Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በነጭ ፕሮፓጋንዳ የሚፈርስ ሀገር የለም! የገባንበት ጦርነት የህልውና ጦርነት ነው!
News

በነጭ ፕሮፓጋንዳ የሚፈርስ ሀገር የለም! የገባንበት ጦርነት የህልውና ጦርነት ነው!

Ethioreview newsEthioreview news—November 4, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያ የማዳን ጥሪን ተከትሎ እየተመመ ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ተጋድሎ የጥፋት ኃይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ያላትን ዝግጁነትና ተግባር የሚያመለክት ነው፡፡ በቅርቡ በፌደራልና የክልል መንግስት አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ ለመላው ኢትዮጵያውን ለቀረበው ጥሪ መላው ህዝባችን በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ያሳየው ምላሽና ተነሳሽነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው፡፡

ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ኢትዮጵያውያን ተቆጥተው በሁሉም አቅጣጫ በተደራጀ አግባብ ወደ ጦር ግንባር እየተመሙ ይገኛሉ፡፡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በማሸነፍ ወኔ፣ ሥነ-ልቦና፣ ጀግነትና ቁጭት ግንባሩን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡ የበረሃ አንበሶቹ የአፋር ልዩ ኃይልና አይበገሬዎቹ የአፋር ወጣቶች ወደ ክልላቸው ለመስፋፋት ያሰፈሰፈውን ኃይል ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጋር ህብር ፈጥረው ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሽንፈት እንዲከናነቡ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጠላት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ጉዳይ አስፈፃሚ አድርጎ ያስቀመጣቸው አመራሮች ላይ ህዝቡ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በሁሉም ግንባሮች ጠላትን ለመቅበር ህዝቡና የወገን ጦር አንድነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የአሸባሪው ቡድን ትሕነግና ፍልፍሎቹ አለን የሚሉትን ኃይል በማሰባሰብ በወገን ጥምር ጦር ከበባ ውስጥ እየገቡ ናቸው፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎና በወገን ኃይል ከፍተኛ ንቃትና መነሳሳት ተፈጥሯል፡፡ አይጥ ከጉድጓዷ እየራቀች በሄደች ቁጥር መሞቻዋ ነው እንደሚባለው የጠላት ግብዓተ መሬት ተቃርቧል፡፡

የጥፋት ኃይሉ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት የዘር ማጥፋት በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል፣ የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ረሀብ እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቀሟል፣ አስገድዶ መድፈርን የትግራይን ህዝብ ለመቅጫነት የኢትዮጵያ መንግስት ተጠቅሟል ወዘተ እያለ ሲጠቀምባቸው የነበሩ አሰልቺ ስብከቶቹ በዓለም አቀፍ ገለልተኛ ተቋም በተደረገው የእውነት ማፈላለግ ስራ እነዚህ ጉዳዮች በኢትዮጵያ መንግስት እንዳልተፈፀሙ ተረጋግጧል፡፡

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

በቁጣ የተነሳሳው የህዝብ ማዕበል ያስበረገገው የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የመጨረሻ ያሉትን የሽብር ወሬ በማሰራጨት ተጠምደዋል፡፡ ቁልፍ ኢላማቸው አድርገው የወሰዱት ደግሞ በአመራሩ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር፣ ፍርሃት እንዲነግስ የማሸበር ስራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት እንዲባባስ አበክረው የሚሰሩ እንደ ፌስቡክ አይነት የማህበራዊ ሚዲያዎች የጠቅላይ ሚኒስትራችንን መዕልክቶች ከገፁ በመሰረዝ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

እንደ ሮይተርስ ያሉት ደግሞ በጠላት ያልተያዙ አካባቢዎችን እንደተያዙ በማስመሰል የተሳሳተ መረጃ እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡ በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ነው፡፡ ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

መንግስት በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ ያስጠነቅቃል፡፡ መላው ህዝባችን ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የምንገኝ መሆኑን ተገንዝቦ የጀመረውን ሀገር የማዳን ንቅናቄ አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ዋስትናችን ህልውናችንን በአንድነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት በአፍራሽ ኃይሎችና ግብር አበሮቻቸው በኩል የሚነዙ የውሸትና መርዛማ ወሬዎቻቸው የሚመጡበት መንገድ በመዝጋት በአንድነት የመነሳቱን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

የኢትዮጵያውያንና የወዳጅ ሀገር ሚዲያዎች ለህብረተሰባችን ትክክለኛውን መረጃ በወቅትና በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡ መንግስት ይጠይቃል፡፡ በጊዜያዊ ድሎች መወራጨት የጀመሩትን የጥፋት ኃይሎች የማይናወጥ ዘላለማዊ ድሎችን በማስመዝገብ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ያለብን አሁን ነውና ሁላችንም በአንድነት እንቁም፡፡ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የታቀደልንና የተደገሰለንን ድግስ በጋራ በጣምራ ክንዳችን እንወጣዋለን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ለሉአላዊነታችን፣ ለአንድነታችን እና ለማንነታችን ሞት ክብራችን ነው! ከመሥዋዕትነት ውጪ ኢትዮጵያዊነት የለም!!

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

_ አካባቢህን ጠብቅ
_ ወደ ግንባር ዝመት
_ መከላከያን ደግፍ


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢትዮጵያን በፕሮፓጋንዳ ለማተራመስ እጅግ የተቀናጀ ዘመቻ ተጀምሯል
በሶማሌ ክልል ከፍተኛ ወንጀል ከሚፈለጉት አንዱ የትህነግ ሰራዊት መሪ ተማረከ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2