በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ላልይበላ ጠቅላላ ሆስፒታል በከተማዋ ለአራት ወራት ያህል ከርሞ የነበረውን የሽብር ቡድኑን የጭካኔ በትር ተጋፍጦ አገልግሎቱ ሲሰጥ መቆየቱን የሆስፒታሉ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።
ግፈኛውና አሸባሪው ቡድን የሆስፒታሉን ባለሙያዎች ከመደብደብ አልፎ የሆስፒታሉን ቁሳቁስ በመዝረፍ እና በመሰባበር የክፋቱን ጥግ አሳይቷል ብለዋል።

ሆስፒታሉን በተወካይ ሥራ አስኪያጅነት እየመሩ የሚገኙት ባዮ ሜዲካል ኢንጂነር ሲሳይ ታመነ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ሆስፒታሉ በአካባቢው ላሉ 300 ሺ የኅብረተሰብ ክፍል አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ወራሪው ኃይል ወደ ላልይበላ ከተማ ከገባ ጀምሮ ለአንድ ሁለት ቀን ያህል ሥራ አቋርጦ የነበረ ቢሆንም ወዲያው ኮሚቴ ተዋቅሮ የሽብር ቡድኑን የግፍ በትር በመቋቋም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወደሥራ ገብቷል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ፣ ለጊዜው የተወሰኑ ዲፓርትመንቶችን በማጠፍ በተለይ ወላጆችንና ስር የሰደደ (ክሮኒክ) ችግር ያለባቸውን ህሙማን አሸባሪው ኃይል የሚያደርሰውን ፈተና በመጋፈጥ ሲያገለግሉ መቆየታውን ተወካይ ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
እርሳቸው እንዳሉት፤ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መንገድ ላይ እየተደበደቡም ቢሆን ወራሪው ኃይል ከተማውን ተቆጣጥሮት በቆየባቸው በአራት ወር ውስጥ ወደ 34 እናቶች በኦፕራሲዮን እንዲወልዱ ማድረግ ችለዋል። ከአምስት ሺ በላይ የሆኑ ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ተስተናግደዋል። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ስራውን ሳያቋርጥ ቆይቷል።
በወራሪው ኃይል ተደፍረው ከመጡ ሴቶች መካከል ሁለት ታካሚዎች ሲሆኑ፣ አንዷ እመጫት መሆኗን የተናገሩት ተወካዩ፣ በኑሮ ደረጃዋም ዝቅተኛ ከሚባሉት መካከል የምትመደብ መሆኗ ተናግረዋል። ተደፍረው የመጡ ሴቶች በተገቢው መንገድ አገልግሎት እንደተሰጣቸውም አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አቤኔዘር ፈንቴ በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ በከባድ ፈተና ውስጥ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ነው ብለዋል። በተለይ የሆስፒታሉ የፋርማሲ ባለሙያዎች ይደበደቡ እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የወራሪውን ዱላ ሳይፈሩ ተቋቁመው አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ኮሚቴ ሰብሳቢው ገለጻ፤ አንዲት እናት ልትወልድ ወደሆስፒታሉ መጥታ እርሷን ለማዋለድ በሚደረገው ሂደት ለጄኔሬተር ናፍጣ መጠቀም እየተፈለገ ወራሪው ኃይል ግን ናፍጣውን በጉልበት ይወስድ ነበር። ከሆስፒታሉ አውቶቡሶች ውስጥ ሁሉ ናፍጣውን በቱቦ እየሳበ ይጠቀም ነበር።
ሆስፒታሉ ከዚህ በኋላ በርካታ ወረዳዎችን የሚያገለግል እንደመሆኑ የክልል ጤና ቢሮ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አቶ አቤኔዘር ጥሪ አስተላልፈዋል። ሆስፒታሉ በመከራ ውስጥ ሆኖ አገልግሎት ሲሰራ በተመቻቸ ሁኔታ አለመሆኑም መታወቅ አለበት ብለዋል።
በሆስፒታሉ የሐብት አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መለሰ አሰፋ በበኩላቸው፤ ወራሪው ኃይል ሆስፒታሉን ካምፕ አድርጎ መክረሙን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ለአንድ ሁለት ቀን አገልግሎት መስጠት ያቆመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ ምንም አይነት መድኃኒት እንዳልነበር ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ የላስታ ላልይበላ ተወላጆች አስቸኳይ እርዳታ በማቋቋም መድኃኒት ተገዝቶ ከዞኑ መቄት ከሚባል ወረዳ ከፍላቂት ከተማ መድኃኒት ተገዝቶ በአህያ ተጭኖ መምጣቱን አስታውሰዋል።
በዚህ መሃል ግን ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ይሞቱ እንደነበር አስታውሰዋል። የቅዱስ ላልይበላ ሆስፒታል ክፍት ነው በሚልም ከወልዲያ፣ ከቆቦና ላስታ ድረስ ሰዎች መጥተው ይታከሙ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ መለስ፣ እንዳሉት፣ በወቅቱ ወደ13 የስራ ክፍሎች በወራሪው ኃይል ተሰባብረዋል። ማህበረሰቡን ሲያገለግሉ የነበረው የጥገና ስራ በማካሄድ ነው። በርካታ የሆስፒታሉ እቃዎች በሽብር ቡድኑ አባላት ተሰርቀዋል። በተለይ የህክምና አላቂና ቋሚ እቃዎች ተወስደዋል።
አስቴር ኤልያስ አዲስ ዘመን ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር።… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
- የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?ቪኦኢ ዜና – በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ ካርታ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል… Read more: የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?
- ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደርበኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
- Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises In a sudden change, Iran has reportedly once again closed off the Strait of… Read more: Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises
- Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump callTurkish President Recep Tayyip Erdogan welcomed the two-week truce with Iran, pledging Türkiye’s continued… Read more: Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call
- እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ በኢትዮጵያ ምድር እየኖሩ የኤርዶኻን መልእክተኛ ለመሆን… Read more: እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…
- የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙየአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር Dr. Annette Weber ለኤርትራ መሪዎች… Read more: የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ

