Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  «ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠት በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብር ይመክናል!» የአ.አበባ ከከተማ አስ.በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
News

«ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠት በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብር ይመክናል!» የአ.አበባ ከከተማ አስ.በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

Ethioreview newsEthioreview news—July 15, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠው የአቋም መግለጫ ሙሉ ቃል፡-

ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠት በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብር ይመክናል!

በሰሜን ኢትዮጵያ ከተካሄደዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ መንግስት ህዝቡ በጦር እንቅስቃሴ ሳይረበሽ በጥሞና ጊዜ ፋታ አግኝቶ እርሻውን የሚያከናውንበት የእርዳታና ድጋፍ አቅርቦቱም ያለሰበብ ሳይደናቀፍ የሚከናወንበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ወስዷል፡፡

ሆኖም ግን ይህ አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ መንግስት የታወጀውን ህዝብን ያስቀደመ የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠቅሞ ከስህተቱ ተምሮ የትግራይን ህዝብ ከከፋ ስቃይ እና መከራ መታደግ ሲገባው፤ የመንግስትን አርቆ አስተዋይነት እንደሽንፈት ቆጥሮ ከተደበቀበት ጎሬ ወጥቶ እንደ ድል አድራጊ በየአካበቢው መፎከር ብቻ ሳይሆን ከዚያም አልፎ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም የተዘረጉትን መልካም የሰላም እድሎችን ሁሉ ዝግ በማድረግ እንደገና ጥቃት ከፍቷል፡፡

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

ጥቃቱ የተከፈተብን መላ ኢትዮጵያውያን አለምን ባስደነቀ መልኩ እጅግ ሰላማዊ የሆነ ምርጫ አከናውነን የጋራ አሸናፊነታችንን ባረጋገጥንበት ለዲሞክራሲ ግንባታ ያላንን ቁርጠኝነት በተግባር ባሳየንበት ወቅት መሆኑም ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብን በመሙላት ላይ ባለንበትና መላው ኢትዮጵያውያን የሃገራችንን የትንሳኤ ዘመን ብስራት የሆነው የህዳሴ ግድባችን ላይ እየተቃጣ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ለሉአላዊነታችን መከበር በአንድነት ትከሻ ለትከሻ በቆምንበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን በተለየ ስሜት እንድንመለከተውና ሃላፊነታችን ላቅ ያለ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ለዚህ እኩይ አላማው፤ እንክብካቤ የሚያሻቸው ፤የጦር መሳርያ ሳይሆን ደብተር ማንገብ የሚገባቸውን ህፃናት፤ የሃይማኖት አባቶችን ፤አዛውንቶችን ደካሞችን ጨምሮ በግዳጅ በጦርነት በመማገድ ለሃገራችን ብቻ ሳይሆን ለአለም አቀፍ ህግጋት ተፈጻሚነት ደንታ የሌለው ጨካኝ ቡድን መሆኑን በይፋ እያስመሰከረ ይገኛል፡፡

አንዳንድ አለም አቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎቻቸዉ ጭምር ይህ የሽብር ቡድን መንግስት ተግባራዊ ያደረገዉን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ወደ ጎን በማለት በንጹሀን ላይ እምነትን ጭምር መሰረት አድርጎ ግድያና ጭፍጨፋ ሲያካሂድ፤ባለዉ አቅም ሁሉ ትንኮሳ ከማድረግ አልፎ ጥቃት ለመፈጸም ሲዘጋጅና ሲጀምር የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ እና የጋዜጠኝነትን ስነ-ምግባር በጣሰ መልኩ ጉዳዩን አይቶ እንዳላየ ሲያልፉት ተመልክተናል፡፡

ይባስ ብለዉ አሁን ላይ መንግስት የህልዉና ዘመቻዉን በጀመረበት ሰዓት የተኩስ አቁም ይደረግ በሚል የተለመደ የሽብር ቡድኑን የማዳኛ ታክቲካቸዉን ለመተግበር ሲሯሯጡ ታዝበናል፤ ይህ ኢ-ፍትሃዊ ተግባር ለመላዉ የኢትዮጰያ ህዝብ ድብቅ አላማቸዉን ይፋ ያደረገ ሆኗል፡፡

