የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከ700 ሺህ በላይ ኩንታል የምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን አስታወቀ። መንግስት ይህን እያደረገ ” ረህብን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ያደርጋል መባሉ አሳዛኝ ነው”
ካለፈው ወር አንስቶ በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የቆዳ ስፋት በአጋር አካላት ቀሪው 14 በመቶ ደግሞ በመንግስት እንደሚሸፈን መገለፁ ይታወሳል። ይህ እውነት እያለ ነው መንግስት እርዳታን ለፖለቲካ እንደሚጠቀም የሚገለጸው።
በዚህም መሰረት ምዕራብ ዞን፣ ደቡብ ዞን አምስት ወረዳዎች፥ በመንግስት የሚሸፈኑ ሲሆኑ ደቡብ ሶስት ወረዳዎች፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና የመቐለ ከተማ ደግሞ በአጋር አካላት የሚሸፈኑ መሆናቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንዳሉት ኮሚሽኑ በግጭትም ሆነ በሌሎች የአደጋ ክስተቶች ተጎጂ ለሆኑ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ያደርጋል።
ኮሚሽኑ በአማራ፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጊዜያዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በትግራይ ለ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የሶስተኛ ዙር ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ በመንግስትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ጥምረት እየተሰጠ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ቀደም ሲል ድጋፉ 70 በመቶ በመንግስት ቀሪው 30 በመቶ በአጋር አካላት ይቀርብ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ 86 በመቶ በአጋር አካላት 14 በመቶ ደግሞ በመንግስት እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል።
እስካሁን ባለው ለትግራይ ክልል 772 ሺህ 954 ኩንታል እህልና 289 ሺህ 339 ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ መላኩንም ጠቁመዋል።
ኮሚሽኑ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ኀብረተሰቡ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ኮሚሽኑ በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችም መሰል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ 124 ሺህ 49 ኩንታል እህል እንዲሁም በአማራ ክልል አጣዬ የተፈናቃዮች 32 ሺህ 520 ኩንታል ምግብ ተልኳል ብለዋል።
በዚህ መረጃ መሰረት መንግስት አስራ አራት በመቶ የሚሆነውን የቆዳ ስፋት ብቻ ለይቶ እርዳታ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ ረሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ እንዳዋለው ተደርጎ የሚነገረውን ዜና ውድቅ እንደሚያደርገው ባለሙያዎች እርዳታ ከሚሰጡትና ሃሰት ሪፖርት ለሚያደርጉት ክፍሎች አስታውቀዋል።
86 መቶኛውን የትግራይን የቆዳ ስፋት እርዳታ የሚመሩት ወገኖች ስለምን እንዲህ ያለውን ቅጥፈት ይናገራሉ? ለሚለው ምላሹ ሌላ እንደሆነና ሕዝብን ዛሬ ላይ ተንቅቆ እንደሚረዳው ባለያዎቹ አመልክተዋል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






