Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የሰላም ስምምነቱ የለውጡን ሂደት እንደሚያሳልጥ አብይ አህመድ አስታወቁ
News

የሰላም ስምምነቱ የለውጡን ሂደት እንደሚያሳልጥ አብይ አህመድ አስታወቁ

Ethioreview newsEthioreview news—November 3, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሰላም ስምምነቱ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚጠቅምና ለውጡንም የማስቀጠል ስራ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ አስታወቁ። በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላሙም እንደግፈዋለን ሲሉም ተናገረዋል።

በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ከአራት ዓመት ብፊት የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማሳለጥ የሚያስችል መሰረት የጣለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ያስታወቁት የሰላም ድርድሩን መጠናቀቅ ተከትሎ ባወጡት የምስጋና ደብዳቤያቸው ነው።

በዚሁ መግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት አሁንም የፀና መሆኑን ጠቅሰው “ስምምነቱ ወደተግባር እንዲለወጥም አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግም በተመሳሳይ ጠንካራ አቋም አለን“ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን ጨምሮ የከፍተኛው ተወካዮች አባላት፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ፉሙዝሊ ምላምቦን በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም አመስግነዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

አያይዘውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፈኪ መሀመድ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን መፍታት የሚለውን የህብረቱን መርህ በመከተል ላበረከቱት አስተዋፅኦም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛንም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ የሰላም ውይይቱን በማስተናገድ ላደረጉት አስተዋፅኦ ኢትዮጵያ አገራቸውንና ህዝባቸውን ታመሰግናለች ብለዋል።

ቡብ ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ዶክተር ዓብይ ሳዉላ-ጎፋ ዉስጥ አቀባበል ላደረጉላቸዉ ባለስልጣናትና ነዋሪዎች እንደነገሩት የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚፀናዉ የጦር ሜዳዉ ድል በሰላም፣የሰላሙ ደግሞ በብልፅግና ሲደገም ነዉ

“ዛሬ ኢትዮጵያና ሰላም ድል አድርገዋል”- ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መናገራቸውን ኢዜአ አመልክቷል። “የዛሬው ቀን ኢትዮጵያና ሰላም ድል ያደረጉበት ቀን ነው” ሲሉ የተናገሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ኢትዮጵያን በመወከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተሰየመው ልዑክ አባል የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን “ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ፤ እኔ ልገልጸው የማልችለው ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ወደፊት መጓዝና ብሩህ ነገር ለመፍጠር መስራት እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል። ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሓት መካከል ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያከበረና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠበቀ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል። ሲሉም አክለዋል።

    ኢትዮጵያዉያን «እንኳን የሰዉ የዱር እንስሳትም መብት ያከብራሉ»ጠሚ ዓብይ

Play Video

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ «በጦር ሜዳ ያገኘነዉ» ያሉት ድል በሰላምም ይደገማል አሉ።ደቡብ ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ዶክተር ዓብይ ሳዉላ-ጎፋ ዉስጥ አቀባበል ላደረጉላቸዉ ባለስልጣናትና ነዋሪዎች እንደነገሩት የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚፀናዉ የጦር ሜዳዉ ድል በሰላም፣የሰላሙ ደግሞ በብልፅግና ሲደገም ነዉ።በመንግስታቸዉ ላይ የሚሰነዘረዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት ወቀሳና ትችትም «እንኳን የሰዉ የዱር እንስሳት መብትም እንጠብቃለን» በማለት አጣጥለዉታል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሳውላ ምን አሉ ?   

ትናንት አመሻሽ ላይ ወደ ደቡብ ክልል ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በክልሉ የጋሞና የጎፋ ዞኖችን ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አቀባበል ለማድረግ ለተሰባሰቡ የከተማይቱ ነዋሪዎች ንግግር አሰምተዋል፡፡ አብይ በዚሁ ንግግራቸው በስም ያልጠቀሷቸው አገራትና ተቋማት በሰው ልጆች መብት አጠባበቅ ላይ ያቀርባሉ ያሏቸውን ክሶች አጣጥለዋል ፡፡ 

