ድርጅታቸው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት / ትህነግ የህዳሴው ግድብ ተጠናቆ መመረቁን ተከትሎ ምንም አላለም፤ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን “እንኳን ደስ አለን” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አሕመድን “እናመሰግናለን” ብለዋቸዋል።
እስከ 2017 የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው የሚቀጥሉት ዶክተር ቴዎድሮስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲያመስኙ አቶ መለስ ዜናዊን ” ፕሮጀክቱን ለመጀመር ባሳዩት ራዕይ እና ድፍረት እናስታውሳለን” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” አስደናቂ ክስተት” ሲሉ የጠሩትን የህዳሴ ግድብ በማጠናቀቃቸው “እናምሰግናለን” ያሉት ዶክተር ቴዎድሮስ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን አላነሱም። አቶ ኃይለማሪያም ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ቴዎድሮስ አድሃኖም ቦታውን ለመያዝ ሞክረው አለመሳካቱን የሚያስታውሱ ምን አልባትም ከዚያ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ይገምታሉ።
ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻች እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ በዓል አደረሳችሁ! የዚህ አስደናቂ ክስተት አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፕሮጀክቱን ለመጀመር ባሳዩት ራዕይ እና ድፍረት እናስታውሳሸዋለን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ፕሮጀክቱን ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን።
ዶክተር ቴዎድሮስ የእንኳን ደስ ያለን መልዕክት ሲያስተላልፉ እሳቸው የውጭ ጉዳይ በነበሩበት ወቅት በዲሰምበር 9 ቀን 2014 የሱዳኑን መሪ አልበሽርንና የጅቡቲውን መሪ ኢስማኤል ጊሌን ፕሮጀክቱ ዘንድ በመውሰድ ማስጎብኘታቸውን ጠቅሰው በፌስ ቡክ ያሰራጩትን መልዕክትና ፎቶም አባሪ አድርገው አቅርበዋል። የዚህ አስደናቂ ክስትተ አካል በመሆናቸው መደሰታቸውንም አመልክተዋል።
በዚሁ የቆየው ልጥፋቸው በወቅቱ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 42% መድረሱን አመልክተዋል። እሳቸው ያሉበት መንግስትና ድርጅታቸው በይፋ ፕሮጀክቱ በሰባት ዓመት እንደሚተናቀቅ በጋራና በግል በየወቅቱ ሲናገሩ እንደነበር የሚያስታውሱ፣ ቴዎድሮስ ዛሬ ላይ ሆነው በ2014 አሰራጭተውት በነበረው ልጥፍ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 42% መድረሱን በድጋሚ ለማስታወስ መድፈራቸውን አንዳንዶች በጥያቄ መልክ አቅርበዋል።
እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸው የፕሮጀክቱ ዋና መሪ ኢንጂነር ስመኘው የግድቡን አፈጻጸም በተመለከተ ሲሰጡት የነበረው መረጃ የተሳሳተና ሕዝብን ያታለለ እንደነበር የጠቀሱ፣ ፕሮጀክቱ ላይ በተሰራ ደባ ኢትዮጵያ 460 ሚሊዮን ፓውንድ መክፈሏ፣ አብዛኛው ግንባታ ፈርሶ በአዲስ መሰራቱና ፣ ፕሮጀክቱ በሌብነት ዳዋ የመታው መሆኑ በመረጃ ቀርቦ ሳለ ዶክተር አድሃኖም ዛሬም 42% በሚለው መረጃቸው ላይ መቆማቸው አስወርፏቸዋል። ያም ቢሆን ግን ለማመስገን የወሰዱትን ተነሳሽነት ብዙዎች አድንቀዋል።
ፓርቲያቸው ትህነግ በድርጅት ደረጃም ሆነ በመሪ ደረጃ ምንም ሳይል እሳቸው አስደባባይ ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዕውቅና መስጠታቸው በበጎ ተወስዶላቸዋል።
የህዳሴው ግድብ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ ሰባት ዓመት አሳልፎ በአስራ አራተኛ ዓመቱ ለመመረቅ መብቃቱ ደስታ የፈጠረውን ያህል ሌላም ቁጭት ማስነሳቱ ፕሮጀክቱን በመሩትና ባስፈጸሙት ባለሙያዎች እየተነሳ ነው።
