Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “ትግራይ! የቁርጥ ቀን የነፍስ አድን ልጆችዋን ለመከራ ነጋዴዎች አትገብርም”!!
News

“ትግራይ! የቁርጥ ቀን የነፍስ አድን ልጆችዋን ለመከራ ነጋዴዎች አትገብርም”!!

Ethioreview newsEthioreview news—June 25, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰጠው ሙሉ መግለጫ

በትግራይ የንፁሐን ዜጎችን ሰቆቃን የማስቆም፤ ተጨማሪ የህይወት መጥፋት እንዳይከሰት አጥብቆ የመስራት ጉዳይ፣ አሁንም በርካታ ፈተናዎች ያሉበትንና የልዩ ልዮ ተዋናዮች ተግባራትም ቢያንስ፣ በሰብአዊነትና ነፍስን በማዳን ጉዳይ ላይ አግባቢ ሊሆን ይገባ ነበር። ሆኖም በተጨባጭ ከእለት ወደ እለት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ስንመለከት ከሰብአዊነትና ከተለመደ የማህበራዊ ሁኔታ ልምምዶች ያፈነገጡ መሆናቸውን ስንታዘብ ግን በእጅጉ የተለየና አሳዛኝ መሆኑን እንረዳለን።

በትግራይ በሚካሔዱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በተመለከተ፣ በማህበራዊ ሚዲያና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች በአንዳንድ የታጣቂ ቡድኑ የጦር አመራሮች ከሰሞኑ ታቅደው በተከታታይ የተላለፋ የዘመቻ ውጤቶች ቃለ ምልልሶች፤ የራሳቸው የተለየ አላማን ለማስፈፀም የተዘረጉ ንፁሃንን ሰለባ የሚያደርግ አደገኛ የሰለባነት ትርክቶች ናቸው።

እነዚህ የበቀልና ዛቻ ጥሪዎች ፣ የትግራይን የቁርጥ ቀን ወጣት የነፍስ አድን ሙያተኞች ህይወት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መንጠቅ መጀመራቸውን ተከታታይ መርዶዎች በቁጭት ፣ በእልህና በጥልቅ ሀዘን ስናረዳ ፣ የምላሹ መቋጫና መላም እጅግ የፈጠነ ፣ የተሰላና አስተማሪ የሚሆን መሆኑን ለአጥፊዎች ከወዲሁ በጥብቅ በማስገንዘብም ጭምር ነው።

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ በግምት ከቀኑ ሰባት ሰዓት በኃላ ባለው ግዜ ፣ ከቢሮ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ የአየር ማረፊያ ለመጓዝ በተዘጋጀበት፣ ለግዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አፋኞች በሐይል ተወስዶ ደብዛው መጥፋቱ ሲነገርለት የቆየው ወጣቱ እንጅነር እምብዛ ታደሰ ፤ በጨካኝ የከተማ ሽብር ተልእኮዎች አስፈፃሚ ወንጀለኞች ተገድሎ ፤ በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሐይሎች በተከናወነ አሰሳ ፣ በትላንትናው እለት ከረፋዱ አምስት ሰዓት በዓይደር ልዩ ስሙ ማረምያ ቤት በተባለ ስፍራ ተገድሎ ብቻ ሳይሆን ለጅቦች ከተጣለበት ስፍራ ቁርጥራጭ የሰውነት አካላቱን በመለየት በተጨማሪ ምርመራም፤ በአረመኒያዊ አፈፃፀም በጭካኔ መገደሉን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ በእጅጉ ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅና የሚኮነን አረመኔያዊ የግድያ ወንጀል እየተፈፀመ ያለው፤ በተለይ ትግራይ በአሁኑ ግዜ ላጋጠማት ችግር የመፍትሔ አካል በመሆን ከግዚያዊ አስተዳደሩ ወቅታዊ የተልእኮ አቅጣጫ በመውሰድ ወገኖቻችን ለተጨማሪ ሞትና ስቃይ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በዘመቻ መልክ በቅንጅት በመተግበር ፣ የምግብ እና የህክምና እርዳታዎችን ተደራሽ ማድረግ፣ የያዝነው ክረምት የዝናብ ፀጋ ገበሬያችን እንዳያልፈው እርሻ ስራን ለማስጀመር ርብርብ በሚደረግበት ወቅት፣ መሰረተ-ልማቶች ወደ ስራ ለማስገባት ሌት ተቀን በሚለፉ፣ ፋብሪካዎችን ወደስራ በመመለስ የስራ ዕድል ፈጠራው ዳግም ለማንሰራራት በሚባክኑ፣ ጨለማን ገፈው ብርሃን ለህዝባቸው ለማቅረብ በሚዳክሩ፣ የጤና ተደራሽነት እንዲሻሻል በሚመክሩ፣ የትግራይ ህዝብ ሃብት የሆኑትን የትእምት ፋብሪካዎች የምር የህዝብ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ሚገኙ ወጣቶች ወዘተ፣ በግጭቶች መስፋትና መካረር በዘላቂነት በትግራይ ውስጥ ሊፈጥር የሚችለው ተጨማሪ ቀውስ እንዳይባባስ ትንቅንቅ በያዝንበት በዚህ ወቅት ነው። ይህም የትግራይን እምባ የማበስ መስዋእት የሚያስከፍል የሰማእት ወጣቶች ተልእኮ ለአረመኔዎች ደንታ የማይሰጥበት የጭካኔ ጠርዝ መኖሩን እያስቃኘን ይገኛል።

