Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  «ሂዱ አማራንና አፋርን እንዲሁም ቀሪዉን የኢትዮጵየሠ ህዝብ ውረሩ፣ ሀብት ንብረቱንም ዝረፉ ኢትዮጵያንም አፍርሱ…»
News

«ሂዱ አማራንና አፋርን እንዲሁም ቀሪዉን የኢትዮጵየሠ ህዝብ ውረሩ፣ ሀብት ንብረቱንም ዝረፉ ኢትዮጵያንም አፍርሱ…»

Ethioreview newsEthioreview news—August 15, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ሙሉቃል


አሸባሪው ትህነግ የአማራ ሕዝብ ላይ ያለሀጥያቱ “ሒሳብ አወራርዳለሁ” እያለ በሚዲያ ተናግሯል። በአደባባይ ዓለም እየሰማው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል መግባት ካለበት እንደሚገባ ገልፆል። ትርክቱም ሆነ ድርጊቱ በእውን የማይታሰብ የእብደት ገጸ ባህሪ ቢመስልም ከመቼውም ጊዜ በላይ በግብር ትርክቱን ሊኖረው የጥፋት ሰይፉን በአማራና በኢትዮጵያ ላይ መዝዟል።

“የአማራ ሕዝብ ላይ ሒሳብ አወራርዳለሁ” ያለው ትህነግ፣ ሽብርና ወረራ ለሚፈፅሙለት የሽብር አባላቱ ምን አይነት ተልዕኮ እንደሰጣቸው ከምርኮኞች በምርመራ የሰበሰብናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።

በርግጥም ትህነግ በእብሪት በወረራቸው አካባቢዎች እየፈፀማቸው ያሉ ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በወንድም የአፋር ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ የጥፋት ሰይፉን መዝዟል። በዚህም የአፋር ሴቶችን ደፍሯል፣ ሕጻናትንና ወጣቶችን ገድሏሎ፣ የአርብቶ አደሩን የቁም እንስሳት በገፍ ዘርፏል። የጠኔ ማወራረጃው አድርጎታል። አቅዶ የመጣውን ቂም በቀል በግልፅ በተግባር እያሳየን ነው።

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

በሌላ በኩል በየቀኑ ሲረግመው የሚውለውን የአማራ ልሂቅ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው ትህነግ፣ ነገ አድገው አማራን ይጠቅማሉ ያላቸውን የአማራ ልጆች የማጥፋት ውጥን ይዟል። በዚህም ትውልዱን ለማምከን ባቀደው ክፉ እቅድ መሰረት በየከተማው ያገኛቸውን ታዳጊ ወጣቶች በራቸው ላይ ገድሎ ጥሏቸዋል።

ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ባለሀብቶች፣ ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ ትኩረት አድርጎ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከወሰነ ቆይቷል። የአእምሮ ህሙማንን በስለላ ሲያሰማራ የለመደው ትህነግ፣ ሁሉም እንደ እሱ መስሎትና በህመም የሚሰቃዩትንም በየደረሰበት አካባቢ ገድሏቸዋል። ከሚገድላቸው በተጨማሪ ሕዝብን በገፍ በማፈናቀል ከቀየው ተፈናቅሎ ተቅበዥባዥ ማድረግን፣ እረፍት መንሳትን የደስታው ምንጭ አድርጎታል።

ሕዝብ ሲፈናቀልለት ከተማውን በሙሉ ዘርፎ ለማሸሸትም እድል እየፈጠረ ይገኛል። ትህነግ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ለሚኖሩት የሽብር አባላቱና ተባባሪዎቹ አማራን ወርረው እንዴት ንብረቱን ዘርፈው ወደ ትግራይ እንደሚወስዱት የዘረፋ ዕቅድ አውጥቷል። አንዳንድ የትግራይ ተወላጆችም ለአማራ ወዳጆቻቸው እስከ መስከረምና ጥቅምት ባለው ጊዜ ያለቀው ኃይላቸውን አልቆ ወረራውን እንደሚያሳኩና የአማራን ሀብትና ንብረት ዘርፈው፣ የተረፈውንና መውሰድ የማይችሉትን አውድመው የአማራን ሕዝብ አደኸይቶ የመበቀል አላማ እንዳላቸው ገልፀውላቸዋል። ይህን መረጃ ከምርኮኞችና ከመረጃ ክትትላችን ማረጋገጥ ችለናል።

የትህነግ አሸባሪ ኃይል አባል አልቆ አማራም ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚልሰው የሚቀምሰው ማሳጣት የሽብር ቡድኑ ግብ ነው። ወትሮም በአማራ ቁልቁለት፣ በተዳከመች ኢትዮጵያ ታላቋን ትግራይ የመፍጠር ፖለቲካዊ ግብ ይዞ የተነሳው የጥፋት ኃይል፣ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያውያን የደም ጎርፍ ራሱን ነጻ ለማውጣት ጋኔሉን ከጠርሙሱ አስወጥቶታል። ዛሬ በአማራም ሆነ በአፋር ወረራና የሽብር ተልዕኮ ላይ የተሰማሩ የሽብር ቡድኑ አባላት ከጠርሙሱ የወጣው ጋኔል ተምሳሌት ናቸው።

