፍተኛ ተቃውሞ መሰማቱ አይዘነጋም። ሹመቱ ኤርትራን ለመውጋት እንደሆነ አድርገው የቅሰቀሳ መረጃ ሲያሰራጩ፣ ሹመቱም የአንድ ብሄር አባላት የበዙበት እንደሆነ በማመልከት ከኢህአዴ ጊዜ ጀምሮ በተዋረድ የመጡ ሲኒየር መኮንኖች እንደሆኑ ማስተባበያ ሲሰሰጥም ሰንብቷል።

መከላከያ ሠራዊት ብሔራዊ ጥቅሞችን በማስከበር ሂደት ለሚመጣ የደኅንነት አጣብቂኝ እንደሚዘጋጅ ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን ስታለማና በራሷ ብሄራዊ ትቅም ዙሪያ ስትንቀሳቀስ ለሚገጥማት ተግዳሮት መዘጋጀት እንዳለባት መገለጹ፣ ልክ ” የጦርነት ማስጠንቀቂያ” እንደሆነ አድርገው እነዚሁ ክፍሎች ተደጋጋሚ ፕሮግራም ሰርተዋል። “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉት እነዚሁ ክፍሎች በአደባባይ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መዘጋጀት እንደማያስፈልጋት ሰብከዋል።

የማዕረግ ዕድገት የተሰጠው የመከላከያ ሠራዊት ሕጎች እና አሠራሮች ተጠብቀው እንደሆነ የሠራዊቱ የሰው ኃብት አመራር ዋና መመሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አጫሉ ዝርዝር መረጃ በመስጠት አስታውቀዋል። የማዕረግ ዕድገቱ ሲሰጥ ታሳቢ ከሚደረጉ መስፈርቶች ውስጥ ወታደራዊ ግዳጅ አፈጻጸም፣ የአመራር ችሎታ፣ ብቃትና ሥነ ሥርዓት አክባሪነት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች እንደሆኑም አመልክተዋል።

ሹመቱን የሚያገኙ መኮንኖች ስብጥር “ኢትዮጵያን እንዲመስል” ማድረግ እና ክፍት የሹመት ቦታ መኖርም ከግምት ውስጥ እንዲገቡ ጄነራሉ አምልክተዋል። አክለውም “ሹመት ቀጣይ ሊኖር የሚችለውን ግዳጅ መሸከም እንዲችል ኃላፊነትን ተቀብሎ የመሥራት ጉዳይ” መሆኑን ግልጽ አድርገዋል።

የጦር መኮንኖች ወታደራዊ ሹመት የሚያገኙት “ተጨማሪ ግዳጅ እና ተልዕኮ መሸከም እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ” እንደሆነም ገልጸዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የብርጋዴር ጄነራል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው፤ የተሰጠው ሹመት የሠራዊቱን ዝግጁነት እንደሚያጠነክር እና ለወደፊት ተልዕኮ በጎ ተጽእኖ እንደሚፈጥር አንስተዋል። በሌላ ቋንቋ የተሰጠው ከፍተኛ ሹመት ስነልቦና የሚገነባ፣ ለበለጠ ኃላፊነት የሚያነሳሳ መሆኑን ገልጸዋል።

የማዕረግ ዕድገቱ “ከብሔራዊ ጥቅም” እና “ሉዐላዊነትን ከማጽናት” አንጻርም መታየት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት መንግሥት “ብሔራዊ ጥቅም” በሚል በአጀንዳነት ያቀረባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፤ ከእነዚህም መካከል በውሃ የመጠቀም መብት እና የወደብ ጥያቄ እንደሚገኙበት አመክተዋል።

“ጋዝ፣ የኒውክሌር ማብላያ ፕላንት፣ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች መመሥረት” ጉዳዮችም ከአጀንዳዎቹ መካከል እንደሆኑ አንስተዋል። ብርጋዴር ጄነራል ጌትነት፤ “በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እነዚህን ብሔራዊ ጥቅሞችን ‘እነዚህ ናቸው ላሳካቸው የምፈልገው’ እስካለ ድረስ ሠራዊት ደግሞ መዘጋጀት አለበት” ብለዋል።

ሠራዊቱ የሚያደርገው የመጀመሪያ ዝግጅት አንጀንዳዎቹን በማስፈጸም ሂደት ውስጥ በሌላ አካል ሊፈጠር ከሚችል ወደ ኃይል አማራጭ የመምጣት አዝማሚያ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ይህንን ጥያቄ ሲያነሳ ‘በሰላማላዊ መልኩ እፈታዋለሁ’ ብሎ ነው የሚያነሳው። ግን ደግሞ በዚህ ውስጥ የሚገባ security dilemma የሚባል ነገር አለ” ሲሉ በሂደቱ የደኅንነት አጣብቂኝ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቁመዋል።

