Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ባለሀብቶች ብድር ከመስጠት አንስቶ ሌሎችም ድጋፎች እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

    February 9, 20220

    ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች የሞት ቅጣት ተወሰነባቸው

    October 21, 20240

    የአማራ ክልል ከትግራይ ጋር ሁሉንም ጉዳይ በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

    March 31, 20230

    Sudan official: ‘Mediation between Khartoum and Addis Ababa faces obstacles’

    February 14, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    መላው አማራ ከነገ ጀምሮ ለህልውና ዘመቻ እንዲነሳ ክተት ተጠራ

    July 25, 20210

    የጆ.ባይደን አስተዳደር የሰላም አማራጭ ንግግሩን ቀድሞ የትህነግን ፍላጎት አቋም አድርጎ አቀረበ

    November 1, 20220

    በሽረ አዲስ ተስፋ፤ ሕዝብ በነጻነት ስለቀጣዩ ዕጣው አየመከረ ነው

    December 26, 20220

    እውነትን ለሥልጣን መናገር ፣ ሳማንታ ፖወር ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

    March 1, 20210

    በአዲስ አበባ ከ27ሺህ በላይ ወጣቶች ተደራጅተው ከተማዋን እየጠበቁ ነው

    November 11, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  አብይ አሕመድ የሰላም መርሆዎችን አመላከቱ፤ በሰላም ሂደቱ ፍትህ እንደማይዛነፍ ግልጽ አደረጉ
News

አብይ አሕመድ የሰላም መርሆዎችን አመላከቱ፤ በሰላም ሂደቱ ፍትህ እንደማይዛነፍ ግልጽ አደረጉ

Ethioreview newsEthioreview news—January 7, 20220
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከድል በሁዋላ በመጪው ጊዜ በሁሉን አቀፍ የፍትህ ሽግግርና በተሃዶስ ፍትሃዊ እይታ፣ አገራዊ ባህልና እሴቶችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ያጠፉ እንዲቀጡ፣ የተበደሉ እንዲካሱ በሚያድርግ አግባብ ፍትህ ለማስፈን እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ግልጽ አደረጉ። ለሕዝብ በቀጥታ ለማሳወቅ፣ መረጃው ሳይኖራቸው ወይም “መሆን አለበት” ሲሉ የፍትህ ሽግግር እንዲደረግ ሲጠይቁና ሲተቹ ለነበሩ ምላሽ ይሆን ይሆን ዘንድ ፍትህ እንደማይዛነፍና በተለያዩ አግባቦች እንደሚተገበር መልስ ግልጽ አድርገዋል።

በመላው አገሪቱ የሰላም መድረክ እንዲካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በአሁን ሰዓት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት በግል የማህበራዊ ገጻቸው “ጀግና ሕዝብ – በቀኝ እጁ ድልን የሚጨብጥ፣ በግራ እጁ ይቅርታና ምህረትን የሚቸር ነው!” በሚል ዕርዕስ ባሰራጩት ጽሁፍ ነው።

የነገሮች አጨራረስና አወቃቀር ውበትን ለማሳየት የመኖሪያ ቤትን ግንባታና የነተላን ቁጭት አንስተው ያስረዱትና ሁሉም መዕራፎች በራሳቸው አግባብ ሊቁጩ እንደሚገባ ያመለከቱት አብይ አሕመድ፣ ምንም ይሁን ምን አራት መርሆችን መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር እንደሚገባ አመልክተዋል። አራቱ መርሆችም አንዱ ሌላውን ሳይተካ ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንደ አስፈላጊነታቸው ሁሉም የሚተገበሩ እንደሆነ አመልክተዋል። መልኩ ይተለያየ ቢሆንም ፍትህ እንደምያታጠፍ አመልክተዋል።

ሳይጓደሉና አንዱ አንዱን ስይነካ ” ከድል ማግስት ሊፈጸሙ ይገባል” ሲሉ ያስቀመጡዋቸው አራቱ መርሆች

More stories

ለመንግስት ሁሉ አቀፍ የሰላም አሳብ ቀረበለት፤ የእርቅ ኮሚሽን በመጪው ዓመት ህገ መንግስት እስከመቀየር የሚያደርሰውን ስራ ይጀምራል

September 6, 2023

አንድ መቶ አስራ አንድ አገሪቱን በብሄርና በሃይማኖት የሚንጡ ህገወጥ ድረ ገጾች ተለዩ፤ አስሩ ተያዙ

June 1, 2022

ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን ሊተካ የሚችል የማህበራዊ ትስስር ገጽ ስራ ላይ ልታውል ነው

