Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035 ምን ይዞ መጣ?
News

የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035 ምን ይዞ መጣ?

Ethioreview newsEthioreview news—December 5, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ቻይና ለአፍሪካ 600 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት በነጻ እንደምትሰጥ ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ቃል ገብተዋል። ፕሬዝደንቱ ይፋ ባደረጉት የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035 የመጀመሪያ ሶስት አመታት የአፍሪካን የወጪ ንግድ ለማገዝ፣ የድሕነት ቅነሳና የግብርና ልማት መርሐ-ግብር ለማከናወንና ቻይና ከአፍሪካ የምትሸምተውን ሸቀጥ ለማሳደግ ቃል ገብተዋ

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዋንግ ይ ወደ አዲስ አበባ ከማቅናታቸው በፊት ትናንት ማክሰኞ በዳካር በሰጡት መግለጫ ቻይና እና አፍሪካ በግንኙነቶቻቸው ረገድ ጠቃሚ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም (FOCAC) ሲጠናቀቅ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ከሴኔጋሉ አቻቸው አይሳታ ታል ሳል ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ “ዓለም አቀፉ ነባራዊ ሁኔታ የቱንም ያክል ቢቀየር እና ቻይና እና አፍሪካ ምንም አይነት ፈተናዎች እና እንቅፋቶች ቢገጥሟቸው ሁለቱ ወገኖች ፖለቲካዊ መተማመን ለማጠናከር እና ተግባራዊ ትብብርን ጥልቅ ለማድረግ ቁርጠኛ ሆነው ለመዝለቅ መስማማታቸውን” ገልጸዋል።

ቻይና እና 53 የአፍሪካ አገራት የተሳተፉበት እና ከሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር አቅራቢያ በምትገኘው ዲያምኒያዲዮ የተካሔደው ይኸው ስብሰባ በርከት ባሉ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነበር። የቻይና አፍሪካ አማካሪ ተቋም መሥራች እና ዳይሬክተር አቶ አሌክሳንደር ደምሴ “ስምንተኛው ዙር ስብሰባ የቻይና እና የአፍሪካ አገሮች ግንኙነት እየበሰለ እየመጣ እንደሆነ የሚያሳይ” እንደሆነ ይናገራሉ። “ቻይና ከዚህ በፊት የ3 አመት ዕቅድ ብቻ ነበር ይዛ የምትንቀሳቀሰው። አሁን ግን የአስር አመት ዕቅድ ይዛ መጥታለች” የሚሉት አቶ አሌክሳንደር የሴኔጋሉ ስብሰባ “ስኬታማ ነበር” የሚል ዕምነት አድሮባቸዋል።

የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035 ምን ይዞ መጣ?

More stories

የፋይናንስ ደኅንነት ከሕገ ወጥ ምንዛሬ ጋር በተያያዘ የ138 ተጠረጣሪዎች የባንክ ሂሳብ አገደ

August 9, 2025

ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ሀሰተኛ ግብይት መፈጸሙ ተገለጸ

December 6, 2021

«የኢትዮጵያ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ለውጥ ባያገኝ ኖሮ ሀገሪቱ ወዳልተፈለገ ሁኔታ የምትሄድበት አጋጣሚ ይፈጠር ነበር» ዶክተር ነመራ ገበየሁ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

April 7, 2021

የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ጸደቀ፤ የኑሮ ውድነት በማሻሻያው ላይ ሰፊ ክርክር አስነስቷል፤ ግብር ካልተሰበሰበስ?

July 18, 2025

የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም የምኒስትሮች ስብሰባ ባለፈው ሰኞ ሲጀመር ንግግር ያደረጉት የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ 65 አመታት ላስቆጠረው የቻይና እና የአፍሪካ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አዲስ መንገድ መቀየዱን ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዝደንቱ የሴኔጋሉ ስብሰባ ከመካሔዱ በፊት ሁለቱ ወገኖች ለግንኙነታቸው “የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035” የተባለ ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በዕቅዱ የመጀመሪያ ሶስት አመታት ቻይና በአፍሪካ ልታከናውን ያቀደቻቸውን ዘጠኝ ሥራዎች ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ በንግግራቸው ዘርዝረው አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ እንዳሉት ከዘጠኙ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀዳሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ጉዳይን የተመለከተው የሕክምና እና የጤና መርሐ-ግብር ነው።

ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ “የአፍሪካ ኅብረት [በጎርጎሮሳዊው] 2022 ከአኅጉሩ ሕዝብ 60 በመቶውን ለመከተብ የያዘው ዕቅድ እንዲያሳካ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለአፍሪካ እናቀርባለን። ከዚህ ውስጥ 600 ሚሊዮን ክትባት በነጻ፤ የተቀረው 400 ሚሊዮን ክትባት ደግሞ የቻይና ኢንርፕራይዞች ከሚመለከታቸው የአፍሪካ አገራት ጋር በጥምረት እንዲያመርቱ በማድረግ የሚቀርብ ይሆናል” ሲሉ ተናግረዋል።

በመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት ተግባራዊ በሚሆነው በዚሁ ዕቅድ “የአፍሪካ አገሮች አስር የሕክምና እና የጤና አጠባበቅ ፕሮጀክቶችን እንዲያከናውኑ ቻይና ዕገዛ ታደርጋለች። ከዚህ በተጨማሪ 1,500 የሕክምና እና የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎችን ወደ አፍሪካ ትልካለች” በማለት አብራርተዋል።  

ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ በንግግራቸው ይፋ ያደረጉት ሁለተኛ መርሐ-ግብር የድሕነት ቅነሳ እና የግብርና ልማት ነው። በዚህ መርሐ-ግብር ቻይና አስር የድሕነት ቅነሳ እና የግብርና ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ለመከወን መዘጋጀቷን ሺ ዢንፒንግ ተናግረዋል። ፕሬዝደንቱ እንዳሉት አገራቸው 500 የግብርና ባለሙያዎችን ወደ አፍሪካ ትልካለች። ዕቅዱ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ማዕከላት፣ ማሰልጠኛዎች እና ሰርቶ ማሳያዎች መገንባትን ያካተተ ነው።

በንግድ ማስፋፊያ ረገድ በተወጠነው ዕቅድ የአፍሪካ የግብርና ውጤቶች ለቻይና ገበያ የሚቀርቡበትን መንገድ የሚያፋጥን እና የሚያቀላጥፍ ሥርዓት ለመዘርጋት የፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ መንግሥት አቅዷል። የአፍሪካን የወጪ ንግድ ለማገዝ ቻይና 10 ቢሊዮን ዶላር እንደምታቀርብ ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል። ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሺየቲቭ በተባለው የቻይና ዕቅድ ላይ በሚመረኮዘው መርሐ-ግብር አገራቸው የአፍሪካ አገሮችን እርስ በርስ የሚያገናኙ አስር የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች ለማከናወን እና ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ጽህፈት ቤት ጋር የኤኮኖሚ ትብብር የሚያበጅ የባለሙያዎች ቡድን ለማቋቋም ሺ ዢንፒንግ ቃል ገብተዋል።

አራተኛው ዕቅድ በሶስቱ አመታት የቻይና ኩባንያዎች ከ10 ቢሊዮን ዶላር በማያንስ መዋዕለ-ንዋይ በአፍሪካ እንዲሰማሩ ለማበረታታት እና የቻይና አፍሪካ የግል መዋዕለ ንዋይ መድረክ ለማቋቋም የተወጠነ ነው። ቻይና አስር የኢንዱስትሪ ማስፋፊያ እና የሥራ ፈጠራ ፕሮጀክቶችን በአፍሪካ እንደምታከናውን የተናገሩት ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ የአኅጉሪቱን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለመደገፍ ለአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደምታቀርብ ቃል ገብተዋል። ቻይና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ካላት የመበደር አቅም አስር ቢሊዮን ዶላሩን ለአፍሪካ አገራት ለማስተላለፍ ዝግጁ መሆኗን ሺ ገልጸዋል።

የቻይና አፍሪካ አማካሪ ተቋም ዳይሬክተር አቶ አሌክሳንደር ደምሴ “የአፍሪካ አገሮች ራሳቸው የራሳቸውን ምርቶች ወደ ቻይና እንዲልኩ ይፈለጋል። [በጎርጎሮሳዊው] እስከ 2024 ዓ.ም. ድረስ እስከ 300 ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካን ቁሳቁሶች ከአፍሪካ አገሮች ቻይና መሸመት ትፈልጋለች። ይኸ ትልቅ ዕድል እየፈጠረ ነው” ሲሉ ይናገራሉ። “እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች፤ ሌሎች ትልልቅ የግብርና አምራች አገሮች በዚህ በጣም ሊጠቀሙ ይችላሉ” ሲሉ አቶ አሌክሳንደር አብራርተዋል።

Infografik Chinesische Direktinvestitionen (FDI) in Afrika EN

በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ተግባራዊ ከሚደረጉ የቻይና አፍሪካ ትብብር ርዕይ 2035 ውጥኖች መካከል ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ እንዳሉት በአፍሪካ አስር የዲጂታል ኤኮኖሚ ፕሮጀክቶች መገንባት፤ በሳተላይት እና በኤሌክትሮኒክ ግብይት ዘርፎች ትብብሮችን ማጠናከር ይገኙበታል።

ቻይና በሚቀጥሉት ሶስት አመታት አስር የአረንጓዴ ልማት እና የከባቢ አየር ጥበቃ ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ለማከናወን፤ አስር ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እና ለማደስ፣ 10,000 የአፍሪካ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና ስብሰባዎች ለመጋበዝ ፕሬዝዳንቱ ቃል ገብተዋል። የቻይና እና የአፍሪካን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ቃል የገቡት ፕሬዝደንቱ በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ ጭምር ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት መኖሩን ጠቁመዋል።

ቻይና እና የአፍሪካ አገሮች የዕዳ ጫና ሥጋት

ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ በስብሰባው ይፋ ያደረጓቸው ዘርፈ ብዙ ዕቅዶች የዓለምን ትኩረት የመሳባቸውን ያክል ቻይና ከአፍሪካ ባላት ግንኙነት ተጠቃሚው ማነው? የሚለው ሙግት ላለፉት ጥቂት አመታት በርትቶ ታይቷል። ቻይና ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በአፍሪካ ያከናወነችው መዋዕለ-ንዋይ እና ለአገራቱ የሰጠችውን ብድር ፍላጎቷን ለማስፈጸም ተጠቅማበታለች የሚል ክስ ይደመጣል። በጀርመን ላይፕዚግ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ኤኮኖሚ እና የአፍሪካ ጥናት ፕሮፌሰሩ ሔልሙት አሼ ግን “ይሁነኝ ተብሎ የታቀደ ፖሊሲ መሆኑን እጠራጠራለሁ። ቻይና የአፍሪካ አገሮች በዕዳ ወጥመድ ውስጥ ሲወድቁ የማየት ፍላጎት የላትም። ችግሩ የአፍሪካ አገሮች ከቻይና ከተበደሩት ግማሹ ድብቅ ዕዳ ነው። ድብቅ ዕዳ ማለት የአከፋፈል ውሉ እና ሒደቱ አይታወቅም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

በአሜሪካው የጆን ኾፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የቻይና አፍሪካ ጥናት ተቋም ባለፈው መስከረም ይፋ ያደረገው አንድ ሰነድ ዛምቢያ ከቻይና መንግሥት እና የግል ተቋማት 6.6 ቢሊዮን ዶላር መበደሯን ይፋ አድርጓል። ይኸ የቀደመው የዛምቢያ መንግሥት ይፋ ካደረገው በእጥፍ ገደማ ከፍ ያለ ነው። እንዲህ አይነቱ የግልጽነት እጦት ቻይናን ለትችት እና ጥርጣሬ አጋልጧታል። የቻይና አፍሪካ አማካሪ ተቋም ዳይሬክተር አቶ አሌክሳንደር ደምሴ የአፍሪካ አገሮች ከሩቅ ምሥራቅ ወዳጃቸው ባላቸው ግንኙነት በቅጡ ለመጠቀም ብልኅ ሊሆኑ እንደሚገባ ያምናሉ። 

“አንዳንድ አገሮች የተሻለ አቅም አላቸው። የተሻለ ግንዛቤም ይዘው እየመጡ ነው” የሚሉት አቶ አሌክሳንደር ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ግብጽ ከወደ ቻይና የመጣውን ዕድል አጠቃቀም ካወቁበት ጎራ ይመድቧቸዋል። “ብዙ የአፍሪካ አገሮች የበለጠ ሥራ መሥራት አለባቸው። አንድ ስብሰባ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሌት ተቀን መሥራት ግድ ይላል” ሲሉ አቶ አሌክሳንደር ያስረዳሉ። 

የቻይና ዕዳ ከተጫናቸው የአፍሪካ አገሮች መካከል ከቤጂንግ በወሰደችው ብድር የባቡር መጓጓዣዎች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የስኳር ፋብሪካዎች እና የተለያዩ ማምረቻዎችን ጨምሮ ግዙፍ መሠረተ-ልማቶች ስትገነባ የቆየችው ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። አገሪቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ ከቻይና የተበደረችውን ገንዘብ መክፈል ቸግሯታል። በአሜሪካው የጆን ኾፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የቻይና አፍሪካ ጥናት ተቋም ሰነድ እንደሚያሳየው ከጎርጎሮሳዊው 2000 እስከ 2018 ዓ.ም. ባሉት አመታት ቻይና ለአፍሪካ አገሮች ከሰጠችው 148 ቢሊዮን ዶላር ብድር 13.7 ቢሊዮን ዶላር የኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ ከወደ ቻይና የተበደረችው የገንዘብ መጠን በቡድን 20 አገራት በኩል የጀመረችውን የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ሊያወሳስብ እንደሚችል ባለሙያዎች ሥጋት አላቸው። 

እሸቴ በቀለ ነጋሽ መሐመድ DW

ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አፕል “ስልክህን ራስህ” ጠግን አለ
አሸባሪው ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2