ኢትዮጵያ የባህር በሯንና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዋን ከተነጠቀች ከሶስት አስርት ዓመታት በሁዋላ አዲስ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመሯ ይፋ ሆነ። ዜናው ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትርና የዘርፉ ሚኒስትሮች ይህ እንደሚሆን ሲያስታውቁ ባጣጣሉና “ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው” በማለት ሲያስተጋቡ በነበሩ ቡድኖች ዘንዳ በይፋ ተቃውሞ አልተነሳበትም።

ኢትዮጵያ በግፍተላልፎ ለማይገባቸው ታሪካዊ ተላቶቿ ከተሰጥጡት ሃብቶቿ መካከል አእሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ንጉስ አጼ ሃይለስላሴ ዘመን የተሰራ ትልቅ ፕሮጀክት ቢኖር አሰብ ነዳጅ ማጣሪ ነው። በፈረንጆች ቀን አቆጣጠር በ1964 ተጀመሮ በ1967 ተጠናቆ ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት ስራ ጀምሯል። የአሰብ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ በዮጎዝላቪያ እና ሶቬት ህብረት ትብብር የተሰራ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ነው።
“በፍጥነት፣ በጥራትና በከፍታ” የሚል መርህ በመላ አገሪቱ እየተከሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል” በማለት መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም ዜናውን አብስረዋስል።
በተለያዩ ወቅቶች መጀመሩንና መቋረጡን ፣ ውል እየታሰረ መፍረሱ በወፍ በረር ከመዘገቡ በቀር በቂ መረጃ እንኳን የማይቀርበበት የነዳጅ ድፍድፍ ፍለጋ መስመር መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶስት ዓመት በፊት ፍንጭ ሰጥተው ነበር። በቅርቡም ሙከራ መደረጉን አስታውቀው ነበር።
ዜናውን “ተራ ፕሮፓጋንዳና የአቅጣጫ ማስቀየሻ የሃሰት ዜና” በማለት በተቃውሞ ሰልፍ ውስጥ ያሉ የሚታወቁ ሚዲያዎችና ባለቤውቶቻቸው ሲያጣጥሉ እንደነበር የሚታወስ ነው። በአገር ቤትም ሆነው የሚሰሩ አንድንድ ሚዲያዎች ዜናውን ወደ ወደቀው ኢህአዴግ በመጎተት ስልታዊ የማንቋሸሽ ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “እነሱ ያወራሉ፣ እኛ እንሰራለን” በማለት እንዳስታወቁት ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት የተያዙት ፕሮጀክቶች እንዲሁ ለስም ብቻ ሳይሆን በተያዘላቸው ጊዜ የሜመረቁ እንደሆነ አመልክተዋል። ኢትዮጵያዊያንንም ” እስራ፣ እንትጋ” ሲሉ ከድህነት ማምለጫው ዋናው ጉዳይ ይኸው ትጋት መሆኑን አመላክተዋል።
በሱማሌ ክልል ሲካሄድ በቆየው የነዳጅ ፍለጋ መሰረት ኢላላ በተባለ የቁፋሮ ቦታ የተገኘውን ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ ስራ ከተቆፈሩት ስምንት ጉድጓዶች መካከል በሶስቱ ድፍድፍ ነዳጅ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያስታውቁ ያጣጣሉ ሚዲያዎች ይህ እስከተጻፈ ድረስ አላስተባበሉም።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የድፍድፍ ነዳጅ ማምረት ሙከራ እደምትጀምር ሲበሰር፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋም ስኬታማ በመሆኑ በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑ ከተጠቀሰ በሁዋላ ዛሬ የነዳጅ ድፍድፍ ማጣሪያ ፋብሪካ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጧ ለክ እንደ አባይ ግድብ የዓለም ዜና ሆኗል።
ቀደም ሲል “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ግድብን ሸጡት” በሚል በገሃድ የዘገቡ ሚዲያዎችና የሚታወቁ “ጋዜጠኞች” ግድቡ ተመርቆ “ኢትዮጵያ ግብጽን ረታች” በሚል ዓለም ዜናውን በአድናቆት ሲቀባበለው እነዚህ ወገኖች ማስተካከያ ወይም ይቅርታ አልጠየቁም።
በጎዴ የሚገነባው የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ከሂላል የነዳጅ ድፍድፍ ማምረቻ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በዓመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም እንዳለው አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ዜናውን በዝርዝር ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ እርስ በርስ የሚደረገው ግብግብ ይቆም ዘንድ እግረመንገዳቸውን አመልክተዋል።