August 21, 2021

ኢትዮጵያ አንደ አገር ገናና በነበረችበት ዘመን አሜሪካ አትታወቅም ነበር

October 17, 2022

1ኛ – ድላችንን እንዳይቀለበስ አድርገን በሁለንተናዊ መስክ እናጠብቀዋለን።

2ኛ – ድላችን ዘላቂ እንዲሆን በፖለቲካዊና ሰላማዊ መንገዶች እንዲቋጭ እናደርገዋለን።

3ኛ – ድላችንን ለመጠበቅና ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምሕረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን።

4ኛ – ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግግር እና በተሃድሶ ፍትህ እይታ፣ ሃገራዊ ባህሎቻችን እና አሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን። እነዚህ አራቱ መርሖች አንዱ ሌላውን ሳይተካ ሁላችንንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንደ አስፈላጊነታቸው ሁሉንም እንተገብራለን። ሙሉ መልዕክታቸው ከዚህ በታች ቀርቧል።

“ጀግና ሕዝብ – በቀኝ እጁ ድልን የሚጨብጥ፣ በግራ እጁ ይቅርታና ምህረትን የሚቸር ነው!” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ማንኛውም ጉዞ በስኬት ተቋጨ የሚባለው አንድም በየምእራፉ፣ ሁለትም የጉዞው መጨረሻ በስኬት መጠናቀቅ ሲችል ነው። አጠቃላይ ጉዞው ያማረና የሠመረ እንዲሆን እያንዳንዱ ምእራፍ በሚገባ መቋጨት አለበት። የቤቱ ጥንካሬና ውበት የሚመሠረተው ቤቱን ከገነቡት እያንዳንዱ ጡብዎች ጥንካሬና ውበት እንጂ፣ በጣራው ጥንካሬና በግድግዳ ቀለም ብቻ አይደለም። በያንዳንዱ እርከን ውበቱና ጥንካሬው እየተረጋገጠ የመጣ ቤትም፣ በግንባታው መጨረሻ – በድምድማቱ አምሮና ጠንክሮ መቋጨት አለበት። እንዲያ ሲሆን ቤቱ – እድሜው ረጅም፣ ሲኖሩበት የሚያምር ይሆናል። በሀገራችን ባህል የጋቢ ወይም የነጠላ መጨረሻው መቋጨት ነው። ያልተቋጨ ነጠላ ወይም ጋቢ የመተርተር ዕድሉ ሰፊ ነው።

የሀገራችን ጉዞ በተደጋጋሚ ከሚገጥመው ፈተና አንዱ በተገቢ መንገድ ምእራፎቹንም ሆነ ፍጻሜውን ያለመቋጨት ነው። በዚህ የተነሣም በሂደቱ የተገኙ ድሎች በየምእራፉ ሲዝረከረኩ ይገኛሉ፤ ወይም የታሰበላቸውን የፍጻሜ ውጤት ሳያመጡ ይቀራሉ። ማንኛውም ሀገራዊ ተግባር መለካት ያለበት በሂደቱና በውጤቱ ነው። ሂደቱም ውጤቱም ተገቢውን ደረጃ ጠብቀው ተገቢን ውጤት ማምጣት አለባቸው።

ሀገራዊ ለውጡን ከጀመርን ጊዜ አንስቶ “መንገዳችን መደመር፣ ግባችን ብልጽግና ነው” ብለናል። በመደመር መንገድ ተጉዘን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመድረስ ደግሞ ሰላም፣ ይቅርታና ፍቅር (ሰ.ይ.ፍ) ዋናዎቹ ዕሴቶቻችን መሆናቸውን ገልጠናል። ሀገራዊ ሰላምን ለማስፈን ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድን ብቻ መከተል፤ ያለፉ ቁርሾዎችን በይቅርታ መፍታት፤ የወደፊቱን መንገድ ደግሞ በሕዝቦች ፍቅር ላይ በመመሥረት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጽናት አለብን ማለታችን ነው። ከመነሻችን በዋና ዋና ልዩነቶቻችን ላይ ሀገራዊ ምክክር እናድርግ፤ ልዩነቶቻችን በውይይት እንጂ በጠብና በጦርነት አይፈቱም ስንል የነበረው በዚህ የጸና መርሐችን የተነሣ ነው።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍቅር ይልቅ ጠብና ጥላቻን በመረጡ፤ ከሰላም ይልቅ የጦርነትን መንገድ በተከተሉ፤ ከይቅርታ ይልቅ ነባር ቁርሾዎችን ለፖለቲካ ትግል መጠቀም በሚፈልጉ ኃይሎች ቀውስ ተፈጥሮብናል። ይሄም ቢሆን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሰላማዊውን መንገድ መርጠን ነበር። ነገር ግን እነዚህ ከጥላቻና ከጦርነት፣ ከጠብና ከመከፋፈል ውጭ ህልውና የሌላቸው አካላት ሰላማዊውን መንገድ አልመረጡም። የዘረጋናቸውን የሰላም እጆች ነክሰዋል። ከእኛ ይቅር በሚል መርህ ግማሽ መንገድ ስንቀርባቸው እጥፉን እየሸሹ፣ ልዩነቶች በሰላማዊ መፍትሔ ሊታረቁ ሲችሉ የጸብ መንደር ውስጥ ይዘውን ገብተዋል።

