Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ዐቃቤ ሕግ በአክሱም ደረሰ የተባለውን ጥፋት መርመሮ ይፋ አደረገ፤ አነጋጋሪ አሃዞችና የጥፋቱ መንስኤዎች ይፋ ሆኑ
News

ዐቃቤ ሕግ በአክሱም ደረሰ የተባለውን ጥፋት መርመሮ ይፋ አደረገ፤ አነጋጋሪ አሃዞችና የጥፋቱ መንስኤዎች ይፋ ሆኑ

Ethioreview newsEthioreview news—May 10, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በትግራይ ክልል በአክሱም ከተማ በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ ወንጀሎችን እና የተከናወኑ የወንጀል ምርመራ ተግበራትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ላለፉት ሁለት ወራት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከተውጣጡ አባላት በተቋቋመ የምርመራ ቡድን አማካኝነት ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በሀገሪቱ ላይ ያወጀውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በህዳር ወር 2013 ዓ.ም የተፈጸሙትን ወንጀሎች የመመርመር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም በከተማዋ ውስጥ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ወታደሮች ተፈጽመዋል በሚል ለቀረበ ጥቆማ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የምርመራ ቡድኑ ወንጀል ተፈጽሟላ በተባለበት ስፍራ በአካል በመገኘት የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ስለመኖር ወይም አለመኖራቸው፤ እንዲሁም ተፈጽመውም እንደሆነ የወንጀል ፈጻሚዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል የወንጀል ምርመራ እያካሄደ  ይገኛል፡፡

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በከተማው ሞቱ ስለተባሉ ሰዎች በተደረገ የማጣራት ስራም በጦርነቱ መካከል ህገ-ወጡን ቡድን ኢላማ ያደረገ መድፍ ተተኩሶ ኢላማውን በመሳቱ እና በከተማዋ የሰዎች መኖሪያ ቤት እና ዩኒቨርስቲ አካባቢ በመውደቁ በመኖሪያ ስፍራው 4 እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው አካባቢ አንድ በድምሩ አምስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን በተጨማሪም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስፈጸም ሂደት ውስጥ ከሰዓት እላፊ ጋር በተገናኘ ሕግ በማስከበር ስራ ላይ ካሉ የፖሊስ አባላት ጋር በተፈጠረ እሰጥአገባ ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰው በአጠቃላይ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሌላ ግዳጅ ከተማውን ለቆ እስከወጣበት እለት ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በአክሱም ከተማ ቆይቷል፡፡

ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም የመከላከያ ሰራዊቱ ለተጨማሪ ግዳጅ ከተማዋን ለቆ ሲወጣ የህወሀት ካድሬዎች ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ የኤርትራ ሰራዊት በሁለት ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ተራራማ ቦታ ላይ መጥቶ ሰፍሯል።

የኤርትራ ሰራዊት ለመዋጋት ሳይሆን እጅ ለመስጠት ይፈልጋል በሚል አስወርተው አዴት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ያሉ የሕወሃት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት በከተማዋ ውስጥ ካሉት 1500 የሚጠጉ የተኩስ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ጋር በመሆን ወደ አክሱም ከተማ ለመዋጋት ገብተዋል፡፡

በበረሀ የነበረው የቀድሞ የአክሱም ከተማ ከንቲባም ደብዳቤ ጽፎ ከሰሜን እዝ ላይ የተሰረቁትን ጨምሮ በአምስት ቦታዎች ላይ የተከማቹትን የጦር መሳሪያዎች በአክሱም ከተማ ከህዳር 01-09/2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ህወሃት የአንድ ቀን የመሳሪያ ተኩስ ስልጠና በመስጠት ለህገ-ወጥ ተግባር ላሰናዳቸው 1,500 ወጣቶች እንዲከፋፈል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ይህ ስለመሆኑ የምርመራ ቡድኑ የጦር መሳሪያ ከደረሳቸው እና ካልደረሳቸው ወጣቶች እንዲሁም ከልዩ ኃይል አባላት የምስክርነት ቃል ማረጋገጥ ችሏል፡፡