‹‹ አንዳንድ አገራት የሰው ልጅ መብት መከበር አለበት ›› የሚሉ ወቀሳና ክሶች ይቀርባሉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ‹‹ ለእነኝህ ወዳጆቼ ያለኝ መልዕክት መጥታችሁ በጎፋና አካባቢው የሚገኘውን የማዜ ፓርክን ተመልከቱ ፡፡ እኛ ኢትዮጲያን የሰው ልጆች መብት ቀርቶ የዝሆንና የአንበሳ መብቶችን  የምንጠብቅ ሰዎች ነን ›› በማለት በሳውላ ከተማ ስታዲየም ለተሰበሰቡ ተዳሚዎች ንግግራቸውን አሰምተዋል ፡፡  

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተሰበሰበ ጎፋ ህዝብ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በደቡባዊ የአገሪቱ ክልል ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት መንግሥታቸው ከህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ጋር እያካሄደ በሚገኘው ጦርነት ዋና ዋና የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን እየገለፁ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላም መድገም አለብን የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳውላ ንግግር መንግሥታቸው በጦርነቱ የበላይነቱን እየያዘ ስለመምጣቱ ይበልጥ ያረጋገጡበት ይመስላል፡፡  

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚሁ ንግግራቸው ‹‹ ከእናንተ ጋር ሆነን በጦርነት ያገኘነውን ድል በሰላም መድገም ይኖርብናል ፡፡ በጦርነት የተገኘ ድል በሰላም ፣ በሰላም የተገኘ ድል ደግሞ በብልፅግና ካልተደገመ  የኢትዮጲያ ህልውና በአንድ ወይም በሌላ መልኩ መደፈሩ አይቀርም ፡፡ ሥለዚህ በአንዱ ድል ሳንኩራራ በጦርነት ያገኘነውን ድል በሰላም በመድገም የማትደፈር ፣ የተከበረችና ለልጆቿ ምቹ የሆነች  ኢትዮጲያን በጋራ እንድንፈጥር አደራ እላለሁ   ›› ብለዋል ፡፡ 

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እየተጎበኘ የሚገኘው የደቡብ ክልል በመዋቅር አደረጃጀት ፣ በወሰን ይገባኛልና የማንነት ጥያቄዎችን መሠረት ያደረጉና ሄድ መለስ የሚሉ ግጭቶች የሚስተዋሉበት ነው፡፡ ያም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አካባቢው ያለውን የመልማት እድል ከመጥቀስ ባለፈ በክልል የአደረጃጀት ጥያቄም ሆነ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በንግግራቸው ያሉት ነገር የለም፡፡ 

የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር  እንድምታ  

ዶቼ ቬለ DW ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ አጥኚውና የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን የሥራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ደያሞ ዳሌ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ያደረጉት ንግግር የራሱ እንድምታ አለው ይላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንና በሰብአዊ መብት ተቋማት ሥም የሚወጡት መግለጫዎች የማሸማቀቅና የማስጨነቅ ዘመቻ አይነት ባህሪ አላቸው ፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው አነኝህ መግለጫዎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን የሚገልጹ እንዳልሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል ፡፡ አኛ ሰብአዊ መብት የመጣስ ባህሪያችንና ባህላችን አይፈቅድልንም ፡፡ ትክክለኛ ባህሪያችን እንደውም ለእንሰሳት ጭምር ማዘንና መብታቸውን ማክበር ነው የሚል መልዕክት ያስተላለፉበት ነው  ›› ብለዋል   

‹‹ በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላምም መድገም ›› በሚል የጠቀሱት ሀሳብ የመንግስታቸውን ቀጣይ አቅጣጫ የሚያመላክት መሆኑን አቶ ደያሞ ተናግረዋል፡፡ 

‹‹ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጦርነት ድል አድረገናል የሚሉት  የፌዴራሉ ምንግሥት ቀደምሲል በአፋርና በአማራ ክልሎች በትግራይ ተዋጊዎች ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ከማስለቀቁም በላይ ትግራ ክልል ውስጥ ተጨማሪ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል ፡፡ በንግግራቸው ማሳየት የፈለጉት ባሸነፉባቸው የትግራይ  አካባቢዎችም ሆነ በተቀሩት የኢትዮጲያ አካባቢዎች ሰላም መስፈን አንዳለበት የጠቆሙበት ነው  ›› ብለዋል አቶ ደያሞ ፡፡ 

ሸዋን ግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
እመኑ – ኢትዮጵያ ዛሬ አረፈች! የሴራው ዋርካ ተገነደሰ
የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2