Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ዓለም ዓቀፍ ወንጀል
News

ዓለም ዓቀፍ ወንጀል

Ethioreview newsEthioreview news—July 13, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ይህ ፎቶግራፍ ብዙ ይናገራል። ከክምር ቃላት በላይ ጠለቅ ያለ መልዕክት አዝሏል። አንዳንድ ፎቶግራፎች ታሪክን ይቀይራሉ። የአሜሪካ ቬትናም ጦርነት ላይ የአንዲት የዘጠኝ ዓመት ልጅ ፎቶግራፍ ዓለምን አስደንግጧል። በአሜሪካን ትላልቅ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሶ ጦርነቱ እንዲቆም የዚያች ልጅ ፎቶግራፍ ሚናው ከፍተኛ እንደነበረ ይነገራል። ራቁቷን ከጦርነት መሀል እያለቀሰች የምትታየው ቬትናማዊት ልጅ ፎቶግራፍ ዓለም ዓቀፉን የፑልቲዘር ሽልማትን ተቀዳጅቷል። ፎቶግራፉ ከሺህ መጻህፍት፡ ከአያሌ ፊልሞች በላይ ስለቬትናሙ ጦርነት ታሪክን እየነገረ በታሪክ ወደፊትም ይኖራል።

ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሰኞ ዕትሙ ህወሀትን ለማጀገን በሚል ይዞ የወጣው ፎግራፍም እንደቬትናማዊቷ ህጻን ፎቶግራፍ ታሪክ መቀየር የሚችል መሆን አለበት። ፎቶግራፉ የህወሀትን የክፋት ጥግ በማሳየት ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ምድር ምን እየተደረገ እንዳለ እንዲያውቀው የማድረግ ግዙፍ ሃይል አለው ብዬ አምናለሁ። በእርግጥ ኒውዮርክ ታይምስ የህወሀትን ‘አይበገሬነት’፡ ‘ህዝባዊነት’ ያሳያል ያለው ፎቶግራፍ ከታሰበለት መልዕክት ይልቅ የህወሀትን ጉድ ያጋለጠ ሆኖ ለዓለም ቀርቧል።

ዕድሜአቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናት ለጦርነት እየተማገዱ መሆኑን ፎቶግራፉ ምስክር ሆኖ ይታያል። ህወሀት አከርካሪው ተሰብሮ ወደ ቆላ ተምቤን ከመውረዱ በፊት ጀምሮ ህጻናት ወታደሮች በከፍተኛ ቁጥር መልምሎ በለብለብ ስልጠና ለጦርነት ሲማግድ ቆይቷል። ይህ ዓለም ዓቀፍ ወንጀል በመሆኑ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም።

እንደህወሀት የትግራይን ህዝብ ስቃይ መከራ የጋተ አገዛዝ የለም። ከፍጥረቱ ጀምሮ የትግራይን ህዝብ ለእኩይና ሴጣናዊ ዓላማው ሲገድል፣ ሲያስገድል ኖሯል። አሁንም እያንቋረረ፣ ሞቱን በቅርብ እያየ የትግራይ ህዝብ ላይ ታላቁን እልቂት አውጆ እየተንቀሳቀሰ ነው። በረሃ እያለ ህዝቡን እንደአልቂት ተጣብቆት በረሃብና በጦርነት ሲቆላው እንደነበር ቅን የትግራይ ልጆች የሚመሰክሩት ሀቅ ነው።

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

ስልጣን ላይ ወጥቶ በቆየባቸው 27ዓመታት በስሙ እየማለ፣ ጥቂቶችን የሀብት ጋራ ላይ እንዲወጡና የአንድ መንደር ስረወ መንግስት እንዲተከል አድርጓል።

በእነዚህ ዓመታት የትግራይን ህዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ወገኑ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ በማድረግ የጥላቻ ግድግዳ ሲያቆም ነው የከረመው።

ይኸው ያ ጦስ ሁለቱንም ወገኖች ዋጋ ማስከፈል ጀምሯል። በፎቶግራፉ ላይ የሚይታየው ትዕይንት የሚያረጋግጥልን ህወሀት በመጪው ትውልድ ላይ ቂምና ጥላቻ ለማቆየት እየሄደ ያለበትን ርቀት ነው።

ይህ ፎግራፍ ከወጣ በኋላ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፡ የህጻናት መብት ላይ የሚሰሩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት፡ ለሰው ልጅ እንቆረቆራለን የሚሉ እጅ ጠምዛዥ መንግስታት አንድ ነገር ይላሉ ብዬ ጠብቄ ነበር።

ልብ ያላቸው፡ ትንሹ ፈጣሪ ለሆነው ህሊናቸው የተገዙ ጥቂት የትግራይ ምሁራን ከፎቶግራፉ በኋላ እንኳን የህወሀትን የእብደት አካሄድ በግልጽ ለማውገዝ ወደ አደባባይ ይወጣሉ የሚል ግምት ነበረኝ።

በእርግጥ ፎቶግራፉ ከወጣ 24 ሰዓት ስላልሞላው ቸኩዬ ሊሆን ይችላል።

ዓለም ይህን ድርጊት ካላወገዘው፡ እንደእርጎ ዝንብ በሰው ሀገር ጥልቅ እያሉ የሚፈተፍቱ ሀገራት ህወሀትን ተው ካላሉት ስለሰው ልጅ መብት ለመከራከር ሞራል ሊኖራቸው አይገባም። ከዚህ በላይ ወንጀል ምን አለ?

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ፎቶግራፍ ይዞ የዲፕሎማሲ ዘመቻ መክፈት አለበት። ሳይታሰብ ድንገት የተገኘ ማስረጃ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።

ጩኸቱ ለምን እንደነበረ ይህ ፎቶግራፍ የሚነግረን ነገር አለ። ይህን መጠቀም ይገባል። በገዛ እጃቸው ትልቅ ዶክመንት ሰጥተዋልና።

Messay Mekonnen

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በአሸባሪው የትህነግ ተጠርጣሪ አባላት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ እንደሚመሠረት ተገለጸ።
ዓለም ዓቀፍ ወንጀል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2