በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት ከተደረገ በሁዋላ እነማን ባለ ስልጣን ሆነው እንደሚመደቡ የሚያሳይ ሰነድ መያዙ ተሰማ። ሰነዱ የተያዘው ፖሊስ በተመረጡ ድንገተኛ ቦታዎች ባካሄደው ፍተሻ እንደሆነ ታውቋል። መከላከያን ለማፍረስ የሚደረግ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት መደረጉን የሚያሳይ መረጃም ተገኝቷል።
በትናንትናው ዕለት ፖሊስ የአሸባሪው ትህነግ ደጋፊ ናቸው ያላቸውን ክፍሎችና ንግድ ቤቶች በድንገትና በጥቆማ ፈትሾ በርካታ ቁሳቁሶችን፣ መሳሪያዎችን፣ የወታደራዊ ማዕረግ፣ ሃሺሽ፣በርካታ የውጭ ምንዛሬ፣ የጦር መሳሪያ፣ የጦር መሳሪያ መነጽሮች፣ የስዳተላይት መገናኛና ከአሸባሪው ሃይል ጋር የተካሄዱ ውይይቶች እንዲሁም ሰነዶች እንዳገኝ ማስታወቁ አይዘነጋም።
የኢትዮ12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካሎች ጠቅሶ እንዳለው “ሰነድና የድምጽ ማስረጃ” ሲሉ የፊደራል ፖሊስ ከተቀሰው ውስጥ የምንግስት ግልበጣ ከተካሄደ በሁዋላ ትህነግ እንዲሾሙ ያግባባቸውና ሴራው ውስጥ ያሉ አካላት ስም ዝርዝርና ሹመታቸው ተገኝቷል።
“የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ነን” የሚሉና የሽግግር መንግስት ካልተቋቋመ በሚል አጥብቀው ሲከራከሩ የነበሩ ቁንጮዎች በሹመት ዝርዝር ውስጥ እንዳሉበት ተመልክቷል። ለጊዜው ለምረመራ ስራ ሲባል ስም ዝርዝር መጥቀስ አግባብ እንዳልሆነም ተባባሪያችን አስታውቋል።
የሽብር ቡድኑ አመራሮችና ደጋፊዎች የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ” የአብይ ጦር” እያሉ ደጋግመው የሚጠሩት በምክንያት እንደሆነ ያመለከተው ተባባሪያችን ባገነው መረጃ ከተገኘው የውይይት ሰነድ ውስጥ የአገር መከላከያ እንደሚፈርስ የተደረገ ውይይት ይገኝበታል።
ሟቹ ሴኮ ቱሬ ሰራዊቱን ” ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል” ማለቱን ያስታወሱት የዜናው ባለቤቶች ” መንግስት ሆነው ጎን ለጎን የራሳቸውን ሃይል ካደራጁ በሁዋላ አስቀድሞ መከላከያውን ማፍረስና መምታት የተፈለገው ለውጭ ሃይሎቹ ድጋፍ ሲባል ነበር” ብለዋል። ሲያስረዱም “የአገር መከላከያ ፈራርሷል በሚል የባለ ተጋ ዓገሮችን ጥቅም ማስከበር የሚችሉት እነሱ ብቻ እንደሆኑ አድርጎ ለማሳየት ያቀዱት እቅድ ነው”
አሁን ተገኘ በተባለው የውይይት ሰነድ የአገር መከላከያ ፈርሶ ትግራይ የተደራጀው ሃይልና ከኦነግ ሸኔ በሚመጣ መጠነኛ ሃይል መልሶ ለማደራጅት እቅድ መኖሩን አመላካች ሆኖ ተገኝቷል።
በተደጋጋሚ የአገር መከላከያን ስም ለማቆሸሽ የሚደረገው ዘመቻ ተራ ዘመቻ ሳይሆን ጦሩን ልክ እንደ ቀድሞ በትኖ ለማኝ ለማድረግ ይረዳ ዘነድ ቅድመ ዝግጅት መሆኑንን ተባባሪያችን ዜናውን የነገሩትን ጠቅሶ አመልክቷል።
የአሸባሪው ቡድን ደጋፊዎች በገሃድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚያራክስና ጸረ ሕዝብ አቋም እንዳለው መቀስቀስ ከጀመሩ መሰንበታቸው፣ በሃያ ዓመት የትግራይ ቆይታው ህዝብ አክባሪ፣ ታማኝ፣ የልማት አጋር፣ በተለይ የትግራይ ህዝብን ሰላም ሲተብቅ የኖረ፣ ዕድሜውን በምሽግ ውስጥ ያሳለፈ ሰራዊት ሆኖ ሳለ ሳያስበው በተኛበት ታርዶ፣ ተረሽኖ፣ እንደ ምርኮኛ ታግቶ፣ አስከሬኑ አሞራ እንዲበላው ተደርጎ፣ የሴቶች ጡታቸው ተቆርጦ … በታሪክ ሊሽር የማይችል ግፍ እንደተፈጸመበት ምስክሮች በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይህ የሆነው ብሄር ተመርጦ ሳይሆን በኦሮሞ፣ በአማራ፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ… ከትግራይ በቀር በሁሉም ብሄረሰብ አባላት ላይ እንደሆነም አስታውቀው ነበር።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ትጥቅ እንዲፈቱ ከተደረጉ በሁዋላ ጡታቸው ስለተቆረጠ፣ እንግልትና ስቃይ ስለደረሰባቸው፣ ሲኖ ትራክ ስለተነዳባቸው፣ ተገደው ስለተደፈሩ የመከላከያ ሴት አባላት እስካሁን ያለው ነገር የለም። ኮሚሽኑ እነ አቶ ስብሃትን እስር ቤት እየተመላለሰ እንደሚተይቅ ገልጾ ሪፖርት ሲያወጣ ግፍ የተፈጸመባቸው ሴት ወታደሮች አዲስ አበባ ማገገሚያ እያሉ እንዲያናግራቸው ቢጠይቁም ፈቃደኛ አልሆነም። ከቀናት በፊት የትግራይ ልጆች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑንን ተቃውሞ ሪፖርት ሲያዘጋጅ ፖሊስ በይፋ ያሳየውን ኢግዚቢት በሪፖርቱ አላካተተም። ኮሚሽኑ የማይካድራን ጭፍጨፋ የመጨረሻ ሪፖርትም እስካሁን ይፋ አላደረገም።
ገለልተኛ ዜጎችና ነዋሪዎች ንጽህ የትግራይ ተውላጆች እንግልት እንዳይደርስባቸው፣ ፖሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ በማህበራዊ ገጻቸው ሲያሳብቡ ማስተዋል ተችሏል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም።… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች







