Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  ትህነግ ‘የሰው ልጆች’ መብት ተቆርቋሪ ሆነ፤ እኛም አፈርን
SOCIETY

ትህነግ ‘የሰው ልጆች’ መብት ተቆርቋሪ ሆነ፤ እኛም አፈርን

Ethioreview newsEthioreview news—July 4, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዛሬ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ የሰውል ልጆች መብት ተቆርቋሪ ሆኖ፤ የሰው ልጆች መብት ካልተከበረ ተኩስ እንደማያቆም ይፋ ሲያደርግ ይህ ታሪክ ትዝ አለኝንና ላኩላችሁ። የወያኔን የሰው ልጆች ተቆርቋሪነት ስሰማ ከመላው ቤተሰቤ ጋር አፈርን። ዛሬ ሶማሊ ክልል ከስር በጽሁፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ለማድረግ መዋጮ እያሰባሰብን ነው ስለትህነግ ደግነት የሰማነው። ጅግጅጋ

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆንያ እየሠፈረ በፈለገበት ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዓላማው የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጪ ግምባር (ህወሃት)፤ በኦሮሞ ተቃውሞ #oromoprotest እና በአማራ ተጋድሎ #amhararesistance የተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዕንቅልፍ ስለነሳው በተለይም ደግሞ የሁለቱ በኅብረት መቆም ኅልውናው ላይ አደጋ ስለጣለበት ሶማሊና አፋር ክልል መንጎዳጎድ ጀምሯል፡፡

ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታህል ደንታ የሌለው ህወሃት የኦጋዴንን ሕዝብ እንዴት እንደፈጀ፣ ሴቶችን (ህጻናትንና ወንዶች ልጆችን ጨምሮ) እንደደፈረ፣ ለመከራና ለስቃይ እንደዳረገ የተረሳ መስሎት ሰሞኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቅኝቱንም ሆነ ዜማውን የሶማሊ አድርጎታል፡፡ የህወሃትን ግፍ እንኳንስ የክልሉ ነዋሪዎች ሊረሱት ስዊድናውያኑ ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን እስከ ሞት የሚረሱት አይደለም፡፡

“ዝም የተባለው ዳርፉር” በመባል ከዳርፉር እልቂት ጋር በእኩልነት የሚጠቀሰው የኦጋዴን ሰቆቃ ፈጻሚዎች ጨካኞቹ ህወሃቶችና ተባባሪዎቻቸውን ድርጊት ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ዳጎስ ያለ መረጃና ማስረጃ የያዙበት ነው፡፡

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

የኦጋዴን ጉዳይ የመለስ ራስምታት መሆኑን ጠቅሶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቦታው ስለተፈጸመው ግፍ መግለጫ አውጥቶ ነበር፤

“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቦታ ተወስነው መኖር የማይችሉ አርብቶ አደሮች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች (ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን) ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ” (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ከሶስት ወር በፊት “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም አውጥቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ June 25, 2016 አትመነው ነበር፡፡ የሰሞኑ የህወሃት የማስመሰያ “የፍቅር እሽሩሩ” ፈጽሞ የማይረሳ እንደሆነና የኦጋዴን ወገናችን መከራ የእኛም በመሆኑ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህወሃት ቀንበር ነጻ መውታት ያለበትና ፍትህ ማግኘት የሚገባው መሆኑን ለማሳየት እንዳል ደግመን አትመነዋል! “በጭራሽ አንረሳውም!!”


 “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

“አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

ogaden 4

የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል)

ogaden 1

“በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላ የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ ከተናገረችው፡፡

የሚዲና የዕርዳታ ሥራዎችን የሚያካሂዱ ሁሉ ወደ ኦጋዴን እንዳይገቡ በህወሃት ትዕዛዝ ተደርጎባቸው ባለበት ባሁኑ ወቅት በኦጋዴን የሚካሄደው ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፤ እስር፣ እንግልት፣ ወከባ፣ … በድብቅ ቀጥሏል ይላል ጋዜጠኛ ግራሃም፡፡

ዘጋቢ ፊልሙን ለመሥራት መረጃው የተሰበሰበው ከሚሊታሪው የኮበለሉና ሌሎች ለህይወታቸው ያልሳሱ ደፋሮች በሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ ኮብለለው በቅርቡ ኬኒያ ልትዘጋው ወደ ወሰነችው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ሦስት ሴቶች የህወሃት ሠራዊት ስላደረሰባቸው መከራ፣ ሥቃይና አስገድዶ መድፈር ተግባራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሚሪያም

ወደ ዳዳብ በግንቦት 2006ዓም የመጣችው ሚሪያም ለሁለት ዓመት ተኩል እንዴት እንደተሰቃየች፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዴት እንደተፈጸመባት ትናግራለች፤

ogaden 10

“እንደ ማሰቃያ ይሆን ዘንድ እስኪደክመኝ ድረስ ሬሣ አቅፌ እንድቆም ተደርጌአለሁ፤ ከዚያም ሚጥሚጣ የሞላበት ላስቲክ በራሴ ላይ አስረውብኛል፤ ገመዱን ሲያስሩት አጥብቀው ከአንገቴ ጋር በማሰራቸው ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡ ከዚያ ለብዙ ሆነ እየተፈራረቁ አስገድደው ደፈሩኝ …”

