“ነጻ በወጡ አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ ነው” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎ
ከአሸባሪው ህወሃት ነጻ በወጡ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በሰጡት መግለጫ “የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር ባከናወኑት ምርመራ ውጤትና ምክረ ሃሳብ መሰረት መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል” ብለዋል።
መልሶ ግንባታና አገልግሎቶችን ከማስጀምር ጎን ለጎን በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል።
“በወራራ ተይዘው በነበሩ አካባቢዎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመረምር የወንጀል ምርመራና የማስቀጣት ቡድን በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል ተቋቁሞ የምርመራ ስራው ተጀምሯል” ብለዋል።
“የምርመራ ቡድኖቹ በአሸባሪው ትህነግ ተይዘው በነበሩ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የደረሱትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎችን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት በሚያስችል መልኩ ቅኝት ለማድረግ ተሰማርተዋል” ነው ያሉት።
በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ የንጹሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋትን፣ የአካል መጉደልን፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን፣ ከቤት ንብረት መፈናቀልን፣ የንብረት ውድመትን፣የመንግስታዊ ተቋማት ሰነዶች ውድመት እና ሌሎች እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎችን ለማጣራት እነዚህ የመርማሪ ቡድኖች ተሰማርተዋልም ሲሉ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል መርማሪ ቡድን መሰማራቱንና በስሩ ሁለት ንዑሳን ቡድኖችን ይዞ ምርመራ እያከናወኑ ይገኛል ያሉት ሚኒስተር ዴኤታዋ “በአማራ ክልል ደግሞ በርካታ ቡድኖች መሰማራታቸውን አንስተው ሸዋሮቢትን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአስር ወረዳዎች፣ በደቡብ ወሎ ስምንት ወረዳዎች፣ የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች፣ በደሴና ኮምቦልቻ፣ ጋሸናን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ምርመራና ምልከታዎችን ለማድረግ ቡድኖቹ ተሰማርተዋል” ብለዋል።
ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ ቡድኖቹ ወደ ዋግኽምራ አካባቢዎችና ወደ ወልድያ መሰማራታቸውንም አንስተዋል።
ምርመራዎቹና ምልከታዎቹ የሚካሄዱት በአሸባሪው ትህነግ የተካሄዱትን ጥፋቶች በተጨባጭና በሁለንተናዊ መልኩ ማሳየት በሚችሉበት ደረጃ እንደሆነም አስታውቀዋል። via (አሚኮ)
- አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱበዙፋን ኡርጋ ደራሲነት የተጻፈውን ሌንጮ ለታ ትግል ሕይወቱ መጽሐፍን አነበብኩት።… Read more: አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
- የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?ቪኦኢ ዜና – በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ ካርታ… Read more: የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?
- ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደርበኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
- Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises In a sudden change, Iran has reportedly once again closed… Read more: Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises


