Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ማህደር  “ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

Ethioreview newsEthioreview news—October 4, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዋቄፈና የቀደምት ኦሮሞ ሕዝቦች እምነት ሲሆን የእምነቱ ተከታዩች ሁሉን በፈጠረ አንድ አምላክ እንደሚያምኑ ይናገራሉ።

አቶ አስናቀ ተሾመ ኢርኮ፣ ላለፉት 20 ዓመታት ስለ ዋቄፈና እምነት አጥንተዋል። አሁንም በዓለም አቀፍ የዋቄፈና እምነት ምክር ቤት በአመራርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በዋቄፈና እምነት ዙሪያ የአገር ሽማግሌዎች እና ካደረጉት ጥናት የተረዱትን ለቢቢሲ እንዲህ በማለት አካፍለዋል።

አቶ አስናቀ ቦረና አካባቢ በመሄድ ጥናታቸውን እንዳደረጉ ገልፀው “ፈጣሪ ስሙ መቶ፣ ሆዱ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ፣ ሃሳቡ ደግሞ ንጹህ ነው፤” ድሮ ድሮ ሰው ሃጥያት መስራት ሳይጀምር በፊት የፈጣሪን ድምጽ የሰሙ ሰዎች ነበሩ ይባላል ይላሉ።

ስሙ መቶ ነው የሚለው ደግሞ ፈጣሪ “አንድ” እና ከሁሉ በላይ የሆነ መሆኑን እና ሀይማኖቶች ወይንም እምነቶች ግን ብዙ መሆናቸውን ለማሳየት መሆኑን አቶ አስናቀ ያብራራሉ።

More stories

ኢትዮጵያ የተነጠቀችውን የባህር በሯን አስመልሳ ስታስመረቅ ንጉሰ ነገስቱ የተናገሩት …

March 26, 2025

ደበበ ሰይፉ – የኪነት ፀሐይ

November 27, 2024

 የዳውሮ ባለውለታ- ያልተነገሩ ትጋቶች

May 22, 2025

የኢትዮጵያ ልጅ የሜጄር ጄኔራል ሁሴን አህመድ ሲታወሱ

June 23, 2025

ይሁንና ፈጣሪን በዓይኑ ያየው ሰው የለም በማለት ነው ኦሮሞ የሚያምነው ሲሉ ያስረዳሉ። ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል።

የኦሮሞ ፈጣሪ ጥቁር ነው ስንል ግን ይኼ የሚታየውን መልክ ወይም የቀለም ጉዳይ ሳይሆን፣ “ፈጣሪ ጥልቅ ነው፤ ፈጣሪን ማየት፤ መለየት አይቻልም የሚለውን ለመግለጽ ነው። ማንም ተመራምሮ ሊደርስበት አይችልም።” ብለዋል።

“ፈጣሪ ምስጢር ነው፤ ከሰው አእምሮ በላይ ነው የሚለውን ለማሳየት ነው በጥቁር መልክ የሚገለፀው።”

ዘፍጥረት

እንደ ዋቄፈና እምነት፤ ፈጣሪ ሁሉን ነገር የፈጠረው በቀደመ ዘመን ከነበረ ውሃ እንደሆነ ይታመናል። ፈጣሪም ይህንንም ውሃ ‘የላይኛውና የታችኛው ውሃ’ በማለት ለሁለት ከፈለው የሚሉት አቶ አስናቀ፣ የላይኛው ውሃ ጠፈር ውስጥ የሚገኙ አካላትን ሰማይን እንዲሁም ፀሀይንና ከዋክብትን ይይዛል።

የታችኛው ውሃ ደግሞ፣ የውሃ አካላትን እንደ ውቅያኖስ፣ ባህርን፣ ደረቅ መሬትን ይይዛል።

ዋቄፈና በዚህ ምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ በ27 ቀናት ተፈጠሩ ብሎ ነው የሚያምነው።

መጀመሪያ ሰውን ፈጠረ፣ ከዚያም ወንድና ሴት ብሎ እኩል ለሁለት ከፈላቸው። ሌሎች ፍጥረቶችንና ተክሎችን እንደዚሁ በቅደም ተከተል ፈጠራቸው።

ፈጣሪ ምድርን ሲፈጥር ሰው በስነ-ስርዓት እንዲኖር ሕግንም አብሮ ፈጠረ። እነዚህም ሕጎች የሰው ሕግ፣ የከብቶች ሕግ፣ የፈረሶች ሕግ፣ የዱር አራዊት ሕግ፣ የእጽዋትና የፀሀይና የከዋክብት ሕግ ይሰኛሉ።

‘ሰፉ’ የማይቀየር የፈጣሪ ሕግ ነው። ይህም ክልክል የሆኑትን ሰውን መግደል፣ መስረቅ፣ ዝሙት እና መዋሸትን ተላልፎ መገኘት ነው።

ፈጣሪን፣ ምድርን እንዲሁም ሌሎችን ፍጥረቶች ሁሉ ማክበር የፈጣሪን ሕግ መጠበቅ ነው።

ክልከላዎች ‘ለጉ’ የሚባሉት የማህበረሰቡን አይነኬ ተግባራት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። አንድ ሰው ሀጥያት ሰራ የሚባለው እነዚህን የፈጣሪን ሕግና ክልከላዎች ሲጥስ/ ሲተላለፍ ነው።

የኦሮሞ ሴቶች ባህላዊ ዘፈን እየዘፈኑ

ከሞት በኋላ ሕይወት?

ቀደምት የኦሮሞ ሕዝቦች ሰው ሲሞት ነፍሱ ወደ ፈጣሪ ወይንም ደግሞ ወደ እውነት ቦታ ትሄዳለች ብለው ነው የሚያምኑት። እንደ ዋቄፈና እምነት ሰው ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከእሳት እና ከአፈር በአንድ ላይ ተበጅቷል።

ስለዚህ ሰው ሲሞት አካሉ ከአፈር ይቀላቀላል፣ ደሙ ወደ ውሃ ይሰርጋል። ነፍሱ ደግሞ ወደ ፈጣሪው ይሄዳል።

“እንደ ሌሎች እምነቶች ዋቄፈና ሰው ከሞተ በኋላ ይነሳል ወይንም በሕይወት ይኖራል ብሎ አያምንም። እንዲሁም በሴጣን መኖርና ፈጣሪን የሚገዳደር ሌላ ኃይል አለ ብሎ አያምንም። ሰዎችንም ኃጥያት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው ኃይል የለም ብሎ ነው የሚያምነው” ይላሉ አቶ አስናቀ።

ይኹን እንጂ “ክፉ መንፈስ አለ ብሎ ያምናል” በማለት፣ ሰው የማይቀየረውን የፈጣሪን ሕግ ከተላለፈ፣ ስለሚጠየቅ እና ርግማንም ወደ ሰባት ትውልዱ ስለሚተላለፍ ኃጥያት መስራት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ሕዝቡም ይህንን ይፈራል።

ለምሳሌ አንድ ሰው፣ ነፍስ አጥፍቶ ሳይናገር ከሞተ በፈጣሪ ዘንድ ስለሚጠየቅ ቤተሰቦቹ ወይንም ዘመዶቹ የሙት መንፈስን የሚያናግሩ “አዋቂዎች” ዘንድ ይሄዱና ካሳውን “ልክ በሕይወት እንዳለ ሰው” ይጠይቃሉ።

በዚህ እምነት ገሃነም ወይንም ገነት የሚባል ነገር የለም። እንዲህ ማለት ግን ሰው የፈለገውን እያደረገ ይኖራል ማለት አይደለም። በእነዚያ በፈጣሪ በማይቀረው ሕግ ስር መመላለስ አለበት።

በዚህ መንገድም በፍጥረታት እና በሰዎች መካከል ያለ ሚዛን ተጠብቆ በሰላም መኖር ይቻላል ብሎ ያምናል፤ ዋቄፈና።

አቶ ተሻገር የአገር ሽማግሌዎች ‘እዳየነው እንደሰማነው’ በማለት ሲናገሩ፣ ኦሮሞ ፈጣሪን ሴት ወይንም ወንድ ብሎ ለይቶ አይጠራም። ነገር ግን ሲጠሩት በወንድ ጾታ ነው። ይህ ግን ጾታውን ለማመለክት አለመሆኑን.ይናገራሉ።

የኦሮሞ ወጣቶች ባህላዊ አልባሳት ለብሰው

የዋቄፈና እምነት ተከታዮች

አቶ ደሳለኝ ደሜ በቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ የዋቄፈና ቤተ እምነት “ዋዩ” ናቸው።

ዋዩ ማለት የዋቄፈና ቤተ እምነት ውስጥ ያሉ የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚሰበስብና የሚመራ ሰው ነው።

አቶ ደሳለኝ ዋቄፈና ከአባቶቻችን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ እምነት ቢሆንም፣ እኛ የአሁኖቹ ትውልዶች ደግሞ ስርዓት እና ባህሉን ሳይለቅ ለአሁኑ ዘመን በሚመች መልኩ በ1990ዎቹ ቤተ እምነት መስርተን ኃይማኖቱን አቋቁመናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