” ‘ኢትዮጵያ ይህንን ካነሳችማ እንዲህ ሊሆን ነው’ ብሎ ወደ ኃይል አማራጭ የሚመጣ ነገር ከሆነ ሠራዊት መዘጋጀት አለበት ማለት ነው” ሲሉም ሐሳባቸውን አብራርተዋል።

በሠራዊቱ በኩል የሚደረገው ዝግጅትም “የመንግሥትን ተልዕኮ እና ትዕዛዝ ያከበረ” እንደሚሆንም አያይዘው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት መስከረም 6/2018 ዓ.ም. ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ “የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም” እንደማትኖር መናገራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ “አይቀሬ” መሆኑን በአጽንኦት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጉዳዩ የሚመለክታቸው አገራት “በፈጠነ ጊዜ ራሳቸውን ለድርድር ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስባለሁ” ማለታቸው አይዘነጋም።

ከለወጡ በሁዋላ በብዛት፣ በጥራት፣ በትጥቅ፣ በዓይነት ራሱን በአየር፣ በመድርና በባህር ኃይል ያበቃው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አቅም በቀጣናው አስፈሪ መሆኑን ተከትሎ በቀጣናው ሰፊ ኃላፊነት በመቀበል ላይ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

በተለይም በቀይ ባህር ላይ ስጋት ያላቸው ኃያላን አገራት፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር እንድትገባ ድጋፍ በሚሰጡበት ወቅት ኤርትራ ለድርድር ዝግጁ መሆኗን ማስታወቋ ተሰምቷል።

“በአፍሪካ ቀንድ ፣ በቀይ ባህር ፣ በናይል ተፋሰስ ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ” መሆኗን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦስማን ሳሌህ ናቸው የተናገሩት። ኦስማን ሳሌህ ይህን ማለታቸው በተደጋጋሚ ለመነጋገር ጥያቄ ለመታቀርበው ኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ በቲውተር ገጻቸው “የምን ድርድር” በሚል ሲረጩት ከነበረርው ምላሽ ጋር የተቃረነ ሆኗል።

በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግሥታት (UN) ጉባኤ ላይ ሆነው በጎንዮሽ ከኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ይህ የተባለው።

በውይይት ኢትዮጵያ ግልጽ ያደረገችው የቀይ ባህር ጉዳይ የተነሳ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ሀገራቸው ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን በጠበቀ ሁኔታ በጋራ ጉዳዮች ላይ በተለም በአፍሪካ ቀንድ ፣ በናይል ተፋሰስ፣ በቀይ ባህር  ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ማሳድ ቦሎስ  ሀገራቸው አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ንግድ፣ ደህንነት እና ፀረ-ሽብርተኝነት ጥረቶች ወሳኝ በሆነ ቀጠና ውስጥ ውይይት እና መግባባትን ለመፍጠር ፅኑ ፍላጎት እንዳላት አስምረውበታል።

ኤርትራ አጋጣሚውን ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት ለማደስ እንደምትጠቀምበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። አሜሪካም በተመሳሳይ ከኤርትራ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች ተብሏል።

ኤርትራ ለዝግጅት ክፍት መሆኗን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ በኩል የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በህግ፣ በዓለም ዓቀፍ አጋብቦችና የባህር በሯን ስትነጠቅ በነበሩ አስቻይ ያልሆኑ ህገ ወጥ አካሄዶችን ሳቢያ መብቷን ማታቷን በማንሳት የተፈጠረው የታሪክ ስብራት የሁለቱንም ሕዝብና አገራት በማይጎዳ መልኩ ለማስፈጸም እንደምትሰራ ደጋግማ ማስታወቋ አይዘነጋም።

በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ የኢትዮጵያን ፍላጎት ከዓለም ዓቀፍ ህግ አንጻር ቀይ ባህር ብቻ ሳይሆን እስከ ህንድ ውቅያኖስ መጠቀም ሊከለከል እንደማይገባ ጠቅሰው ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም፣ ተዘገታ መኖር አለባት” የሚሉት በስም “ኢትዮጵያዊ” የሚባሉ ቡድኖችና ግለሰቦች የኤርትራን አዲስ አቋም አስመልክቶ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያሉት ነገር የለም።

የኤርትራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነጋገሩት የአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ማሳድ ቦሎስ አዲስ አበባ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መምክራቸው አይዘነጋም። በምክክራቸውን በተመሳሳይ ጉዳይና በቀተናው እንዲሁም በቀይ ባህር ጸጥታ ዙሪያ ገንቢ ውይይት ማደራግቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል። ይህ ውይይት የዚያ ቀታይ እንደሆነም ይታመናል።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የቡርጂ ዞን ትልቅ የሀገር ሽማግሌ በታጣቂዎች ተገደሉ
California Man Wrongfully Imprisoned for 38 Years to Receive $25 Million Settlement
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2