ሀገራችን ከአንድ ዓመት በላይ ከአሸባሪዎቹ ሕወሐትና ከጋሻ ጃግሬው ሸኔ ጋር ጦርነት የገባችው፣ የዘረጋነውን የሰላም እጅ ረግጠው ጦር ስለመዘዙብን ነው። መንግሥት የመጀመሪያ ምርጫው ምንጊዜም ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ ለመፍታት ነው። ሰላማዊ መንገድ አድካሚና አታካች ቢመስልም ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። ለጦርነት ሊውል የሚችለውን የሰው ኃይልና በጀትም ለብልጽግና ለማዋል ያስችላል። ዳሩ ግን ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚገኝ አልሆነም። የቱንም ያህል ብንታገስ፣ የቱንም ያህል ለሰላም ደፋ ቀና ብንል የጠላት ልብ ደነደነ እንጂ አልተለወጠም።

ማንኛውም የሰላም፣ የይቅርታና የፍቅር መንገድ ሊጥሳቸው የማይገቡ ቀይ መሥመሮች አሉ። ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚከፋፈል፣ የሀገራችንን ክብርና ሉዓላዊነት የሚጥስና የግዛት አንድነታችንን ለአደጋ የሚያጋልጥ ማንኛውንም መፍትሔ ተቀባይነት የለውም። የክህደትና የክፍፍል መንገድን የሚከጅል ሁሉ፣ የኢትዮጵያውያን ክንድ መቅመሱ አይቀርም። ከዚያ በታች ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ድሮም ልባችን ክፍት ነበር፤ ወደፊትም የሰላም እጃችን አይታጠፍም።

ከአሸባሪው ሕወሐትና ከተላላኪው ሸኔ ጋር ያደረግነው ጦርነት ቀይ መሥመሩ በመጣሱ ምክንያት የተከሠተ ነው። አሸባሪወው ሕወሐት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለመከፋፈል ተነሣ፤ የሀገራችንን ክብርና ሉዓላዊነት ከባዕዳን ጋር ሆኖ ለመግሠሥ ጦሩን ሰብቆ ሰሜን ዕዝን አጠቃ፤ የግዛት አንድነታችንን ለአደጋ እንዲጋለጥ በር ከፈተ። የቅርብና የሩቅ ጠላቶቻችንም እንደ ፈለጉት እጃችንን ሊጠመዝዙ ምክንያት አገኙ። በሀሰት ፕሮፓጋንዳቸውና ሴራ ባልተለየው የሚዲያ ዘመቻዎቻቸው ኢትዮጵያን በማዋከብ የፍላጎታቸው ተንበርካኪ ሊያደርጓት ሌት-ተቀን ይሮጡ ጀመር።

የጥንካሬና የኩራታችን ምንጭ የሆነው ሕዝባችን ግን በቀላሉ የሚበገር አልሆነም። በሀገር ውስጥ አሸባሪም ሆነ በውጭ ኃይሎች ሉአላዊነቱ ተነክቶበት ሕዝባችን እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ቀፎው እንደተነካ ንብ ‹ሆ› ብሎ በመነሳት በሁለት አቅጣጫ የተሰነዘረበትን ጥቃት በብቃት እየመከተ ይገኛል።

