በቻይና በተካሄደ አገር አቋራጭ የተራራ (አልትራማራቶን) ውድድር ላይ በተከሰተ ከባድ የአየር ሁኔታ የ21 ሯጮች ሕይወት አልፏል። በ100 ኪ.ሜ (60 ማይልስ) የአልትራማራ ውድድሩ በጋንሱ አውራጃ የቱሪስት ስፍራ በሆነው በቢጫ ወንዝ የድንጋይ ደን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መካሄዱ ተገልጿል።
በወቅቱም በተከሰተው ከፍተኛ ንፋስ እና በረዶ የቀላቀለበት ዝናብ አትሌቶቹ በመመታታቸው በውድድሩ ከተሳፉ 172 ሯጮች መካከል አንዳንዶቹ ሲጠፉ ÷21 ሯጮች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል። ውድድሩ ተቋርጦም የነፍስ አድን ሥራ መጀመሩ ተመላክቷል።
በዚህም ከተሳታፊ አትሌቶች መካከል 151 የሚሆኑት ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ መቁሰላቸውም ነው ባለሥልጣናቱ የገለጹት ፡፡ ውድድሩ ሲጀመርም የተወሰኑ ተወዳዳሪዎችን ቁምጣ እና ቲሸርት ብቻ ለብሰው እንደነበር ነው የተገለጸው ፡፡
በሕይወት የተረፉት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ÷የአየር ሁኔታው በእይታቸው ላይ ተጽዕኞ በማሳረፉ መንገዳቸውን መሳታቸውን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ትንበያው የተወሰነ ንፋስ እና ዝናብ እንደሚጠበቅ ቢተነብይም እነሱ የገጠማቸውን ያህል የከፋ የአየር ጸባይ ሊኖር እንደሚችል አለመግለጹን ተናግረዋል።
ሩጫው ከተጀመረ ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ በተራራማው ክፍል በበረዶ ፣ በከባድ ዝናብ በመምታቱ የአካባቢው ሙቀት መጠኑን እንዲያሽቆለቁል ምክንያት መሆኑን በአቅራቢያው የሚገኘው የቤይን ከተማ ባለሥልጣናት ገልጸዋል ፡፡
የነፍስ አድን ስራው ሌሊቱን ሙሉ እስከ እሁድ ጠዋት የቀጠለ ሲሆን÷ ተጨማሪ የሙቀት መጠን መቀነሱ ፍለጋውን ይበልጥ ከባድ እንዳደረገው የቻይናው የዜና አውታር ዘግቧል ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