“ኦጋዴን በሚገኘው እስርቤት 1097 የምንሆን ነበርን፤ ቁጥሩን በትክክል አውቀዋለሁ ምክንያቱም በየቀኑ ማለዳ ላይ እያሰለፉ ከቆጠሩን በኋላ በቡድን በቡድን እያደረጉ ይከፋፍሉን ነበር፤ …

“(የተያዝን ጊዜ) እህቴን ጉሮሮዋን አንቀው መረጃ አምጪ አሏት፤ ምንም እንደማታውቅ ብትነግራቸውም አልሰሟትም፤ ከሌሎቻችን ጋር ተቀላቅላ እንድትቀመጥ አደረጓት ከዚያም ሁላችን እያየን አራት ቤቶቻችን አቃጠሏቸው፤ ቤቱን እያቃጠሉ እህቴን ከመካከል ነጥለው ግምባሯ ላይ በጥይት መቷት፤ እህቴን እስከሞት ስትደማ አየኋት፤ ከእርሷ አጠገብ ሌላ ሴት ልጅ በድብደባ ብዛት ሞታ ነበር፤ ከዚያም እኔን ሬሣ ባለበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉኝ፤ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ አራት ቀንና አራት ምሽት አሳለፍኩ፤ ጥፋተኛ መሆኔን እንድናዘዝ ምርመራ ይካሄድብኝ ነበር፤ አለበለዚያ መጨረሻዬ እንደ ሬሣው እንደሚሆን ይነግሩኝ ነበር፤ እኔም ምንም የምናዘዘው የለኝም የምታርዱኝ ከሆነ እረዱኝ አልኳቸው፤ (ጉድጓድ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ) ከሬሣው መካከል አንዱ ጉሮሮው ታርዶ፤ አንገቱም በዱልዱም ነገር ተቆርጦ ጭንቅላቱ እዚያው የቀረው አካሉ ጎን ነበር፤…”

አናብ

በመስከረም 2007ዓም ወደ ዳዳብ ካምፕ የመጣቸው አናብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅምላ ከገደሉ በኋላ በጅምላ የሚቀብሩበትን ቦታ በመደበቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ አንዳንዶቹ መቼም አይገኙም፤ አንዳንዶቹ ግን በቁሻሻ ጉድጓዶች ውስጥ ተገኝተዋል” ትላለች፡፡

Ogaden 11

በእርሷ ላይ የደረሰውን በተመለከተ ስትናገር አናብ እንዲህ ትላለች፤ “ወደ እስር ቤት ተወስጄ በሽቦ ታነቅሁኝ፤ ይህ ዓይነቱን ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ቆይተው በኋላ እስርቤት ተዉኝ፤ በተያዝኩ ጊዜ ከፊት፥ ከኋላና ጭኔ ላይ በጎማ ጠፍር ገርፈውናል፤ ከእኔ ጋር የተያዙ አምስት ልጃገረዶች ነበሩ፤ ከተያዙት ውስጥ ትልቋ 19ዓመቷ አካባቢ ነበር፤ ትንሽዋ ደግሞ ወደ 15ዓመት አካባቢ ነበረች፤ በተያዝንበት ወቅት ልጆቹን ክፉኛ ሲደበድቧቸውና በሰደፍ ሲመቷቸው አይቻለሁ፤ ልብሳቸውንም ቀዳድደውባቸው ብጣቂ እራፊ አድርገው ተመልሰዋል፤ ይህንን በየጊዜው የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ …

“መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”

ፋጡማ

Ogaden 12

እንደ ሚሪያም በግንቦት 2006 ዓም ወደ ዳዳብ የመጣችው ፋጡማ “ወታደሮቹ እናንተ የኦጋዴንን ሰዎች እናጠፋችኋለን፤ ምንም ዓይነት ነዋሪ እዚህ አካባቢ አንፈልግም፤ እንጨርሳችኋለን” ይሉናል፡፡ “እስርቤት ሳለሁ አንቀውኝ ነበር፤ በሳንጃም ወግተውኛል፤ በየጊዜው መላ አካላቴን ደብድበውኛል፤ ጭንቅላቴን በኤሌትሪክ ጠብሰውታል፤ የማያደርጉት ዓይነት ስቃይ የለም …” በማለት ምሬት እና ሰቆቃ በተሞላበት ድምጽ ምስክርነቷን ስትሰጥ ትደመጣለች፡፡ ኦብነግ በአካባቢው እንዳለ እና ሠራዊቱ አንድ መቀመጫ ቦታ እንደሌለው፤ በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሰፈር እንደሚመጡ እና የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ፋጡማ ትናገራለች፡፡

