በቅርቡ “ሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ” በሚል የተቋቋመውን የትይዩ መንግስት በሊቀመንበር የሚመሩት ሌተና ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የህዳሴ ግድብ በመተናቀቁ “ተደስተናል” ሲሉ በይፋ አስታወቁ። በምስራቅ አፍሪቃ ደስታቸውን ያልገለጹት በግብጽ የሚደገፉት አል ቡርሃንና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ብቻ ናቸው። አንዳርጋቸው “ግድቡ መገንባት አልነበረበትም ፣ግብጽና ሱዳንን እናስቆጣለን፣ የዲፕሎማሲ ቀውስ ያጋጥመናል” ሲሉ ሚናቸውን ይፋ አድርገዋል።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ዋና አዛዥ ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ባለፈው ዓመት መገባደጃ የተመረቀውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ መመረቅ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት እሳቸው በሚመሩት የሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ መንግስት ስም ዛሬ ባተሰራጨ መግለጫ ነው።
“በህዳሴው ግድብ መተናቀርቅ ተደስተናል” የሚለው በሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ ስም ዛሬ የተሰራጨው መግለጫ፣ “የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለአገሪቱ እድገት ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያ በራስ መተማመንና ዘላቂ ልማት ምልክትም በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንፈልጋለን” ብሏል።
አቶ አንዳርጋቸው በሻዕቢያ በሚደገፈውና እሳቸው ከሻዕቢያ በሚወስዱት መመሪያ መሰረት አቅጣጫ በሚያስቀመጡለት አንከር ሚዲያ “ደለ ይሞላዋል” በሚል ሲይራክሱት የዋሉትን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጀነራሉ የሚመሩት የትይዩ መንግስት ” ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ሀብትን የመጠቀም ብሄራዊ ፍላጎትን እንደሚያንፀባርቅ አሳይቷል” በማለት በክህደት ለቆሙ “ኢትዮጵያዊያ ነን” ከሚሉት በላይ በመግለጫው ስሜት የሚገዛ አሳብ አስፍሯል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሁሉም የአባይ ተፋሰስ አገራት መካከል ያለብዝበዛና ያለመድልኦ ትብብር እንዲፈጠር ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግል ተስፋ የትይዩ መነግስቱ ተስፋ እንዳለው በመግለጫው ተመልክቷል። አክሎም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አፍሪካዊያን ስኬታማ ፕሮጀክትን ሰርተው የማጠናቀቅ ብቃት እንዳላቸው ያስመሰከረ መሆኑ አጉልቷል።
የሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ የትይዩ መንግስት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ሀይልና የማደግ ፍላጎት የሚጨምር ብቻም ሳይሆን በቀጣናውና በመላው አፍሪካ ትብብርን፣ አብሮ መስራትንና መቀናጀትን የሚያስተዋውቅ ሆኖ እንዳገኘው አመልክቷል።
በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው ሌላላኛው መንግስት በግብጽ የሚረዳና በግብጽ የሚመራ በመሆኑ ይሁን በሌላ ምክንያት ይህ እስከታተመ ድረስ ምንም ያለው ነገር የለም
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ራሱን የሚጠራው ትህነግም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ልክ እንደ ሻዕቢያና አልቡርሃን ግድቡን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም። የትግራይ ሕዝብ ኝ ከተለያዩ ወረዳና ከተሞች ደታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። አሁን ድረስም እየገለጹ ነው።
አቶ አንዳርጋቸው በጻፉት ጽሁፍ ልዩነታችን ገና ግድቡ ሳይሰራ ነው። ትልቅ ግድብ ሊሰራ አይገባም ነበር። ትንሽ ግድብ ነበር መሰራት ያለበት፤ ተቃውሞሟችን ግድቡ ወጪው ብዙ ነው የሚል መሆኑንና ጭራሹኑ ግድቡ መገንባት አልነበረበትም ሲሉ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።ንሲገነባም “ግብጽና ሱዳንን እናስቆጣለን፣ የዲፕሎማሲ ቀውስ ያጋጥመናል” ሲሉ የህዳሴውን ግድብ ተቃውመዋል።