መሳሪያዎቹ በአምስት ቦታ የተከማቹ ሲሆኑ በአንዱ ማከማቻ ብቻ 400 መሳሪያ ወጪ ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ አካላት ተባብረው ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 8 ሰዓት በቆየ ውጊያ ጥቃት ሲያደርሱ ውለው አጋዥ ሀይል በቦታው ሲደርስ ወደ ከተማዋ ሸሽተው መግባታቸውም በምርመራው ተረጋግጧል፡፡

በዚህም ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት በተደረገ ጥረት የ95 ሰዎችን የምስክርነት ቃል ለመቀበል የተቻለ ሲሆን በምርመራ ሂደቱም በጦርነቱ የ93 ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና ሟቾቹም ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በአብዛኛው በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ስለመሆናቸውም በምርመራው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን በተመለከለተ በአጠቃላይ 116 ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተከናወነ ምርመራም በወንጀሉ የተሳተፉ የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተለይተው የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳይ በክልሉ ዐቃቤ ሕግ እንዲመረመር እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወታደራዊ ግዳጅ ላይ እያሉ የፈጸሙት ወንጀል በመሆኑ ጉዳዩ በወታደራዊ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡

የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎችን በቀረበው አቤቱታ ልክ ለመለየት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ህወሃት አስቀድሞ በከባድ ወንጀል የተከሰሱ እና የተፈረደባቸው ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን ከእስር ለቆ እና ለክልሉ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ  የኤርትራ ወታደሮችን ዩኒፎርም በማዘጋጀት እንዲሁም የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በሰነዘረበት ጊዜ ከገደላቸው እና ከያዛቸው የሰራዊቱ አባላት ላይ ወታደራዊ የደንብ ልብስ አውልቆ እና አስወልቆ ለራሱ ወታደሮች በማልበስ ይጠቀም የነበረ በመሆኑ የወንጀል ፈጻሚዎችን ማንነት የመለየት ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

በግድያውም ሆነ በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ዙሪያ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ በምርመራ ሊለዩ የሚገባቸው ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም የድርጊቱን አፈጻጸም እና የፈጻሚዎችን ማንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የሰው፣ የሰነድ እና የገላጭ ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል፡፡

አሁንም ምርመራው የቀጠለ ሲሆን ምስክሮች በመልክ የጠቆሟቸውን ተጠርጣሪዎች የመለየት ስራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካባቢም የእምነት አባቶች እና የቀብር አስፈጻሚዎችን  የምስክርነት ቃል የመቀበል እንዲሁም ከሆስፒታሎች የህክምና ማስረጃ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግም ከፌዴራል እና ክልል ፍትህ እና ጸጥታ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ጊዜ ይውስድ ይሆን እንጂ በሁሉም ወንጀሎች የተሳተፉ ሰዎች ሁሉ በፍትህ አደባባይ ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በትጋት የሚሰራ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይገልጻል፡፡


    NEWS
    FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
    ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የ31 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
    በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀ የሽብር ቡድን ተያዘ፤ ምስላቸው ይፋ ሆኗል፤ ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን አቋቁሟል
    Related posts
    • Related posts
    • More from author
    News

    ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

    April 26, 2026
    News

    “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

    April 26, 2026
    News

    ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

    April 13, 2026
    Load more
    Read also
    News

    ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

    April 26, 2026
    WORLD

    ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

    April 26, 2026
    News

    “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

    April 26, 2026
    WORLD

    አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

    April 26, 2026
    WORLD

    የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

    April 26, 2026
    WORLD

    የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

    April 26, 2026
    Load more
    Recent Posts
    • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
    • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
    • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
    • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
    • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
    • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
    • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
    • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
    • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
    • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
    • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
    • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
    • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
    • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
    • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
    Social networks
    FacebookLikes
    X TwitterFollowers
    PinterestFollowers
    InstagramFollowers
    YoutubeSubscribers
    VimeoSubscribers
      VOE
      The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

      MENU

      NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
      © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
      • CONTACT
      • law
      • INTERVIEW
      • ያበደው
      • ECONOMY
      • Home demo times
      • VOE VIDEO
      • ENGLISH PAGE
      • Home Demo default 2