ህወሃት በበረሃ በነበረበት ጊዜ ተጋዳላዮቹ በየምሽቱና በየሌሊቱ ወደ መንደራቸውና ሰፈራቸው በሚመጡበት ጊዜ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብና መጠጥ እያሲያዙ፤ ስንቅ እንየቋጠሩ ይልኩ ነበር በሙስና ወንጀለኛ ሆነው ታስረው የተፈቱት አቶ ስዬ አብርሃ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እንዲያውም የራሳቸውን እናት ጠቅሰው ብዙዎችን ይመግቡ እንደነበርና ለበርካታ ተጋዳላዮች “እናት” እንደነበሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በህወሃት አዛዥነት ወደ ሥፍራው የተላከው ሠራዊት አስገድዶ መድፈር አንዱ የጥቃት መሣሪያው ነው፡፡ በወታደራዊ ሠፈሮች ውስጥ ሴቶች ለወሲብ መገልገያ ሆነዋል፤ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በበርካታዎች ይደፈራሉ በሚለው የግራሃም የቪዲዮ ዘገባ ላይ የስቃይ እንባ የምታፈሰውን ሚሪያም “በተደጋጋሚ ተደፍሬአለሁ፤ ድርጊቱ መደበኛ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ተቀበልነው” ስትል ያሳያል፡፡ “ብዙዎች በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ አንዳንዶችም የሚጥል በሽታ ይዟቸዋል ሌሎችም እውር ሆነዋል፤ እኔም ራሴ ከደረሰብኝ ስቃይና ድብደባ የተነሳ አሁን እየተሻለኝ ቢሆንም የጡንቻ መኮማተርና የሚጥል በሽታ ይዞኛል፡፡”

Ogaden 13

የኦጋዴን ጭፍጨፋ መሃንዲሱና ጀማሪው ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ነው፡፡ የሙት ውርስ እንጠብቃለን የሚሉት አወዳሾቹም በሙት መንፈስ እየተመሩ ግፉን ቀጥለውበታል፡፡

የኢትዮጵያን ስም ይዞ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የዘመተው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሠራዊት ኦጋዴን በደረሰበት ጊዜ የፈጸመውን እማኞቹ በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ይሁኑ ወይም ልዩ ፖሊስ እኔ አላውቅም” የምትለው ፋጡማ ሰፈሮቻቸው በወራሪው ሠራዊት ከተከበበ በኋላ ከብቶቻቸው፤ ግመሎቻቸው፤ … በአጠቃላይ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ትናገራለች፡፡ ከሁለቱ ሴቶች ጋር በመስማማትም ወንዶች እየተነጠሉ እንደተገደሉ ታስረዳለች፡፡ በተለይ የተማሩ የሚባሉ የኦጋዴን ወጣቶችን እየለዩ እንደገደሉ የሟች ቤተሰብ የሆኑት እነዚህ እህቶች በቃለምልልሱ ላይ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ሁልጊዜ የሚባሉትም “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” መሆኑን ግፍ፤ እልህና ሲቃ በሞላው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ግዢው ህወሃት በልዩ ሁኔታ ያሰለጠናቸው በትምህርት ያልታነጹ፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሌላቸውና ከወሮበላ የማይተናነስ ባህርይ ያላቸው ጨካኝ ፓራሚሊታሪዎች እንደሆኑ ያስረዳል፡፡

ህወሃትንና ሹሞቹን በዚህ የኦጋዴን ዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ በሚፈጸም ወንጀል ማስከሰስ፤ ለፍርድ ማቅረብ የኦጋዴን ወገኖችንና የመላ ኢትዮጵያ ልጆችን ትብብር ይጠይቃል፡፡ ስቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ፣ … ካላስተባበረን ሌላ ምን ሊያስተባብረን ይችላል? ሰዎች ደስታን እንደመሰላቸው ሊተረጉሙት ይችላሉ፤ ግፍ ግን ቋንቋውና ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው – እስከ አጥንት ይዘልቃል፤ መቅኔን ይቆጠቁጣል፡፡

Ogaden 15

ከአዘጋጆቹ፤ ምንም እንኳን በጋዜጠኛነት ተግባር ላይ የምንገኝ ቢሆንም የእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ያመናል፤ ያስለቅሰናል፡፡ ከአንዲት እናት የተወለድን ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናችን የሴቶች ስቃይ ከምንም በላይ ልባችንን ያሳምማል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ስቃይ ማቅረብ ሌላውን ዜና የመዘገብ ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድርጊቱ አሁን የተፈጸመ ያህል እየተሰማቸው አሁንም ትኩስ እንባ እያፈሰሱ ስቃያቸውን የገለጹት እህቶቻችን ህመም የማያመውና የማያስለቅሰው ህወሃትና በድንቁርና ጭለማ ውስጥ የገቡት ጀሌዎቹ ናቸው፡፡ ህወሃት ይህንን ዓይነቱን ግፍ ሲደርግ ኖሯል፤ አሁንም እያደረገ ነው፤ ኢትዮጵያ ግን አሁንም ከእናንተ የኦጋዴን ግፉአን ጋር ታለቅሳለች፡፡


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Somali Region Launches Fundraising To Rehabilitate Victims Of TPLF Atrocities
Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2