ኃላፊነት በሚሰማው አመራር ፕሮጀክቶ ብቃት ላላቸው ባለሙያዎችና ተቋም ባለመሰጠቱ አገር 460 ሚሊዮን ዩሮ ከስራለች። ምንም እንኳን የተጠየቀው ኪሳራ አንድ ቢሊዮን ዩሮ ቢሆንም በድርድር የተከፈለው 460 ሚሊዮን ዩሮ ብቻ ነው። ይህ ገንዘብ ጣና በለስ ሲሰራ ከወጣው ወጪ እኩል መሆኑን የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያኪጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታውቀዋል። እሳቸው ቀደም ሲል የጣና በለስ ፕሮጀክት መሪ እንደነበሩ አይዘነጋም።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር ስለሚያስገባ፣ ሰባት ዓመት መዘግየቱ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ሰባት ቢሊዮን ዶላር አሳጥቷታል። ይህን መረጃ ዶክተር ቴዎድሮስም ሆነ ድርጅታቸው ትህነግ ጠንቀቀው እንደሚያውቁት የገለጹ፣ ወደፊት ህዳሴን አስመልክቶ ይፋ የሚሆኑ ዝርዝር መረጃዎች የደስታውን ያህል በርካታ ልብ የሚነኩ ጉዳዮእች እንደሚወጡበት ጥርጥር የላቸውም።
በሌላ በኩል ከሻዕቢያ ጋር በይፋ ግንኙነት የጀመረው ትህነግ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ዝም ማለቱ አስገርሟል። ትህነግ የድርጅቱ መሪ ያስጀመሩት ግድብ ሲጠናቀቅ ዝምታን መምረጡ ምን አልባትም ከሻዕቢይና በሻዕቢያ በኩል ከግብጽ ጋር የመሰርተተውን ግንኙነት ሊያበላሽበት ስለሚችል ሊሆን እንደሚችል አስተያየት እየተሰጠ ነው።
“ኢትዮጵያዊው፣ የኢትዮጵያን በጀት የሚበላው ትህነግ ዝም ሲል፣ ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ‹‹በህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ተደስተናል›› ማለታቸው ጉዳዩን እሳዛኝ አድርጎታል። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ዋና አዛዥ የሆኑትና በቅርቡ የተመሰረተው ‹‹ሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ› መሪ በህዳሴው ግድብ መመረቅ ደስታቸውን ከገለጹ በሁዋላም ትህነግ ያለው ነገር የለም።
ግብጽ ሰሞኑን ይበጃል የምትለውን ውሳኔ ለማሳለፉ ጉዳዩን ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ወስዳለች። ሻዕቢያ እንደሚከፍላቸውና አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥላቸው የሚታወቁ “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ የሚዲያ አክቲቪስቶች ” የህዳሴ ግድብ ፕሮፓጋንዳ ነው፤ አሁን ደግሞ ወደ አሰብ ተዙሯል” በማለት ጠያቂና ተጠያቂ እያዘጋጁ በመኮነን ላይ ናቸው።
ከሻዕቢያ ውክልና ወስደው የፋኖን ትግል እንደሚመሩና ዕቅድ በማውጣት እንደሚያሰማሩ የሚታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ” ግድቡ ደለል ይሞላዋል፤ ዋጋ ቢስ ነው” የሚል አስተያየት በአርበኛ መሳይ ዩቲዩብ አማካይነት ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ የአቶ አንዳርጋቸው ማናናቂያ ግብጽ ምንም ውሃ ሳይጓደልባት “ደለል ቀረብኝ” በሚል ከምታሰማው ጩኸት ጋር መመሳሰሉ “አይ መናበብ” አሰኝቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አባይ ውሃና አፈር ብቻ ሳይሆን ወቅን ጨምሮ የተለያዩ ማዕድናት ያግዝ እንደነበር ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አሁን ላይ ይህ መቅረቱን ለመቃወም አቶ አንዳርጋቸው “ደለሉ ይለቀቅ” ዓይነት ይዘት ያለው ድምጽ ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል። ለዚህ ነው የዶክተር ቴዊድሮስ ምስጋናና እውቅና በበጎነት ብቻ ሳይሂን ሊለመድ የሚገባው አግባብ እንደሆነ ተጠቅሶ አስተያየት የተሰጠበት።