ጀግና ሕዝብ ለጭቆና መንበርከክን እንጂ ትህትናና ይቅርታን አይጠላም። አሸናፊ – ድል አጥባቂ፣ ትኁት እና መሐሪ ነው። ሕዝባችን “ውጊያ የሰው፣ ድል የፈጣሪ ነው” ብሎ ያምናል። አሁን ያገኘነውን ድል በሦስቱ የኢትዮጵያውያን የድል ዕሴቶች ብንቋጫቸው መልካም ነው። ድልን በማጥበቅ፣ በትኅትና እና በምሕረት። አሁን ያገኘነውን ድል እንዳይቀለበስ አድርገን በሁሉም መስክ በሩን ሁሉ ማጥበቅ አለብን። በኢትዮጵያዊ ትኅትና ደግሞ አሁን የገጠምነው ጦርነት በሰላም መንገድ እንዲጠናቀቅ እናደርጋለን። በአንድ በኩል ድል አድራጊውን የኢትዮጵያ ክንድ እያሳየን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ትኁቱን የኢትዮጵያውያን ልብ እናሳያለን። በድል አድራጊ የኢትዮጵያ ክንድ ጠላቶቻችን አፈር ልሰው እንዳይነሡ እንመክታለን። በትኁቱ የኢትዮጵያ ልብ ከፉከራና ኩራታችን ቀንሰን ዛሬም ለሰላም በራችን ክፍት መሆኑን እንናገራለን። ጦርነት ውስጥ የገባነው ሰላምን በሌላ በምንም መልኩ ለማምጣት ስላልቻልን ነው። ጦርነት ሰላምን የማረጋገጫ የመጨረሻው አማራጭ ነውና። ከጦርነት ወደ ሰላም ለመምጣት ያልቻሉ ኃይሎችን ወደ ሰላም ጠረጴዛ የምናመጣበት የመጨረሻ ጉልበት ነው። በባህላችንም የግጭት መቋጫው ዕርቅና ይቅርታ ነው። ደም የተቃቡ ጠበኞችን ጭምር እስከማጋባት የሚደርስ የዕርቅና የሰላም ዕሴት ያለን ሕዝቦች ነን።

ኢትዮጵያዊ ድል አድራጊነት ምህረትንም ያውቃል። በአድዋ ጦርነት የተማረኩትን የጣልያን ወታደሮች በአሸናፊ ምሕረት ምረናል። በዚህም ጣልያኖች ራሳቸው ተገርመው በሰልፍ እስከ ማመስገን ደርሰው ነበር። ያ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ዕሴት ነው። ዛሬም ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ክብር ላይ ናት። ፍትሕ ያልተለየው ምሕረትን አብሮ በማስኬድ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ እናደርጋለን። በአንድ በኩል በደልና ጥፋትን በፍትሕ መንገድ እያየን፣ በሌላ በኩል ለእርምትና ለይቅርታ ቦታ በመስጠት የምሕረትን መንገድ መከተል አለብን።

ከድላችን ማግሥት አራት ነገሮችን መርሖቻችን አድርገን እንሄድባቸዋለን። 1ኛ – ድላችንን እንዳይቀለበስ አድርገን በሁለንተናዊ መስክ እናጠብቀዋለን። 2ኛ – ድላችን ዘላቂ እንዲሆን በፖለቲካዊና ሰላማዊ መንገዶች እንዲቋጭ እናደርገዋለን። 3ኛ – ድላችንን ለመጠበቅና ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምሕረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን። 4ኛ – ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግግር እና በተሃድሶ ፍትህ እይታ፣ ሃገራዊ ባህሎቻችን እና አሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን። እነዚህ አራቱ መርሖች አንዱ ሌላውን ሳይተካ ሁላችንንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንደ አስፈላጊነታቸው ሁሉንም እንተገብራለን።

በድል፣ በምሕረትና በትኅትና፣ ኢትዮጵያን ዘላቂና የጸናች አሸናፊ እናደርጋታለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ታኅሣሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም


አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

by VOE May 17, 2026
ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

by Ethioreview news April 26, 2026April 26, 2026
ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

by Ethioreview news April 13, 2026April 13, 2026
Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises  

Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises  

by Ethioreview news April 8, 2026April 8, 2026
Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call

Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call

by Ethioreview news April 8, 2026April 8, 2026
እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

by Ethioreview news April 8, 2026April 8, 2026
የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ

የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ

by Ethioreview news April 8, 2026April 8, 2026
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

በሀረሪ ክልል የምስራቅ ዞን የሸኔ የሽብር ቡድን አዛዥ ጃል ኦዳ ቀብሶ በቁጥጥር ስር ዋለ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- “በምክክር ችግሮቻችንን እንፈታልን ጀምረናል፤በዘላቂነት እናሳካዋልን”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ART and CULTURE

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

May 17, 20260
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
ART and CULTURE

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

May 17, 20260
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ May 17, 2026
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news