እኛ እንደ እምነታችን ሁሉን በልጦ የሚያስተምር መምህር የለንም ያሉት አቶ ደሳለኝ ደሜ፣ ምክንያቱን ሲያስረዱ ስለዚህ እምነት ጉዳይ ሁሉም ከአባቱ ወርሶ ተምሮ መምጣቱን ይጠቅሳሉ።

ይሁን እንጂ የውይይት ጥላ የሚባል ዝግጅት እንዳላቸው ገልፀዋል። በዚያም ስለፈጣሪ ተነጋግረን ፈጣሪን ለምነን እንገባለን ሲሉም ያክላሉ።

“በአጠቃላይ ግን እምነቱን በበላይነት የሚመራው ‘ቃሉ’ ነው።”

በአሁኑ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ ብቻ አራት የዋቄፈና ቤተ እምነቶች አሉ። ከቢሾፍቱ በተጨማሪ በአዳማ፣ ባቱ ፣ ሰበታ እና ወሊሶ እንዲሁ ቤተ እምነቶች ይገኛሉ።

በየዓመቱ ደግሞ አንድ ቤተ እምነት እንደ ክብረ በዓል ያዘጋጅና ሁሉም በአንድነት ያከብራሉ።

የሆረ አርሰዴ ቤተ እምነት በግምት ከ5000 በላይ አባላት እንዳሉት አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። አብዛኛዎቹ አባላት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሰራተኞችና በተለያየ የኑሮና የስራ ዘርፍ የሚገኙ ሰዎችም አባላት ናቸው።

የዋቄፈና የአምልኮ መርሃ ግብር

ቤተ እምነቱ ሁሌም ለሁሉም ሰው ክፍት ቢሆንም ዘወትር እሁድ ግን አባላቶች በአንድነት ተገናኝተው የአምልኮ ስነ ስርዓት ያካሄዳሉ።

ጠዋት ሲገናኙ ማንኛውም ስነ ስርዓት ከመጀመሩ በፊት አንዱ ለአንዱ ይቅርታ የማድረግ ስርዓት ይፈፀማል።

“በዚያ ቤተ እምነት ውስጥ የሚገኝ ሰው እርቀ ሰላም ካላወረደ፣ ፈጣሪ አይሰማም ተብሎ ስለሚታመን እርቀ ሰላም ይቀድማል” የሚሉት አቶ ደሳለኝ፣ ከዚህ በመቀጠል በእድሜ ታላቅ የሆኑ እና አካባቢን መሰረት በማድረግ የምርቃት ስነ ስርዓት መርሃ ግብር ይካሄዳል።

ከዚህ በኋላ ዋቄፈናን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት በውይይቱ ጥላ ስር ያሉ አባላቶች ይማማራሉ።

አሁን ፀሎትና ምስጋና ይቀጥላል። በዚህም ጊዜ የቡና ማፍላት ስርዓት ይከናወናል። የታመመ ሰው ይፀለይለታል፤ ቤተሰቦቹ የፈጣሪን ሕግ ጥሰው ከሆነ ፈጣሪ እንዲታረቃቸው ይለመናል።

ከዚህ በፊት ፀሎታቸው የተመለሰላቸው ሰዎች ካሉ ደግሞ ምስጋና ያቀርባሉ።

በዚህ ሁሉ መካከል ‘ጄከርሳ’ መዝሙር ይዘመራል።

ይህ መዝሙር በስነ ስርዓቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ከመጨረሻው መዝሙር በፊት ግን አንድ “ባልቻ” የሚባል የመባ መስጠት ስርዓት ይካሄዳል።

ይህ ስርዓት የቤተ እምነቱ አባል የሆነ ሰው የገንዘብ የሃሳብና የንብረት ድጋፍ የሚያደርግበት ነው።

በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት በኩል እውቅና የማግኘትና የአምልኮ ስፍራ ለማግኘት ትልቅ ችግር እንዳለባቸው አቶ ደሳለኝ ጨምረው አስረድተዋል።

ምስጋና ቢቢሲ አማርኛ


archive
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢትዮጵያ የነዳጅ ድፍድፍ ማጣሪያና ግንባታ አስጀመረች፤ በዓመት 3.5 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ያመርታል
በመካነ ሰላም መስጂድ ታጣቂዎች ሰላት ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸኑዋቸው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 2025
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 2025
ማህደር

ደበበ እሸቱ (1934-2017 ዓ.ም)

August 24, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2