Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተወሰኑ የሠራዊቱ አባሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ
SOCIETY

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተወሰኑ የሠራዊቱ አባሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ

Ethioreview newsEthioreview news—March 24, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ትግራይ ክልል፤ በአክሱም ከተማ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአጠቃላይ በክልሉ የተሟላ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነትን ያመለክታልበአክሱም ከተማ፣ ትግራይ ክልል የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ይፋ አደረገ።

ከበርካታ ሳምንታት ጥረት በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን ወደ አክሱም ከተማ መላክ መቻሉን የገለጸው ኢሰመኮ፣ ባለሞያዎቹ ከየካቲት 20 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በከተማዋ በመቆየት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ 45 የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዓይን ምስክሮችን እና የሃይማኖት መሪዎችን አነጋግሯል። እንዲሁም 20 ሰዎች የተሳተፉበት የቡድን ውይይት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አድርጓል። በተጨማሪም ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል፣ ከአክሱም ሪፈራል ሆስፒታል፣ ከሚመለከታቸው የቀበሌ መስተዳደር አካላት እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች የተለያዩ የምስል፣ የድምጽ እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቧል።

ኮሚሽኑ በዚህ ምርመራው ያሰባሰባቸው መረጃዎችና በተለይም ከኅዳር 19 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበሩት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸመና፤ የአክሱም ከተማ እና አከባቢው ነዋሪዎች፣ ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ጦርነት ሸሽተው በከተማዋ የተጠለሉ ተፈናቃዮችና እንዲሁም የኅዳር ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከአንድ መቶ በላይ ሲቪል ሰዎች በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል።

በዚህ የቀዳሚ (መጀመሪያ ደረጃ) ሪፖርት የተጠቀሱ አኃዞች አጠቃላይ የተጎጂዎችን ቁጥር የሚያመላክቱ ሳይሆን፣ ኮሚሽኑ እስከዚህ ምርመራና ሪፖርት ወቅት ድረስ ብቻ ለማረጋገጥ የቻለውን የሲቪል ሰዎች ጉዳት የሚጠቁም ነው። ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ፣ የተጎጂ ቤተሰቦች እና የአይን እማኞች በርካታ ሲቪል ሰዎች ልጆቻቸው፣ ሚስቶቻቸው እና እናቶቻቸው ፊት ጭምር በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ አስረድተዋል።

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

ይህ በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩት የኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተራ ወንጀል ሳይሆን በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና መርኆች የተቀመጡ ድንጋጌዎችን የሚጥስ፣ በግጭቱ ተሳታፊ ያልነበሩ ሲቪል ሰዎች ላይ ጭምር ሆነ ተብሎ ያነጣጠረ እና በሚሊተሪ አስፈላጊነት ሊገመገሙ የማይችሉ እና ሆነ ተብሎ የተደረጉ በሲቪል ሰዎች ንብረቶች በሃይማኖት ተቋማትና በሆስፒታሎች ጭምር ዝርፊያና ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቱ ምናልባት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ስለሚችል፤ በአጠቃላይ በክልሉ የተሟላ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ምርመራ ስራ ማካሄድ ያስፈልጋል።

የሰዓት እላፊ ገደብን ለማስከበርና በደኅንነት አጠባበቅ ምክንያት በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች የሚወሰደው እርምጃ ለሰው ሕይወት መጥፋትና የአካል ጉድለት መድረስ ምክንያት መሆኑ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንና፤ የሰዓት እላፊ ገደብን ተላልፎ የተገኘ ሰውንም ቢሆን በተመጣጣኝ ኃይል በቁጥጥር ስር ማዋል ስለሚቻል፤ ለነገሩ ሁኔታ ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀም የተወሰዱት እርምጃዎችና በዚህ መልክ የተገደሉ ሰዎች ሁኔታ በተሟላው ሪፖርት የጸጥታ ኃይሉንም ምላሽ በማካተት የሚጣራ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በሲቪል ነዋሪዎች ደኅንነት አጠባበቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል አጠቃቀም በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ ሪፖርቱ ያመለክታል።

‹‹በትግራይ ክልል የተከሰተውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በአለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድርጅትና በኮሚሽኑ የጣምራ ምርመራ ቡድን (joint investigation team) አማካኝነት እንዲጣራ የፌዴራሉ መንግስት ስምምነቱን ማሳወቁ ትክክለኛ እርምጃ ነው›› በማለት የገለጹት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አክለውም ‹‹አብዛኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባሎች በሕይወት መስዋእትነት ጭምር አገራቸውንና ሕዝብን የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ በተወሰኑ የሠራዊቱ አባሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ለጣምራ ምርመራ ቡድኑ (joint investigation team) የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ስራ ተገቢውን እገዛ ማድረግ ይገባል›› ብለዋል።የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይመልከቱ:

the-ethiopian-human-rights-commission-esmeko-has-announced-the-first-level-first-report-on-the-attack-on-civilians.-1Download
SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Some of the excerpts from Prime Minister Dr. Abiy Ahmed speech
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስተዳደራዊ በደሎች መፈትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ችግሮች እየገጠሙት መሆኑን ገለጸ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2