Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  እመኑ – ኢትዮጵያ ዛሬ አረፈች! የሴራው ዋርካ ተገነደሰ
News

እመኑ – ኢትዮጵያ ዛሬ አረፈች! የሴራው ዋርካ ተገነደሰ

Ethioreview newsEthioreview news—November 2, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሰላም ንግግር እንደሚደረግ እንደተሰማ ” ስምምነት ላይ ከተደረሰ ኢትዮጵያ ታርፋለች፣ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች ይሆኑላታል” የሚል ዜና ጎን ለጎን ተሰማ። የሰላም ስምምነቱ በሚፈለገው መልኩ እውን ከሆነ ትህነግ በብር፣ በትጥቅ፣ በስልጠና፣ በሎጂስቲክ፣ በሴራ፣ በፕሮፓጋንዳና በክህደት የፈለፈላቸው ድርጅቶች፣ ግለሰቦች፣ ተላላኪዎች፣ ሚዲያዎች፣ በቀቀኖች፣ ተሳዳቢዎች፣ ነጮቹን ተከፋዮች ጨምሮ ይነጥፋሉ ነበር ትንቢቱ። ዛሬ እነዚህ ሁሉ ከሰሙ። ወዲያው ኮማ ውስጥ ገብተው የቁም ሞት የሞቱም አሉ።

የዛሬው የስምምነት አሳብ ቀድሞ የገባቸው ተከፋዮች 360 ዲግሪ እየተወራጩ ሲሳደቡ፣ ሲያቅራሩ፣ የመቀመጫቸው ቋጠሮ እስክበጠስ ሲጮሁ ነበር። ማንም ምንም ቢል “አገር ሻጭ” እየተባሉት፣ ኢትዮጵያን ከፋፋይ፣ግድቡን የሸጡ” በሚል ስድብ የሚወርድባቸው አብይ አሕመድ የበቀቀኖቹን ላንቃ ዘግተውታል። መጨረሻውን የምያውቁት አብይ አህመድ አዲስ አመት ላይ ሰላም እንደሚመጣ ሲናገሩ ” ለኢትዮጵያ በሚተቅም መልኩ” ነበር ያሉት። ሆኗል። ካሉትም ያጉደሉት የለም። ስንዴና አኩሪ አተር በገፍ እንዲመረት ትክረት በመስተታቸው፣ የህጻናት መቦረቂያ በማስገንባታቸው፣ ኢትዮጵያ ልይ የተደረተው የጎሳ ፖለቲካ ቆዳ የሚገፈፍበት የሳይንስ ማዕከል በማስገንባታቸው … የስድብ ናዳ የሚወርድባቸው አብይ ” ክብር ለአምላካችን” ሲሉ ነው የሰላሙን ታላቅ ዜና በምስጋና ያወደሱት።

አስኪ ይህን አስቡት – ጌታቸው ሽፈራው እንዳለው– ንግግሩ ከዓመት በፊት ሆኖ ቢሆን ብለን እንጠይቅ

  • ክብር ለጀግኖቻችን!
  • ድርድሩ የተደረገው ትህነግ ደብረብርሃንን፣ ባህርዳርን፣ ጎንደርን ይዞ ቢሆን ኖሮ ትጥቅ ይፍታ ይባል የነበረው ጥምር ጦሩ ነበር።
  • ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አመት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶቻቸውን ባስወጡበት ወቅት ቢሆን ኖሮ ጥምር ጦሩ ያለ እንቅፋት ወደ መቀሌ ይግባ ሳይሆን፣ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ይግባ ነበር የሚባለው።
  • ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ አምና ትህነግ እንደወረረን የባሰ ገፍቶ ቢሆን ኖሮ የጊዜያዊ አስተዳዳሪ መዳቢው ትህነግ ነበር። ያውም እንደህዝብ እንድንኖር ከፈቀደልን።
  • ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና እንደ ጠላቶቻችን ቢሆን ኖሮ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ ትጥቅ አስፈችዎች።
  • ክብር ለጀግኖቻችንና ወልዲያና፣ ላሊበላን፣ ጋሸናና ደባርቅን ይዘው አልተደራደሩም።
  • ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና አላማጣ ትህነግ ያቋረጠው መብራት ተቀጥሎላታል። ዛሬ። ወልቃይት ጠገዴ ነገ የሰሜን ዕዝን ውለታ በትልቅ ድግስ ታከብራለች።
  • ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ ትህነግ አዲስ አበባን ከብቦ ቢሆን ኖሮ አንድ ሰራዊት የሚባለው ተበትኖ፣ የአገር ሰራዊት ለመሆን ይሰባሰብ የነበረው የትህነግ፣ ኦነግ፣ ጉምዝ ታጣቂ ወዘተ ነበር ይላል ጌታቸው ሽፈራው ምን ሃሰት አለው። ክብርና ሞገስ በደምና አጥንቱ እዚህ ድረስ ላደረሰን የመከላከያ ሰራዊት የሚባለው በምክንያት ነውና!! ወደ ዜናው እናምራ

ላለፉት ሶስት ዓመታት አካባቢ ቁጭ ብለው ነገር ሲጠምቁ፣ ሽብር ሲረጩ፣ በሃሰተኛ ወሬ ሕዝብን ሲያሸንሩ የነበሩ፣ ልጆቻቸው ፊት፣ ትዳራቸው ውስጥ፣ ባልደረቦችና ወገኖቻቸው እያዩ በደም ሲነገዱ የነበሩ ተከፋይ ቁማርተኞች ከአሁን በሁዋላ ስራ ፈት ሆኑ። በሚከፈላቸው መጠንና ዲያስፖራውን እያዋከቡ ሲያልቡ የነበሩ ዲጂታል ለማኞች ጉሮሯቸው ተቀረቀረ። ኢትዮጵያ እንደ አገር አሸነፈች። ትግራይ አማራና አፋር ተነፈሱ። የሰላም ዜና መሰማቱ በሕዝብ ዘንድ ሃሴትን ፈጠረ። ውድመትን፣ መከራን፣ ስቃይንና ስደት ለተፈራረቀባችሁ፣ የአብራኮቻችሁን ክፋይ ለተነጠቃችሁ፣ ግፍና በደል ለተፈጸመባችሁ ሁሉ ይህ ቀን ታላቅ ነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ኢትዮጵያ ላይ ሲዛበቱ፣ ሕዝቧን የመከራ ማቅ ሲያለብሱ የነበሩ ሁሉ በሰላም ስምምነቱ እረፍት ቢያጡም፣ ቢከፋቸውም ህዝብ ክፉውን ረስቶ ወደፊት በሰላም ለመጓዝ ዛሬ መንገድ ጅምሯልና አልቃሾች ደረታቸውን ቢመቱም የሚቀየር ነገር እንደማይኖር ከብሽሽቅ ስሜት የራቁ እየገለጹ ነው።

ልክ የኢትዮጵያ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በታረደበት ቀን የተበሰረው የኢትዮጵያ ልጆች የደም ዋጋ ካሁን በሁዋላ ማንም እንዳይነግድበት ሰላሙን ለማጽናት በቀናነት፣ ከተራ የድል አድራጊነት ስሜት፣ ከብሽሽቅና ጥላቻ ራስን በማቀብ መንቀሳቀስ ግድ እንደሆነ የሚያመለክቱ፣ ሰላም ይፋ በሆነ ሰዓታት ውስጥ አዲስ አበባ ተቀምጠው መርዝ መርጨት የጀመሩ የሚድያ ባለሙያ ነን ባዮች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ፣ አስቸኳይ ህግ በማውጣት ጭምር ገደብ እንዲጥል መክረዋል። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ካሁን በሁዋላ በተቀላቢና ተላላኪ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ የመትሰክርበት፣ ህዝብም የሚሰቃይበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም።

በዚህ ሚዲያ የሰላም አማራጭ ንግግሩ ከመጀመሩ ሳምንታት በፊት ትህነግ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን ተጽፎ ነበር። አሜሪካንም “ከዚህ በላይ ጫና ለማድረግ አንችልም” ሲሉ ትህነጎች ትጥቅ እንዲፈቱ ቀጭን ትእዛዝ ማስተላለፏ ተጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል። የትህነግ መሪ ዶክተር ደብረጽዮንም ” ትግሉን ተተኪው ይመራዋል” ሲሉ ነገሩ ቀድሞ ማለቁን አመልክተው ነበር። አቶ ስዬ አብርሃም ” ከንግግሩ ምንም አንጠብቅም” ሲሉ የትግራይን ወጣቶች ለሽምቅ ውጊያ ወገባችሁን አጥብቁ የሚል ጥሪ አሰምተው ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ቴዎድሮስ አድሃኖምም “የዲፕሎማሲ ቃላቶች አለቁብኝ” በሚል ማልቀሳቸው የተስፋ መቁረጥ ምልክት እንደሆነ ተመልክቶ ነበር። አብይ አህመድ በበክላቸው የስንዴ ነዶ ውስጥ ቆመው በኮምባይነር ውቂያ ሲያካሂዱና ማሽን እርሻ ሜዳ ላይ ሲያርመሰምሱ ነገሩ እንዳበቃ ግምት ነበር።

ሁሉም ሆኖ ጉዳዩ ጫናውን ሁሉ በደረማመሰቸው ኢትዮጵያ ምድር ሰላም እንዲሰፍን ህጋዊ ውል ተዘጋጅቶ ይፋ ሆኖ ተጠቃሏል። በዋናነት ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦች እነዚህን ይመስላሉ። ከስምምነቶቹ መካከል ትህነግ ኢትዮጵያን በሚነኩና በብሄራዊ ጥቅሟ ላይ ከሚነሱ ማናቸው አካላት ጋር ግንኙነትም ሆነ ንክኪ አይኖረውም። በአገር ቤትም ከማናቸውም ሃይላት ጋር ድጋፍና ህብረት አይፈጥርም። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ላይ በነጻ አውጪ ስም ከፍለፈላቸው ድርጅቶች ጋር በይፋ ውሉን እንዲቀድ ተደርጓል። ትህነግ የፈታው ትልቁ ትጥቅ ይህ ነው።

  1. ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤
  2. ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
  3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
  4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
  5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
  6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
  7. የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
  8. ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል።

ምንም ተባለ ምን አሁን የሴራው ዋርካ ተገንድሷል። የሴራው ዋርካ ደርቋል። ስሩን መከላከያ በጣጥሶ ጥሎታል። አሁን በድን ሆኗል። በነጻ አውጪ ስም ሲነዳ የነበረው የቅማንት ሽፍታ “በቃኝ” ብሏል። በሰላም ገብቷል። የቤኒሻንጉሉ ተቀላቢ “በቃኝ” ብሎ ለሰልም እጁን ከሰጠ ሁለት ሳምንቱ ነው። ደሞዝና ሎጂስቲክ የቆመበት ሸኔም የዕርቅ ያለህ እያለ ነው። ትህነግንም ከዳኽኝ ብሎ እየረገመ ነው። ብታምኑም ባታምኑም ኢትዮጵያ ድናለች። ዛሬ መከላከያ በተከዳበት ቀን ጸሃይ ወጣ። አምላክ ይፈርዳል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Joint Statement between Ethiopian government and TPLF
የሰላም ስምምነቱ የለውጡን ሂደት እንደሚያሳልጥ አብይ አህመድ አስታወቁ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2