ወትሮም ቢሆን እኛ ያልመራናት ኢትዮጵያ ሰላም ሆና ማደር የለባትም ‘’እኔ ከሞትኩ፤ ሰርዶ አይብቀል’’ እንዲሉ በተደጋጋሚ እኔ ካልመራዉ ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት! በማለት ሲናገር የከረመውና ላለፉት አመታት አቅሙ በቻለው ሁሉ ከውስጥም ከውጪም ካሉ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ ጋር ሲሰራና ሲያሰማራ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራዎችን ሲያደርግ የቆየው ይህ ቡድን ከጥፋት ተልእኮው መቼም የማይመለስ መሆኑ ለማንም ተመልካች ግልፅ ነው፡፡

አሁንም ቢሆን የተጀመረው ማጥቃት እና ትንኮሳ፤ የአንድ ወገን የአንድ አካባቢ ጥቃት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ጥቃት በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ፤ ፀረ ኢትዮጵያ አቋም የገፋው በህልውናችን ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው፡፡

ይህ አሸባሪ ቡድን የሃገራችን ህዝቦች መተባበርና አንድነት እንቅልፍ የሚነሳው፤ ኢትዮጵያ ተበታትና እስካላየ አልያም እራሱ እስካልመራ ድረስ መቼም ቢሆን አርፎ የማይቀመጥ፤ ይህንንም በተደጋጋሚ በተግባር ያረጋገጠ የኢትዮጵያውያን ሁሉ የጋራ ጠላት ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን እንደሁልጊዜውም በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው ሰራዊታችን ኩራት ይሰማናል፡፡ ለሰራዊታችንም ማንኛውንም ድጋፍ ማድረግን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

በዚህ ሰአት አሸባሪ ቡድኑ የሚያደርሰውን ጥቃት በመመከት የተጀመረው ሃገር የማዳን ተልእኮ ግቡን እንዲመታ መላው ህዝባችን ለሃገሩና ለሰራዊቱ ሁሌም እንደሚያደርገው ያልተቆጠበ ሁለንተናዊ ድጋፍ በገንዘብ፤ በጉልበትም ሆነ በዕውቀት አቅም በፈቀደው ሁሉ በማድረግ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

ወጣቶችና አቅማችን የሚፈቅድ ሰራዊታችንን በመቀላቀል ፤ሌሎቻችን ደግሞ የሞራልና የስንቅ ድጋፋችንን አጠናክረን በመቀጠል ደጀንነታችንን በተግባር የምናሳይበት መሆን ይኖርበታል፡፡

መላው ኢትዮጵያውን፤ በዚህ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሸባሪው ቡድን በሚነዙ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሳንወናበድ፤ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር፤ እርስበእርስ በመመካከርና በመደጋገፍ፤ የተቃጣብንን አገራዊ ጥቃት በህብረትና በአንድነት፤ እንደ አንድ ልብ ሆነን ልንመክት ይገባል፡፡

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ የፀጥታ ሀይሉን በጋራ በትብብር በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስምሪትና ተግባር የምትተቹና እየከፋፈላቹህ በማህበራዊ ሚዲያ የምትፅፉ ከዚህ ድርጊታቹህ በመቆጠብ ይልቁንም የፀጥታ ሀይሉን ስምሪት ለፀጥታ አካሉ ትተን፤ በሀገራችን ላይ ከውስጥም ከውጭም በየአቅጣጫው የተከፈተውን የዲጂታል ሚዲያ ጦርነት በትብብርና በአንድነት ልንመክት ይገባል፡፡

የከተማችን ፊንፊኔ ነዋሪዎች ለሰራዊታችን ከምናደርገው ያልተቆጠበ ድጋፍም ባሻገር የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ፤ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በትብብርና በቅርበት በመስራት፤ ለህዳሴ ግድባችን ድጋፋችንን በማጠናከር ፤ የጀመርነውን የከተማችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ እንቅስቃሴ እንቀጥላለን፤ አገራዊ ሃላፊነታችንን በንቃት እንወጣ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!

ጀግኖች አባቶቻችን ተባብረውና ተጋግዘው በጀግንነት ያቆዩልንን ነፃ ሃገር እኛ ልጆቻቸው የአባቶቻችንን ታሪክ በመድገም የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ህብረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ሃምሌ 2013
አዲስ አበባ

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ትግሬ ከሁሉም በላይ የላቀ ዘር እንደሆነ በይፋ እውቅናና ሥልጣን ይገባዋል”ትህነግ
Sub-Saharan African states should not ignore western complicity on Ethiopia
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2