በመሆኑም እስካሁን ይህን በጎና ቀና ተግባር በመከወን ህዝባቸውን እየረዱ የነበሩ እስካሁን ድረስ በተጠናቀረ መረጃ በአሁኑና መሰል እኩይ ወንጀሎች በትግራይ ከሐምሳ በላይ ወጣት የህይወት አድን እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሰጪ ንፁሐን፤ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ወይም ወታደራዊ ተሳትፎ ፍፁም ገለልተኛ የሆኑ አገልጋዮችን ህይወት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች በከንቱ የመቀጠፋቸው አሳዛኝ ዜና መላው ማህበረሰባችን ነቅቶ ሊከታተለው የሚገባ ጉዳይ ሆነዋል። ገዳዮች ይህንን መሰል ወንጀላቸውን ከመፈፀማቸው በፊትና በኃላ ያለ ህፍረትና መሸማቀቅ በሞትና መከራ ወኪል ልሳኖቻቸው በግልፅ በድፍረት የሚናገሩ ከመሆናቸውም በላይ፤ በሐሳብና ተግባራቸውም በትግራይ ወጣቶች ሞትና መከራ የመነገድና የመደመጥም ተልእኮ እንዳላቸውም አጥፊው ቡድን እና ደጋፊዎቹ ሃላፊነት ወስደው በአደባባይ ሽንጣቸውን ገትረው መስክረዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ በየትኛውም የተግባርም ሆነ በህግ የተቀመጠ የተልእኮ ወሰን መለኪያዎች በተለይ ባለፋት ጥቂት ሳምንታት የተሻሻሉ የአደጋ ጊዜ አመራር መርህዎችን በተከተሉና ሀላፊነት እና ወገናዊነት በሚሰማቸው የህዝብ ልጆች ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና የተቋረጡ አስፈላጊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማስቀጠል ፣ነፍስ አድን ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግና ለህዝቡ ጊዜያዊ እፎይታ ለመስጠት በሚያስችሉ የዘመቻ ስራዎች ተሳትፎ፣ አንፃራዊ የህብረተሰብ ተሳትፎ መሻሻል ባገኘበት በአሁኑ ጊዜ መፈፀሙ ፣ የጥፋት ሀይሎቹ እኩይ አላማቸውን ከህብረተሰቡ የህልውና ጉዳይ በላይ ያስቀደሙ መሆናቸውን በግልፅ የሚያሳይ፤ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ እነዚህን የመከራ ነጋዴዎች በቃ ሊላቸው የሚገባበት የመጨረሻው ደቂቃ ላይ እንደምንገኝ በጥብቅ የሚያመላክት ሀቅ ነው።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህ በተለይ በትግራይ ወጣቶች ላይ የተቃጣ እና ወጣቶች በክልላቸውና በአገራቸው ጉዳይ ላይ በአዎንታዊ አግባብ የሚያደርጉትን የነቃ ተሳትፎና አበረታች ጅማሬ ለማሸማቀቅ የተዘረጉ የጥፋት በትሮችን ከሚመለከታቸው የፀጥታና የደህንነት አካላት ጋር በተቀናጀ እርምጃ ለማክሸፍ የሚሰራም መሆኑን ሁሉም ሊገነዘቡት የሚገባ ጉዳይ ነው ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተጣለበትን ተልእኮ በራሱ ጀምሮ በራሱ ለመጨረስ የማይኮፈስና በትግራይ ተጨማሪ ሞትና ሰቆቃ እንዳይበዛ የማድረግ የሐላፊነት እድልን በስስታምና አግላይ አመለካከት ማስፈፀም ተገቢ አይደለም በሚል ቅን እሳቤ የአሳታፊነት እድሎችን ለማስፋት የተጠኑ እርምጃዎችን ቢያደርግም፣ አንዳንድ ክፋዎች ይህንን አሳታፊነት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ከውስጣችን ሆነው ቅን አገልግሎት የሚሰጡ እንጅነር እምብዛ የመሳሰሉ ለህዝብ የተሰጡ ወጣቶችን ህይወት እስከመቅጠፍ የደረሰ ነውረኛ ሴራ ውስጥ በተግባርና በሐሳብ ጭምር ተካፋይ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። በተገቢና ጠንካራ ምርመራ ሒደት ውስጥ በማሳለፍም አስፈላጊውን አፋጣኝ ፣ የማያዳግምና አስተማሪ የሆነ የማስተካከያ እርምጃዎችንም እንደሚወስድ ከወዲሁ በፅኑ ያስታውቃል።

በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በእንጅነርእምብዛ እና በአጠቃላይ ባለፋት ተከታታይ ወራት በንፁሐን አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶች በጥብቅ እየኮነነና እያወገዘ ፤

ለሟች ንጅነር አርቲስት እምብዛ ታደሰ እና ሌሎች በለጋ እድሜያቸው የተቀጠፉ የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ቤተሰቦች ፣ የስራ ባልደረቦችና አፍቃሪዎቹ በሙሉ ፈጣሪ መፅናናት እንዲሰጥልን እየተመኝን ፣ በወንድማችን እንጅነር እምብዛ ታደሰ አሰቃቂ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ታፈኑ” የተባሉት ኢንጂነር ተገደሉ፤ አስከሬናቸው በአሰሳ ተገኘ
የቅዳሜ ቅምሻ- ኮሮና አምስት ሚሊዮን አዳዲስ ሚሊየነሮች ፈጠረ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2