አሸባሪ ቡድኑ በወረራቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች የተደራጀ ኃይል አሰማርቶ የመንግስት ተቋማትን፣ የግል ንግድ ቤቶችን፣ የግለሰብ ንብረቶችን በከባድ የጭነት መኪናዎች እየጫነ ይገኛል። አጠቃላይ ግቡ የኢትዮጵያን ሕዝብ 100 ዓመት ወደኋላ መጎተት ነው። ይህን ደግሞ በአማራና በአፋር ክልሎች እንደሕዝብ ወረራ ፈጽሞ ጀምሮታል።

አሸባሪውና ወራሪው ትህነግ በእብሪት በወረራቸው የአማራና አፋር አካባቢዎች የጀመራቸው የዘረፋና የጭፍጨፋ ወንጀሎች የወረራ አላማው ቢሳካለት በመላ ኢትዮጵያ ምን ሊያደርግ እንደሚችል እያስመሰከረ ነው። አነስተኛ የመንገድ ዳር ኪዮስኮች ሱቅ ውስጥ ገብቶ ቁሳቁሶችን ዘርፎ ከመጫን በተጨማሪ በወረራቸው አካባቢዎች ያገኛቸውን ተሽከርካሪዎች በሎቬድ ጭኖ አይን ያወጣ ዘረፋ ውስጥ ይገኛል።

በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ሌሎችን በሐሰት ሲከስስ የነበረው አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው የክልላችን አካባቢዎች ግን በግልፅ ዘረፋን የወረራው አላማ አድርጎ እየሰራበት ነው። ከአሸባሪው ተዋጊ አባላት ባልተናነሰ በኋላው ለዘረፋ በአደረጃጀትና በዕዝ የትግራይ ሴቶችንና አዛውንቶችን አሰልፏል። ታሪክ ይቅር ሊለው በማይችልበት ሁኔታ ከ70 ዓመት በታች ያለ የትግሬ ተወላጅ የወረራውና የዘረፋው ተሳታፊ እንዲሆን አደረጃጀት ተፈጥሯል፤ ስምሪትም ተሰጥቷል። “… ሂዱ አማራንና አፋርን እንዲሁም ቀሪዉን የኢትዮጵየሠ ህዝብ ውረሩ፣ ሀብት ንብረቱንም ዝረፉ ኢትዮጵያንም አፍርሱ…” የሚል መመሪያ ከአሸባሪውና ወራሪው ትህነግ የወረደለት ኃይል፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራንና አፋርን ክልሎች እንደአንበጣ በመውረር ላይ ነው። ይህ አደገኛ ተስፋፊ ኃይል እንደሕዝብ ካልተመከተ የጥፋት አድማሱን በማስፋት ኢትዮጵያን ወደ ታሪክ ሊቀይራት እንደሚችል ሕዝባችን ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል።

አሸባሪው አባላቱን ሲመለምል የተጣባውን ክፉ የአማራ ጥላቻ ትርክት ከመስበክ በተጨማሪ የአማራንና የሌላውን ኢትዮጵያዊ ሀብት ዘርፈው ጥሪት ይዘው እንደሚመለሱ በማሳመን ጭምር ስለመሆኑ ምርኮኞች ላይ ባደረግነው ምርመራ ደርሰንበታል። ይህ ኃይል የወረራ አላማው ሕዝብን እንደ ሕዝብ ማጥፋትን ዒላማ ያደረገ ነው። ከጭፍጨፋ የተረፈው ሕዝብ በድህነት ቀንበር እንዲኖር የጥላቻ ጥግ የሆነ እቅዱን አስቀምጦ የመጣ በመሆኑ እንደሕዝብ ተነስተን ካልመከትነው በቀጣይ በአማራውና ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ለመገመት ይከብዳል።

ስለሆነም አለም በቃኝ ያሉ አባቶች የሚኖሩባቸውን ገዳማት ጨምሮ ቤተ እምነቶችን ዘርፎ፣ ቀሪውን የሚያወድም ይህ አሸባሪ ኃይል ትውልድን ገድሎ፣ የአማራ ክልልና የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥረቱ ያፈራውን ሀብት ዘርፎ ለመበቀል የያዘውን የዘረፋና የጭፍጨፋ አላማ በአጭሩ መቅጨት ያስፈልጋል። ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ በባርነትና በድህነት እንዲኖር አቅዶ የመጣን ክፉ ጠላት እንደሕዝብ ተረባርቦ ማስቆም ታሪካዊ ግዴታችን ነው።

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!
ክተት መክት ለፍትሕ ለነጻነት

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የሬዲዮ ግንኙነቱ ተቋርጧል።የስልክ መስመሮች ድምፅ አልባ ሆነዋል …
Jeffrey Filtman’s appointment as a Special Envoy is to escalate pressure on Ethiopia
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2