Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ትህነግ በጣማራ ስድስ ኮር ያሰለፈበት ውጊያ ለጊዜው በበቃኝ ተጠናቀቀ፤ በራያ አላማጣ መስመርና በጨርጨር ሙሉ ጦርነት…
News

ትህነግ በጣማራ ስድስ ኮር ያሰለፈበት ውጊያ ለጊዜው በበቃኝ ተጠናቀቀ፤ በራያ አላማጣ መስመርና በጨርጨር ሙሉ ጦርነት…

Ethioreview newsEthioreview news—January 29, 2026
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የፕሪቶሪያው ስምምነት በትህነግ በኩል መፍረሱን የትግራይ ተቃዋሚ ፓሪዎች አስታወቁ፤ ትግራይን የጦር ማዕከል የሚያደርገው የሻዕቢያ ዕቅድ ተግባራዊ መሆኑ በትግራይ ዳግም ቀውስ አስነሳ፤ አፈሳና ሽሽት መጀመሩ ተነገረ።

  • ያለፈውን ጦርነት የሚያስታውሱ “ጦርነትን ተቃወሙ፣ ጦርነትን እምቢ በሉ “ የሚል ጥሪ ለትግራይ ወጣቶች እያቀረቡ ነው 
  • ጦርነትን አንፈልግም ያሉ እየሸሹ ነው
  • የአገር መከላከያ ከአላማጣ ወደ ቆቦ አመራ።
  • ትህነግ፣ ሻዕቢያና ፋኖ በግብጽ አስተባባሪነት የተቀናጀ ጦርነት ለመክፈት በቋፍ ላይ ናቸው
  • በምዕራብ ጠለምትና በዋልድባ አቅጣጫ መከላከያ ከባድ የተባለ የመከላከያ እርምጃ ወስዷል። ነጥቦቹ እነዚህ ናቸው እንደሚከተለው አጠናክረነዋል።

አዲስ ሪፖርተር – ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ  በሚል ስያሜ የሚጠራው ቡድን ረቡእ ሰባት ሰዓት አካባቢ በምዕራብ ጠገዴ አቅጣጫ የዲማን ከተማ ለመያዝ ስድስት ኮሮችን አስገብቶ ነበር። ሶስቱን ኮሮች ከፊት ለፊት አድርጎ፣ አራቱን በግራና ቀኝ በማሰለፍ ጥቃት ጀመረ። ነገር ግን ብዙ ሳይዋጋ አፈገፈገ። 

በውጊያው ከተሳተፉ የአካባቢው አስተዳደር አመራሮች የተገኘው መረጃ እንደሚያለከተው፣ የአገር መከላከያ ባለበት ሆኖ የሰጠው የመከላከል አጻፋ ከባድ ነበር። በአየርና በከባድ መሳሪያ የተደገፈ አጭርና ጠንካራ ምላሽ ከተሰጠ በሁዋላ ከፊት ለፊት የገባው ሶስት ኮር ምን እንደገጠመው ወደፊት ታሪክ እንደሚዘግበው እነዚሁ ወገኖች አስታወቀዋል። ጥቃቱን የሰነዘረው ትህነግ በጉዳዩ ዙሪያ በድልም ሆነ በሽንፈት እስካሁን ያለው ነገር የለም።

መከላከያ በርቀት ሆኖ የሰጠውን ምላሽ መቋቋም ያቃተው ቀሪው ኃይል አፈግፍጎ ተከዜ ጫፍ ማይበሌ በየጉድጓድ ራሱን መደበቁን ዜናውን ያጋሩን አመልክተዋል። ከትህነግ በኩል ምንም ዓይነት ማብራሪያ ያልቀረበበት ይህ ውጊያ የተካሄደው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ቀጣዩ ዕቅድ ምን እንደሆነ ለመናገር እንደሚችገሩ የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።

More stories

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

April 7, 2021

የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤ አንገታቸው የተቀላ መኮንኖች ፊልም ሊታዩ ነው

May 13, 2021

ከሱዳን የተነሳ የትህነግ ሃይል (ሳምሪ) ሳይዋጋ ሙሉ በሙሉ ተማረከ

August 11, 2021

የመንግስት ማጅራት መቺዎች ፈተና ሆነዋል – ሃላፊዋ አምነዋል

May 9, 2022

ዜናውን ያጋሩን የአስተዳደሩ አካል “ የትህነግ አዋጊዎች ስትራቴጂ ይቀይራሉ፣ ዕቅዱ ስላልተሳካ ሰላም ይሻላል ብለው ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ መጡበት ይመልሳሉ፣ ቦታ ቀይረው ሌላ ዕድል ይሞክራሉ?” ለሚለው ለጊዜው ምንም ምላሽ መስጠት እንደማይቻል አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ኃይላቸውን ዳግም እያሰባሰቡ ስለመሆኑ መረጃና ምልክቶች እንዳሉ አልሸሸጉም።

“የአገር መከላከያን ሳይጨምር በእኛ በኩል ጠንካራ ዝግጅት አለ” ያሉት አስተዳደሩ፣ እስካሁን ባለው እውነታ ክስድስት ኮር በላይ አሰልፎ የመጣው ኃይል ክፉኛ ጉዳት ደርሶበታል። ከዚያ በላይ ደግሞ ሰራዊታቸው የመዋጋት ፍላጎት የለውም። 

ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የትግራይ ሰላም ኃይሎች የስፍራው አመራር፣ መንግስት ከባድ እርምጃ መውሰዱን መታዘባቸውን፣ በርካታ ታጣቂዎችም እነሱን እየተቀላቀሉ መሆኑን በትግርኛ ካደረጉት ቃለ ምልልስ ለማረጋገጥ ተችሏል። 

የአስተዳደሩ አካላት እንደሚሉት ሕዝቡ “አጎሳቆላችሁን፣ አታለላችሁን፣ ጦርነት አንፈልግም፣ በቃን” በማለት በትህነግ ኃይሎች ላይ ተቃውሞ ሲያሰማ መቆየቱን አመልክተዋል። ይህን አስመልክቶ የትህነግ ኃይሎች በግልጽ መረጃ ሲሰጡ ወይም የጀመሩትን ጦርነት በህዝብ ዘንዳ ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት  ድረስ ያስታወቁት ነገር የለም። ይሁን እንጂ ባለፈው ሳምንት “ደህና ሁኚ ሽሬ” በማለት እናቶች ሲጨፍሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቶ ነበር። 

በዋልድባ አቅጣጫ ተጀምሮ ከከሸፈው ጥቃት በሁዋላ በምዕራብ ጠለምት የተካሄደው ጦርነት የተሳካ ውጤት ባያስመዘግብም፣  ሶስቱን ኃይሎች አስተባብራ የምትመራው ግብጽ ዓላማዋ የኢትዮጵያን መንግስት በማፍረስ አገሪቱን ለጎበዝ አለቆች መናኸሪያ ማድረግ እንደሆነ እጃቸውን የሰጡ መናገራቸው ይታወሳል። 

“ለባዕዳን ተልዕኮ አስፈጻሚ አንሆንም፣ ትግሉ ተጠልፎ የግብጽና የሻዕቢያ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ሆኗል” በማለት ወደ ሰላም መንገድ የተመለሱት የፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች እንዳሉት፣ ዘመነ ካሴ የሚመራው የፋኖ ኃይል ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት ስምምነት አድርጓል። ይህ ስምምነት ደግሞ ሰፊውን የፋኖ ኃይል አስቆጥቷል።  አሁን ላይ እንደሚሰማው ከሆነ ወልቃይትን አስመልክቶ አዲስ መረጃ ለመስጠት የፋኖና የትህነግ ኃይሎች እየተዘጋጁ ነው። 

አቶ ጣሂር መሐመድ ወልቃይትን ለማስረጀብ የተስማሙትን የፋኖ ጥቂት አመራሮች አስመልክቶ “ባንዳ” በማለት ዝርዝር ማብራሪያ መስተቱን ተከትሎ “ከድል በሁዋላ ያገናኘን” በማለት በአርበኛ መሳይ መኮንን አመካይነት ማስፈራሪያ ደርሶታል። 

ኤርትራዊ ሚስት ያላቸው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ “የአገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ መሬት ላይ ተረማምዶ ሻዕቢያንና ትህነግን ለማጥቃት ሲሞክር ከጀርባው እንሰፍርበታለን” ማለታቸው አይዘነጋም። በዚህና በተለያዩ መረጃዎች መነሻ የፋኖ ኃይል ቁጣ ማሰማቱና ወደ ሰላም ማምራቱ በሻዕቢያና ትህነግ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ እየተዘገበ ሰንብቷል። 

ይህንኑ ስሜት ተከትሎ ሰፊ ቁጥር ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ወደ ሰላም እየገቡ በመሆኑ ሻዕቢያ ጦርነቱ ቶሎ እንዲቀጣጠል አመራር መስጠቷን ጠቅሰን ከሳምንት በፊት መዘገባችን አይዘነጋም። 

በስተመጨረሻ አዲስ ሪፖርተር ባሰባሰበችው መረጃ በራያ አቅጣጫ፣ በአፋር ጨርጨር፣ በወልቃይት ሙሉ በሙሉ ጦርነት ለመክፈት ዝግጅቱ እየተጧጧፈ ነው። በትግራይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት አቁሟል። ባንኮች በይፋ ባያቆሙም አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ለሕዝብ ጥቅም ወደ ትግራይ የተላከ ነዳጅ ወደ ግዳጅ ጣቢያዎች ተሰራጭቷል። ገሚሱም ወደ ኤርትራ ተልኳል። 

የአፋር ቀይ ባህር አመራሮች ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት በቂ ዝግጅት አድርገው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የጦርነቱን አድማስ በማስፋት በሁሉም በኩል በይፋ ጦርነት ከመለኮሱ በፊት የአገር መከላከያ ሰራዊት ከአላማጣ ለቆ በመውጣት ወደ ቆቦ ተመልሶ ስትራቴጂክ የተባሉ አካባቢዎችን መያዙ ታውቋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ
“በወጣቶች ሕይወት መነገድ ይበቃል!” – ስምረት ፓርቲ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2