Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “የአፍሪካ ኅብረት ያቋቋመው የተናጠል መርማሪ ኮሚሽን መንግሥት እንዲደረግ ይሁንታ ከሰጠው አግባብ ውጪ ነው”
News

“የአፍሪካ ኅብረት ያቋቋመው የተናጠል መርማሪ ኮሚሽን መንግሥት እንዲደረግ ይሁንታ ከሰጠው አግባብ ውጪ ነው”

Ethioreview newsEthioreview news—June 20, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በአፍሪካ ኅብረት ሥር የሚገኘው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለሚደረገው ገለልተኛ ምርመራ ባቋቋመው ኮሚሽን ውስጥ ኢትዮጵያን አለማካተቱ መንግሥት ቅሬታ እንደፈጠረበትና ኮሚሽኑም የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ጥሪ ቀረበ፡፡

ይህ የተገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር ተያይዞ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በጋራ ምርመራ ለማድረግ ሲያግባባ የቆየ ሲሆን፣ ለቀረበው ጥያቄ ኮሚሽኑ ያቋቋመው የተናጠል መርማሪ ኮሚሽን የሕግ መሠረት የሌለውና መንግሥት እንዲደረግ ይሁንታ ከሰጠው አግባብ ውጪ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው እንዳስነበበው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በየካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከፍተኛ የአገር መሪዎችና የአባል አገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ ከአኅጉሩ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጥምረት በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ስለተባሉት የመብት ጥሰቶች ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛነቷን እንደገለጸች አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም  ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የኅብረቱ፣ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መናብርት ጋር  ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጨምሮ ገልጿል፡፡

በተከታታይነት ከተደረገ ውይይት በኋላ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ በጋራ ምርመራ ለማድረግ ያቀረበችውን ሐሳብ መቀበሉን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መጻፉን መግለጫው አስታውሶ፣ ሆኖም ግን የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሚደረገው ምርመራ በተናጠል ያቋቋመው ኮሚሽን ኢትዮጵያን በማግለል የተዋቀረ መሆኑ መንግሥትን ቅሬታ ውስጥ ከመክተቱ ባሻገር፣ ሕጋዊ አካሄድን የተላለፈ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሳምንት በፊት በበይነ መረብ ባከናወነው 32ኛው ልዩ ጉባዔ በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ሌሎች ጉዳዮችን ሁኔታ የሚያመላክት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ከውሳኔ ላይ መድረሱን ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል፡፡

በኅብረቱ የተቋቋመው ኮሚሽን መቀመጫውን በጋምቢያ ርዕስ ከተማ ባንጁል አድርጎ ሥራውን እንደሚጀምር፣ በመቀጠል በኢትዮጵያና አጎራባች አገሮች የሚመለከታቸውን አካላት በምርመራው እየሸፈነ ለሦስት ወራት እንደሚቆይና የምርመራው ጊዜም እንደሁኔታው ታይቶ የመራዘሙ ሁኔታ ታሳቢ መደረጉን የወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሌላ በኩል በመግለጫው የጋራ ተልዕኮን ቸል በማለት በኮሚሽኑ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጠቃሚ ካለመሆናቸው ባሻገር በአኅጉሪቱ በሚገኙ አገሮች ላይ ከሰብዓዊና የዜጎች መብት ጥበቃ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ገለልተኛ ምርመራዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳንሱ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡ በአንድ አካል ፍላጎት የሚደረጉ ምርመራዎችም የተነሱበትን ዓላማ ከማሳካት ይልቅ ለውዥንብር የሚዳርጉ እንደሆኑም ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስረድቷል፡፡

ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በጋራ ለሚደረጉ ምርመራዎች ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ ለመግለጽ እንደምትሻ ያስታወቀው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ በመሆኑም የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ካለኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅናና ፈቃድ ያቋቋመውን የምርመራ እንቅስቃሴ በማቆም አስፈላጊውን የሕግ አካሄድ በተከተለ መልኩ ያቀደውን ምርመራ ለማድረግ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኤልያስ ተገኝ reporter Amharic

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ሥራዬን ከብር ጋር አላያይዘውም” የጥርስ ሐኪም ራሄል አክሊሉ
Sudan rules out force to stop Ethiopia’s second filling of Renaissance Dam
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2